الروم

Ar-Rum

ሱራ 30 · መካ · 60 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 84

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibአ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሩም ተሸነፈች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበጥቂት ዓመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)፡፡ ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ)፡፡ የሚሻውን ሰው ይረዳል፤ እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ እርዳታን ቀጠረ፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፡፡ እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበነፍሶቻቸው (ሁኔታ) አያስተውሉምን? ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ አላህ በእውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸውም፡፡ ከሰዎቹም ብዙዎቹ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲዎች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበምድር ላይ አይኼዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ አይመለከቱምን? በኀይል ከእነርሱም ይበልጥ የጠነከሩ ነበሩ፡፡ ምድርንም አረሱ፡፡ (እነዚህ) ከአለሟትም የበዛ አለሟት፡፡ መልዕክተ ኞቻቸውም በተዓምራቶች መጡባቸው፤ (አስተባበሉምና ጠፉ)፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም የእነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ በአላህ አንቀጾች በማስተባበላቸውና በእርሷ የሚሳለቁ በመኾናቸው ምክንያት መጥፎ ቅጣት ሆነች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም ይመልሰዋል፤ ከዚያም ወደርሱ ትመለሳላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው (ጣዖታት) አማላጆች አይኖሯቸውም፤ በሚያጋሯቸውም (ጣዖታት) ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰዓቲቱ በምትቆምበት ቀንም በዚያ ቀን ይለያያሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያመኑትና መልካሞችን ሥራዎች የሠሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም የካዱትማ በአንቀጾቻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት፤ (ስገዱለት)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ (የተገባው) ነው፡፡ በሰርክም፤ በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ (አጥሩት)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሕያውን ከሙት ያወጣል፡፡ ሙታንም ከሕያው ያወጣል፡፡ ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል፡፡ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእናንተንም ከዐፈር መፍጠሩ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መኾናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሌሊትና በቀንም መተኛታችሁ፣ ከችሮታውም መፈለጋችሁ ከምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለእናንተ ማሳየቱ፣ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ፣ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይና ምድርም (ያለምሰሶ) በትዕዛዙ መቆማቸው፣ ከዚያም (መልአኩ ለትንሣኤ) ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ነው፡፡ እርሱም (መመለሱ) በእርሱ ላይ በጣም ገር ነው፡፡ ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ከፍተኛ ባሕርይ (አንድነትና ለእርሱ ብጤ የሌለው መኾን) አልለው፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእናንተ ከነፍሶቻችሁ የሆነን ምሳሌ አደረገላችሁ፡፡ (እርሱም) እጆቻችሁ ከያዟቸው (ባሮች) ውስጥ በሰጠናችሁ ጸጋ ለእናንተ ተጋሪዎች አሏችሁን? ታዲያ እናንተና እነርሱ በእርሱ ትክክል ናችሁን? ነፍሶቻችሁን (ብጤዎቻችሁን) እንደምትፈሩ ትፈሯቸዋላችሁን? እንደዚሁ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች፤ አንቀጾችን እንገልጻለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይልቁንም እነዚያ የበደሉ ሰዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ፡፡ አላህም ያጠመመውን ሰው የሚያቀናው ማነው? ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት)፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደእርሱ ተመላሾች ሆናቸሁ (የአላህን ሃይማኖት ያዙ)፡፡ ፍሩትም፡፡ ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁኑ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍሎችም ከሆኑት (አትሁኑ)፡፡ ሕዝብ ሁሉ እነሱ ዘንድ ባለው ነገር ተደሳቾች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰዎችንም ችግር ባገኛቸው ጊዜ ጌታቸውን ወደርሱ ተመላሾች ሆነው ይጠሩታል፡፡ ከዚያም ከእርሱ ችሮታን ባቀመሳቸው ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ወዲያውኑ በጌታቸው (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱ (ያጋራሉ)፡፡ ተጣቀሙም፤ በእርግጥም (መጨረሻችሁን) ወደፊት ታውቃላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእነርሱ ላይ አስረጅ አወረድን? ታዲያ እርሱ በዚያ በእርሱ ያጋሩ በነበሩት ነገር ይናገራልን;(የለም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰዎችንም ችሮታን ባቀመስናቸው ገዜ በእርሷ ይደሰታሉ፡፡ እጆቻቸውም ባሳለፉት ምክንያት መከራ ብታገኛቸው ወዲያውኑ እነርሱ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን የሚያሰፋ የሚያጠብም መሆኑን አያዩምን በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስደናቂ ምልክቶች አልሉበት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው፡፡ ለድኻም ለመንገደኛም (እርዳ)፡፡ ይህ ለእነዚያ የአላህን ፊት (ውዴታውን) ለሚሹ መልካም ነው፡፡ እነዚያም እነርሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከበረከትም በሰዎች ገንዘቦች ውስጥ ይጨመር ዘንድ የምትሰጡት አላህ ዘንድ አይጨምርም፡፡ ከምጽዋትም የአላህን ፊት የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት እነዚያ (ሰጪዎች) አበርካቾች እነርሱ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ነው፡፡ ከምታጋሯቸው (ጣዖታት) ውስጥ ከዚህ ነገር አንዳችን የሚሠራ አለን ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ (በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በምድር ላይ ኺዱ የእነዚያንም በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ» በላቸው፡፡ አብዛኞቻቸው አጋሪዎች ነበሩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለርሱ መመለስ የሌለው ቀን (የትንሣኤ ቀን) ከአላህ ሳይመጣ በፊት ፊትህን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ በዚያ ቀን (ወደ ገነትና ወደ እሳት) ይለያያሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየካደ ሰው ክህደቱ (ጠንቁ) በእርሱው ላይ ነው፡፡ መልካምም የሠሩ ለነፍሶቻቸው (ማረፊያዎችን) ያዘጋጃሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ከችሮታው ይመነዳ ዘንድ (ይለያያሉ)፡፡ እርሱ ከሓዲዎችን አይወድምና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibነፋሶችንም (በዝናብ) ልታበስራችሁ፣ ከችሮታውም (በእርሷ) ሊያቀምሳችሁ፣ መርከቦችም በትዕዛዙ እንዲንሻለሉ፣ ከችሮታውም እንድትፈልጉ፣ ታመሰግኑትም ዘንድ መላኩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአንተ በፊትም መልክተኞችን ወደየሕዝቦቻቸው በእርግጥ ላክን፡፡ በግልጽ ማስረጃዎችም መጡባቸው፡፡ ከእነዚያ ካመጹትም ተበቀልን፡፡ ምእመኖቹንም መርዳት በእኛ ላይ ተገቢ ሆነ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ያ ነፋሶችን የሚልክ ነው፡፡ ደመናንም ይቀሰቅሳሉ፡፡ በሰማይ ላይም እንደሚሻ ይዘረጋዋል፡፡ ቁርጥራጮችም ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከደመናው መካከል ሲወጣ ታያለህ፡፡ በእርሱም ከባሮቹ የሚሻውን በለየ ጊዜ ወዲያውኑ እነሱ ይደሰታሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእነርሱም ላይ ከመወረዱ በፊት ከእርሱ በፊት በእርግጥ ተስፋ ቆራጮች ነበሩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ሕያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ችሮታ ፈለጎች ተመልከት፡፡ ይህ (አድራጊ) ሙታንንም በእርግጥ ሕያው አድራጊ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibነፋስንም (በአዝመራዎች ላይ) ብንልክና ገርጥቶ ቢያዩት ከእርሱ በኋላ በእርግጥ (ችሮታውን) የሚክዱ ይሆናሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንተም ሙታንን አታሰማም፡፡ ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥሪን አታሰማም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንተ ዕውሮችንም ከጥመታቸው የምታቀና አይደለህም፡፡ በአንቀጾቻችን የሚያምኑትን ሰዎች እንጂ ሌላን አታሰማም፡፡ እነርሱም ታዛዦች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ያ ከደካማ (ፍትወት ጠብታ) የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከዚያም ከደካማነት በኋላ ኀይልን አደረገ፡፡ ከዚያም ከብርቱነት በኋላ ደካማነትንና ሽበትን አደረገ፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ እርሱም ዐዋቂው ቻዩ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰዓቲቱ በምትሆንበት ቀን ከሓዲዎች «ከአንዲት ሰዓት በስተቀር (በመቃብር) አልቆየንም» ብለው ይምላሉ፡፡ እንደዚሁ (ከእውነት) ይመለሱ ነበሩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያንም ዕውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ (ፍርድ) እስከ ትንሣኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ፡፡ ይህም (የካዳችሁት) የትንሣኤ ቀን ነው፡፡ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ» ይሏቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያም ቀን እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸውም፡፡ እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌ ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ ገለጽን፡፡ በተዓምርም ብትመጣባቸው እነዚያ የካዱት ሰዎች «እናንተ አበላሺዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibስለዚህ ታገስ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ እነዚያም በትንሣኤ የሚያረጋግጡት አያቅልሉህ፡፡