مريم

Maryam

ሱራ 19 · መካ · 98 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 44

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibከ.ሀ.የ.ዐ.ጸ (ካፍ ሃ ያ ዓይን ሷድ)
  1. Sadiq & Sani Habib(ይህ) ጌታህ ባሪያውን ዘከሪያን በችሮታው ያወሳበት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአለ «ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴ ደከመ፤ ራሴም በሺበት ተንቀለቀለ፤ አንተም በመለመኔ ጌታዬ ሆይ! (ምንጊዜም) ዕድለ ቢስ አልሆንኩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔም ከበኋላዬ ዘመዶቼን በእርግጥ ፈራሁ፡፡ ሚስቴም መካን ነበረች ስለዚህ ከአንተ ዘንድ ለኔ ልጅን ስጠኝ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«የሚወርሰኝ ከያዕቆብ ቤተሰቦችም የሚወርስ የሆነን (ልጅ)፡፡ ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib«ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ ስሙ የሕያ በኾነ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን» (አለው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን የነበረች ስትኾን እኔም ከእርጅና ድርቀትን በእርግጥ የደረስኩ ስኾን እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ጅብሪል) አለ «(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ ጌታህ፡- ከአሁን በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስኾን እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ ሆይ! (እንግዲያውስ) ለእኔ ምልክትን አድርግልኝ አለ፡፡ ምልክትህ ጤናማ ሆነህ ሳለህ ሦስት ሌሊትን (ከነቀናቸው) ሰዎችን ለማነጋገር አለመቻልህ ነው» አለው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከምኩራቡም በሕዝቦቹ ላይ ወጣ፡፡ በ×ትና በማታ (ጌታችሁን) አወድሱ በማለትም ወደነሱ ጠቀሰ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ!» (አልነው)፡፡ ጥበብንም በሕፃንነቱ ሰጠነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእኛም የሆነን ርኅራኄ ንጽሕናንም (ሰጠነው)፡፡ ጥንቁቅም ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለወላጆቹም በጎ ሠሪ ነበር፡፡ ትዕቢተኛ አመጸኛም አልነበረም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበተወለደበት ቀንና በሚሞትበትም ቀን፣ ሕያው ሆኖ በሚነሳበትም ቀን ሰላም በእሱ ላይ ይሁን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመጽሐፉ ውስጥ መርየምንም ከቤተሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለይች ጊዜ (የሆነውን ታሪኳን) አውሳ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፡፡ ጌታህን ፈሪ እንደ ሆንክ (አትቅረበኝ)» አለች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ» አላት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«(በጋብቻ) ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላት «(ነገሩ) እንደዚህሽ ነው፡፡» ጌታሽ «እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፡፡ ለሰዎችም ታምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነው» አለ፤ (ነፋባትም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወዲያውኑም አረገዘችው፡፡ በእርሱም (በሆዷ ይዛው) ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፡፡ «ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ» አለች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት «አትዘኝ፡፡ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም፡፡ እኔ ለአልረሕማን ዝምታን ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም» በይ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደርሱም ጠቀሰች፡፡ «በአንቀልባ ያለን ሕጻን እንዴት እናናግራለን!» አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ሕፃኑም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib«በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib«ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል)፡፡ ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፡፡ ያ በርሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ (ከጉድለት ሁሉ) ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ዒሳ አለ) «አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነውና ተገዙት፡፡ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibከመካከላቸውም አሕዛቦቹ በእርሱ ነገር ተለያዩ፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ወዮላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሚመጡን ቀን ምን ሰሚ ምንስ ተመልካች አደረጋቸው! ግን አመጸኞች ዛሬ (በዚህ ዓለም) በግልጽ ስህተት ውስጥ ናቸው፡፤
  1. Sadiq & Sani Habibእነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ኾነው ሳሉ እነሱም የማያምኑ ሲኾኑ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁልጭቱን ቀን አስፈራራቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ ምድርን በእርሷም ላይ ያለውን ሁሉ እኛ እንወርሳለን፡፡ ወደኛም ይመለሳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምንም አውሳ፡፡ እርሱ በጣም እውነተኛ ነቢይ ነበርና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለአባቱ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን (ጣዖት) ለምን ትግገዛለህ
  1. Sadiq & Sani Habib«አባቴ ሆይ! እኔ ከዕውቀት ያልመጣልህ ነገር በእርግጥ መጥቶልኛልና ተከተለኝ፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«አባቴ ሆይ! እኔ ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጓደኛ ልትኾን እፈራለሁ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib(አባቱም) «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ፡፡ ረዥም ጊዜንም ተወኝ» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ደህና ኹን፡፡ ወደፊት ከጌታዬ ምሕረትን እለምንልሃለሁ፡፡ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነውና» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እናንተንም ከአላህ ሌላ የምትግገዙትንም እርቃለሁ፡፡ ጌታዬንም እግገዛለሁ፡፡ ጌታዬን በመገዛት የማፍር አለመኾኔን እከጅላለሁ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱንም ከአላህ ሌላ የሚግገዙትንም በራቀ ጊዜ ለእርሱ ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው፡፡ ሁሉንም ነቢይ አደረግንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነሱም ከችሮታችን ሰጠናቸው፡፡ ለእነርሱም ከፍ ያለ ምስጉን ዝናን አደረግንላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመጽሐፉ ውስጥ ሙሳንም አውሳ፡፡ እርሱ ምርጥ ነበርና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፡፡ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመጽሐፉ ኢድሪስንም (ሄኖክን) አውሳ፡፡ እርሱ እውነተኛ ነቢይ ነበርና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚህ (ዐሥሩ) እነዚያ አላህ በእነሱ ላይ የለገሰላቸው ከነቢያት ከአዳም ዘር ከኑሕ ጋር (በመርከቢቱ ላይ) ከጫናቸውም (ዘሮች) ከኢብራሂምና ከእስራኤልም ዘሮች ከመራናቸውና ከመረጥናቸውም የኾኑት የአልረሕማን አንቀጾች በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ሰጋጆችና አልቃሾች ኾነው ይወድቃሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibግን የተጸጸተና ያመነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ፡፡ አንዳችንም አይበደሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየመኖሪያን ገነቶች ያችን አልረሕማን ለባሮቹ በሩቅ ኾነው ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸውን (ይገባሉ)፡፡ እርሱ ተስፋው ተፈጻሚ ነውና፤
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሷ ሰላምን እንጂ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡ ለእነሱም በርሷ ውስጥ ጧትም ማታም ሲሳያቸው አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህች ያቺ ከባሮቻችን ጥንቁቆች ለኾኑት የምናወርሳት ገነት ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ጂብሪል አለ) «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እርሱ) የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን
  1. Sadiq & Sani Habibሰውም «በሞትኩ ጊዜ ወደፊት ሕያው ኾኜ (ከመቃብር) እወጣለሁን» ይላል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰው ከአሁን በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲኾን እኛ የፈጠርነው መኾኑን አያስታውስምን
  1. Sadiq & Sani Habibበጌታህ እንምላለን ሰይጣናት ጋር በእርግጥ እንሰበስባቸዋለን፡፡ ከዚያም በገሀነም ዙሪያ የተንበረከኩ ኾነው፤ በእርግጥ እናቀርባቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም ከየጭፍሮቹ ሁሉ ከእነርሱ ያንን (እርሱ) በአልረሕማን ላይ በድፍረት በጣም ብርቱ የኾነውን እናወጣለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም እኛ እነዚያን እነርሱ በእርሷ ለመግባት ተገቢ የኾኑትን እናውቃለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ (መውረዱም) ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ አመጸኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእነሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጽ መስረጃዎች ኾነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «ከሁለቱ ክፍሎች መኖሪያው የሚበልጠውና ሸንጎውም ይበልጥ የሚያምረው ማንኛው ነው» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች እነሱ በቁሳቁስና በትርኢትም በጣም ያማሩትን ብዙዎችን አጥፍተናል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በስሕተት ውስጥ የኾነ ሰው አልረሕማን ለእርሱ ማዘግየትን ያዘገየዋል፡፡ የሚዛትባቸውንም ወይም ቅጣቱን ወይም ሰዓቲቱን ባዩ ጊዜ እርሱ ስፍራው መጥፎና ሰራዊቱ ደካማ የኾነው ሰው ማን እንደኾነ በእርግጥ ያውቃሉ» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል፡፡ መልካሞቹ ቀሪዎች (ሥራዎች) እጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው፡፡ በመመለሻም የተሻሉ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያንንም በአንቀጾቻችን የካደውን «(በትንሣኤ ቀን) ገንዘብም ልጅም በእርግጥ እስሰጣለሁ ያለውንም አየህን»
  1. Sadiq & Sani Habibሩቁን ምስጢር ዐወቀን ወይስ አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ
  1. Sadiq & Sani Habibይከልከል (አይሰጠውም)፡፡ የሚለውን ሁሉ በእርግጥ እንጽፋለን፡፡ ለእርሱም ከቅጣት ጭማሬን እንጨምርለታለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(አልለኝ) የሚለውንም ሁሉ እንወርሰዋለን፡፡ ብቻውንም ኾኖ ይመጣናል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአላህም ሌላ አማልክትን ለእነሱ መከበሪያ (አማላጅ) እንዲኾኑዋቸው ያዙ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይከልከሉ፤ መገዛታቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ ሰይጣናትን በከሓዲዎች ላይ (በመጥፎ ሥራ) ማወባራትን የሚያወባሩዋቸው ሲኾኑ የላክን መኾናችንን አለየህምን
  1. Sadiq & Sani Habibበእነሱም (መቀጣት) ላይ አትቻኮል፡፡ ለእነሱ (ቀንን) መቁጠርን እንቆጥርላቸዋለንና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምእምናንን የተከበሩ ጭፍሮች ኾነው ወደ አልረሕማን የምንሰበስብበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከሓዲዎችንም የተጠሙ ኾነው ወደ ገሀነም የምንነዳበትን (ቀን አስታውስ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእርሱ (ከንግግራቸው) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለአልረሕማን ልጅ አልለው ስለአሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርግጥ (በዕውቀቱ) ከቧቸዋል፡፡ መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሁሉም በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነው ወደርሱ መጪዎች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያመኑና በጎ ሥራዎችን የሠሩ አልረሕማን ለእነሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበምላስህም (ቁርኣንን) ያገራነው በእርሱ ጥንቁቆቹን ልታበስርበት በእርሱም ተከራካሪዎችን ሕዝቦች ልታስፈራራበት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን አጥፍተናል፡፡ ከእነሱ አንድን እንኳ ታያለህን ወይስ ለእነሱ ሹክሹክታን ትሰማለህን