الشعراء
Ash-Shu'ara
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibጠ.ሰ.መ. (ጧ ሲን ሚም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህች ግልጽ ከኾነው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibአማኞች ባለመኾናቸው፤ (በቁጭት) ነፍስህን ገዳይ መኾን ይፈራልሃል፡፡
- Sadiq & Sani Habibብንሻ በእነሱ ላይ ከሰማይ ተዓምረን እናወርድና አንገቶቻቸው (መሪዎቻቸው) ለእርሷ ተዋራጆች ይኾናሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከአልረሕማንም ዘንድ ኣዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸውም፤ ከእርሱ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጂ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርግጥም አስተባበሉ፡፡ የዚያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ወሬዎች (ፍጻሜ) ይመጣባቸዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ምድርም በውስጧ ከመልካም (በቃይ) ጎሳ ሁሉ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ አስደናቂ ምልክት አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊ አዛኝ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም ሙሳን «ወደ በደለኞቹ ሕዝቦች ኺድ» በማለት በጠራው ጊዜ (አስታውስ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ወደ ፈርዖን ሕዝቦች (ኺድ) አላህን አይፈሩምን» (አለው)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳም) አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ልቤም ይጠብባል፡፡ ምላሴም አይፈታም፡፡ ስለዚህ ወደ ሃሩን ላክ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ለእነርሱም በእኔ ላይ (የደም) ወንጀል አልለ፡፡ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(አላህ) አለ «ተው! (አይነኩህም)፡፡ በተዓምራቶቻችንም ኺዱ፡፡ እኛ ከእናንተ ጋር ሰሚዎች ነንና፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ወደ ፈርዖንም ኺዱ፡፡ በሉትም፡- እኛ የዓለማት ጌታ መልክተኞች ነን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የእስራኤልን ልጆች ከእኛ ጋር ልቀቅ፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(ፈርዖንም) አለ «ልጅ ኾነህ በእኛ ውስጥ አላሳደግንህምን በእኛ ውስጥም ከዕድሜህ ብዙ ዓመታትን አልተቀመጥክምን
- Sadiq & Sani Habib«ያችንም የሠራሃትን ሥራህን አልሠራህምን አንተም ከውለታ ቢሶቹ ነህ» (አለ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳም) አለ «ያን ጊዜ እኔም ከተሳሳቱት ኾኜ ሠራኋት፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በፈራኋችሁም ጊዜ ከእንናተ ሸሸሁ፡፡ ጌታየም ለእኔ ጥበብን ሰጠኝ፡፡ ከመልክተኞቹም አደረገኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ይህችም የእስራኤልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻደቅባት ጸጋ ነት፡፡»
- Sadiq & Sani Habibፈርዖን አለ «(ላከኝ የምትለው) የዓለማትም ጌታ ምንድነው»
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳ) «የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምታረጋግጡ ብትኾኑ (ነገሩ ይህ ነው)፤» አለው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ፈርዖንም) በዙሪያው ላሉት ሰዎች «አትሰሙምን» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳ) «ጌታችሁና የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው» አለው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ፈርዖን) «ያ ወደእናንተ የተላከው መልክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳ) «የምሥራቅና የምዕራብ በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ ታውቁ እንደኾናችሁ (እመኑበት)» አለው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ፈርዖን) «ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳ) «በግልጽ አስረጅ ብመጣህም እንኳ» አለው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እንግዲያውስ ከእውነተኞች እንደኾንክ (አስረጁን) አምጣው» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበትሩንም ጣለ፡፡ እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች፡፡
- Sadiq & Sani Habibእጁንም አወጣ፡፡ ወዲያውም እርሷ ለተመልካቾች (የምታበራ) ነጭ ኾነች፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ፈርዖን) በዙሪያው ላሉት መማክርት «ይህ በእርግጥ ዐዋቂ ድግምተኛ ነው» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከምድራችሁ በድግምቱ ሊያወጣችሁ ይፈልጋልና ምንን ታዛላችሁ» (አላቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibአሉት «እርሱን ወንድሙንም አቆይና በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን ላክ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በጣም ዐዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና፡፡»
- Sadiq & Sani Habibድግምተኞቹም በታወቀ ቀን ቀጠሮ ተሰበሰቡ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለሰዎቹም «እናንተ ተሰብስባችኋልን» ተባለ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ድግምተኞቹን እነሱ አሸናፊዎች ቢኾኑ እንከተል ዘንድ» (ተባለ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን» አሉት፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አዎን፤ እናንተም ያን ጊዜ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሙሳ «ለእነርሱ እናንተ የምትጥሉትን ጣሉ» አላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ፡፡ «በፈርዖንም ክብር ይኹንብን፡፡ እኛ በእርግጥ አሸናፊዎቹ እኛ ነን» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሙሳም በትሩን ጣለ፡፡ ወዲያውም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እነሱም) አሉ «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው፡፡ ወደፊትም (የሚያገኛችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (ቀኝና ግራን) በማናጋት እቆረርጣለሁ፡፡ ሁላችሁንም እሰቅላችኋለሁም» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) አሉ «ጉዳት የለብንም፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኛ የምእምናን መጀመሪያ በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡»
- Sadiq & Sani Habibወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና» ስንል ላክን፡፡
- Sadiq & Sani Habibፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እነዚህ ጥቂቶች ጭፈሮች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን፤» (አለ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibአወጣናቸውም፡፡ ከአትክልቶችና ከምንጮች፡፡
- Sadiq & Sani Habibከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁ ለእስራኤል ልጆች አወረስናትም፡፡
- Sadiq & Sani Habibፀሐይዋ ስትወጣም ተከተሉዋቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ(የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ (መታውና) ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን፡፡
- Sadiq & Sani Habibሙሳንም ከእርሱ ገር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ውስጥ ታላቅ ታምር አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእነሱም (በሕዝቦችህ) ላይ የኢብራሂምን ወሬ አንብብላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ትግገዛላችሁ» ባለ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ጣዖታትን እንገዛለን፤ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እርሱም) አለ «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን
- Sadiq & Sani Habib«ወይስ ይጠቅሟችኋልን ወይስ ይጎዷችኋልን»
- Sadiq & Sani Habib«የለም! አባቶቻችን እንደዚሁ ሲሠሩ አገኘን» አሉት፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ትግገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን
- Sadiq & Sani Habib«እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም (የተግገዛችሁትን)፡፡»
- Sadiq & Sani Habib«እነሱም (ጣዖቶቹ) ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር (እርሱ ወዳጄ ነው)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«(እርሱ) ያ የፈጠረኝ ነው፡፡ እርሱም ይመራኛል፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ያም የሚገድለኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibያም በፍርዱ ቀን ኀጢአቴን ለእኔ ሊምር የምከጅለው ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ስጠኝ! በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበኋለኞቹም ሕዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየጸጋይቱን ገነት ከሚወርሱትም አድርገኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአባቴም ማር፡፡ እርሱ ከተሳሳቱት ነበረና፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habibገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»
- Sadiq & Sani Habibገነትም ለፈሪዎች በምትቀረብበት (ቀን)፡፡
- Sadiq & Sani Habibገሀነምም ለጠመሞች በምትገለጽበት (ቀን)፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነሱም በሚባል ቀን «ትግገዟቸው የነበራችሁት የት ናቸው»
- Sadiq & Sani Habib«ከአላህ ሌላ ሲኾኑ ይረዱዋችኋልን ወይስ (ለራሳቸው) ይርረዳሉን»
- Sadiq & Sani Habibበውስጧም እነሱና ጠማሞቹ በፊቶቻቸው ተጥለው ይንከባለላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሰይጣንም ሰራዊቶች መላውም (ይጣላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱም በእርሷ ውስጥ የሚከራከሩ ኾነው ይላሉ፡-
- Sadiq & Sani Habibበአላህ እንምላለን፤ እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነበርን፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ጣዖቶቹን) በዓለማት ጌታ ባስተካከልናችሁ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአመጸኞቹም እንጅ ሌላ አላሳሳተንም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከአማላጆችም ለእኛ ምንም የለንም፡፡
- Sadiq & Sani Habibአዛኝ ወዳጂም (የለንም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእኛም አንዲት ጊዜ መመለስ በኖረችንና ከአማኞቹ በኾን እንመኛለን (ይላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ውስጥ አስደናቂ ግሳጼ አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየኑሕ ሕዝቦች መልክተኞችን አስተባበሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወንድማቸው ኑሕ ለእነሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) «ወራዶቹ የተከተሉህ ኾነህ ለአንተ እናምናለን» አሉት፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እርሱም) አላቸው «ይሠሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ብታውቁ ኖሮ (ይህንን ትርረዱ ነበር)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኔም አማኞችን አባራሪ አይደለሁም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም፡፡»
- Sadiq & Sani Habib«ኑሕ ሆይ! (ከምትለው) ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትኾናለህ» አሉት፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እርሱም) አለ «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ አስተባበሉኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) ፍርድን ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን፡፡»
- Sadiq & Sani Habibእርሱንም ከእርሱ ጋር ያለውንም ሁሉ በተመላው መርከብ ውስጥ አዳን፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰጠምን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ውስጥ ታላቅ ግሳጼ አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓድ መልክተኞችን አስተባበለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibወንድማቸው ሁድ ለነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ለናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የምትጫወቱ ኾናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክትን ትገነባላችሁን
- Sadiq & Sani Habib«የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ሕንፃዎችንም ዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ኾናችሁ ትሠራላችሁን
- Sadiq & Sani Habib«በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ኾናችሁ ትቀጣላችሁን
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ያንንም በምታውቁት (ጸጋ) ያጣቀማችሁን ፍሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእንስሳዎችና በልጆች ያጣቀማችሁን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በአትክልቶችና በምንጮችም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) አሉ «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮቹ ባትኾንም በእኛ ላይ እኩል ነው፤ (ያለንበትን አንለቅም)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ይህ የፊተኞቹ ሰዎች ፀባይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኛም የምንቅቀጣ አይደለንም» (አሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibአስተባበሉትም፡፡ አጠፋናቸውም፡፡ በዚህም ውስጥ እርግጠኛ ግሳጼ አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰሙድ መልክተኞችን አስተባበለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በዚያ እዚህ ባለው (ጸጋ) ውስጥ የረካችሁ ኾናችሁ ትተዋላችሁን
- Sadiq & Sani Habib«በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በኾነች ዘንባባም፤ (ውስጥ ትተዋላችሁን)
- Sadiq & Sani Habib«ብልሆች ኾናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(እነሱም) አሉ «አንተ በብዙ ከተደገመባቸው ሰዎች ብቻ ነህ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አንተ ብጤያችን ሰው እንጅ ሌላ አይደለህም፡፡ ከእውነተኞቹም እንደኾንክ ተዓምርን አምጣ፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(እርሱም) አለ «ይህች ግመል ናት፡፡ ለእርሷ የመጠጥ ፋንታ አላት፡፡ ለእናንተም የታወቀ ቀን ፋንታ አላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በክፉም አትንኳት፡፡ የታላቅ ቀን ቅጣት ይይዛችኋልና፡፡»
- Sadiq & Sani Habibወጓትም፡፡ ወዲያውም ተጸጻቾች ኾነው አነጉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibቅጣቱም ያዛቸው፡፡ በዚህም ውስጥ ግሳፄ አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሉጥ ሕዝቦች መልክተኞችን አስተባባሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ «አትጠነቀቁምን
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከዓለማት ሰዎች ወንዶችን ትመጣላችሁን
- Sadiq & Sani Habib«ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦ ናችሁ፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) አሉ «ሉጥ ሆይ! ባትከለከል በእርግጥ (ከአገር) ከሚወጡት ትኾናለህ፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(እርሱም) አለ «እኔ ሥራችሁን ከሚጠሉት ሰዎች ነኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ ሆይ! እኔንም ቤተሰቦቼንም ከሚሠሩት ሥራ (ቅጣት) አድነን፡፡»
- Sadiq & Sani Habibእርሱንም ቤተሰቦቹንም በጠቅላላ አዳንናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበቀሪዎቹ ውስጥ የኾነች አሮጊት ብቻ ስትቀር (እርሷ ጠፋች)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእነሱም ላይ (የድንጋይን) ዝናምን አዘነምንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናም (ምንኛ) ከፋ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዓምር አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየአይከት ሰዎች መልክተኞችን አስተባበሉ፤
- Sadiq & Sani Habibሹዕይብ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ስፍርን ሙሉ፡፡ ከአጉዳዮቹም አትኹኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ላይ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች (የፈጠረውን) ፍሩ፡፡»
- Sadiq & Sani Habibአሉ «አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች ነህ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አንተም ብጤያችን ሰው እንጅ ሌላ አይደለህም፡፡ እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከእውነተኞቹም እንደኾንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን፡፡»
- Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፤» አላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአስተባበሉትም፡፡ የጥላይቷ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፡፡ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት ነበርና፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዓምር አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእምናን አልነበሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱን ታማኙ መንፈስ (ጂብሪል) አወረደው፤
- Sadiq & Sani Habibከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትኾን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረደው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም (ቁርኣን) በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ (የተወሳ ነው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየእስራኤል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መኾኑ ለእነርሱ (ለመካ ከሓዲዎች) ምልክት አይኾናቸውምን
- Sadiq & Sani Habibከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነውም ኖሮ፤
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱ ላይ ባነበበውም በእርሱ አማኞች አይኾኑም ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁ (ማስተባበልን) በተንኮለኞች ልቦች ውስጥ አስገባነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአሳማሚ ቅጣትን እስከሚያዩ ድረስ በእርሱ አያምኑም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ (ቅጣቱ) ድንገት እስከሚመጣባቸውም ድረስ (አያምኑም)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(በመጣባቸው ጊዜ) «እኛ የምንቆይ ነን» እስከሚሉም (አያምኑም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበቅጣታችን ያቻኩላሉን
- Sadiq & Sani Habibአየህን ብዙ ዓመታትን ብናጣቅማቸው፤
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቢመጣባቸው፤
- Sadiq & Sani Habibይጣቀሙበት የነበሩት ሁሉ ከእነሱ ምንም አያብቃቃቸውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስፈራሪዎች ያሏት (እና ያስተባበለች) ኾና እንጅ አላጠፋንም፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ይህች) ግሳፄ ናት፡፡ በዳዮችም አልነበርንም፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰይጣናትም እርሱን (ቁርኣንን) አላወረዱትም፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱም አይገባቸውም፤ አይችሉምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ (የመላእክትን ንግግር) ከመስማት ተከለከሉ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፤ ከሚቀጡት ትኾናለህና፡፡
- Sadiq & Sani Habibቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከምእምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ፤ (ልዝብ ኹን)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እንቢ» ቢሉህም «እኔ ከምትሠሩት ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአሸናፊ አዛኝ በኾነው (ጌታህ) ላይም ተጠጋ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ ላይ ተጠጋ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን
- Sadiq & Sani Habibበውሸታም ኀጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሰሙትን (ወደ ጠንቋዮች) ይጥላሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም ውሸታሞች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ በ(ንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መኾናቸውን አታይምን
- Sadiq & Sani Habibእነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መኾናቸውን (አታይምን)፤
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ አላህንም በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)፡፡ እነዚያም የበደሉ (ከሞቱ በኋላ) እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡