سبإ

Saba

ሱራ 34 · መካ · 54 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 58

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibምስጋና ለዚያ በሰማያትም ያለ በምድርም ያለ ሁሉ የርሱ ለኾነው ለአላህ ይገባው፡፡ በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ከእርሷም የሚወጣውን ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ሁሉ ያውቃል፡፡ እርሱም አዛኙ መሓሪው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከዚህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ሊመነዳ (ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች)፤ እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማፍረስ የጣሩ እነዚያ ለእነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የኾነ አሳማሚ ስቃይ አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት ያንን ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን እርሱ እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው አላህ መንገድ የሚመራ መኾኑን ያውቃሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም የካዱት «(ሙታችሁ) መበጣጠስን ሁሉ በተበጣጠሳችሁ ጊዜ እናንተ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትኾናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን?» አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበትን? (አሉ)፡፡ እንዳሉት አይደለም፡፡ እነዚያ በመጨረሻይቱ (ዓለም) የሚያምኑት (በእርሷ) በቅጣት ውስጥ (አሁን) በራቀ ስህተትም ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወዳለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ በእነርሱ ምድርን እንደረባባቸዋለን፡፡ ወይም በእነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን፤ በዚህ ውስጥ (ወደ ጌታው) ተመላሽ ለኾነ ባሪያ ሁሉ ምልክት አለበት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለዳውድም ከእኛ የኾነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልንም)፡-«ተራራዎች ሆይ! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ፡፡ በራሪዎችንም (ገራንለት)፡፡ ብረትንም ለእርሱ አለዘብንለት፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibሰፋፊዎችን ጥሩሮች ሥራ፡፡ በአሠራርዋም መጥን፡፡ መልካምንም ሥራ ሥሩ፡፡ እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለሱለይማንም ነፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲኾን ገራንለት፡፡ የነሐስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት፡፡ ከጋኔኖችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሠሩን (አደረግንለት)፡፡ ከነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዲድ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል፡፡ (አልናቸውም) «የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! አመስጋኞች ኾናችሁ (ለጌታችሁ) ሥሩ፡፡» ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን በትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸውም፡፡ በወደቀ ጊዜም ጋኔኖች ሩቅን ምስጢር የሚያወቁ በኾኑ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆይ እንደነበሩ ተረዱ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለሰበእ በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው፡፡ ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች (ነበሯቸው)፡፡ «ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ፡፡ ለእርሱም አመስግኑ፡፡ (አገራችሁ) ውብ አገር ናት፡፡ (ጌታችሁ) መሓሪ ጌታም ነው» (ተባሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ከማመስገን) ዞሩም፡፡ በእነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው፡፡ በአትክልቶቻቸውም ሁለት አትክልቶች፣ ባለመርጋጋ ፍሬዎችን፣ ባለጠደቻና ከቁርቁራም ባለጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመካዳቸው ይህንን መነዳናቸው፤ (እንዲህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲን እንጂ ሌላውን እንቀጣለን?
  1. Sadiq & Sani Habibበእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን፡፡ በእርሷም ጉዞን ወሰንን፡፡ «ጸጥተኞች ኾናችሁ በሌሊቶችም በቀኖችም ተጓዙ፤» (አልን)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም፡፡ ነፍሶቻቸውንም በደሉ፡፡ (መገረሚያ) ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ መገሰጫዎች አሉበት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibኢብሊስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ፤ ከአመኑትም የሆኑት ጭፍሮች በስተቀር ተከተሉት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጅ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረውም፡፡ ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከሰማያትና ከምድር (ዝናብንና በቃይን) የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው፡፡ «አላህ ነው፡፡ እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከአጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም፡፡ ከምትሠሩትም ሥራ አንጠየቅም» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእርሱ ያስጠጋችኋቸውን (ጣዖታት) አሳዩኝ፡፡ ተዉ (አታጋሩ)፤ በእውነቱ እርሱ አሸናፊው ብልሃተኛው አላህ ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ የካዱትም በዚህ ቁርኣን በዚያ ከበፊቱ ባለውም (መጽሐፍ) በጭራሽ አናምንም አሉ፡፡ በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላለሱ ሆነው በጌታቸው ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ፤ (አስደናቂን ነገር ታይ ነበር)፡፡ እነዚያ የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ አማኞች በኾን ነበር» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ከትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም (እናንተው) ከሓዲዎች ነበራችሁ» ይሏቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም፤ በአላህ እንድንክድና ለእርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው» ይላሉ፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በእነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን፡፡ ይሠሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን?
  1. Sadiq & Sani Habibበከተማም አስፈራሪን አልላክንም፡፡ ነዋሪዎችዋ «እኛ በዚያ በርሱ በተላካችሁበት ከሓዲዎች ነን» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን፡፡ እኛም የምንቀጣ አይደለንም» አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበላቸው «ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም፡፡ ያመነና መልካምን የሠራ ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በሠሩት መልካም ሥራ እጥፍ ምንዳ አልላቸው፡፡ እነርሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማበላሸት የሚጥሩት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፡፡ ለእርሱም ያጠብባል፡፡ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፡፡ እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቶቹ «እነዚህ እናንተን ይግገዙ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን (የሚኾነውን አስታውስ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(መላእክቶቹም) «ጥራት ይገባህ ከእነርሱ ሌላ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፡፡ (እንደሚሉት) አይደለም ይልቁንም ጋኔንን ይግገዙ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዛሬም ከፊላችሁ ለከፊሉ መጥቀምንም ኾነ መጉዳትን አይችሉም፡፡ ለእነዚያም ለበደሉት «ያችን በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» እንላቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጽ ኾነው በተነበቡላቸው ጊዜ «ይህ አባቶቻችሁ ይግገዙት ከነበሩት ነገር ሊከለክላችሁ የሚፈልግ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ «ይህም (ቁርኣን) የተቀጣጠፈ ውሸት ነው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡ እነዚያም የካዱት እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው እንጂ ሌላ አይደለም» አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሚያጠኑዋቸው የኾኑ መጽሐፍቶችንም ምንም አልሰጠናቸውም፡፡ ከአንተ በፊትም አስፈራሪ ነቢይን ወደእነርሱ አልላክንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የሰጠናቸውንም ከዐስር አንዱን (እነዚህ) አልደረሱም፡፡ መልክተኞቼንም አስተባበሉ፤ (ነቀፍኳቸውም)፡፡ መንቀፌም እንዴት ነበር!
  1. Sadiq & Sani Habib«የምገስጻችሁ ባንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ (እርሷም) ሁለት ሁለት አንድ አንድም ኾናችሁ ለአላህ እንድትነሱ ከዚያም በጓደኛችሁ (በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መኾኑን መርምራችሁ እንድትርረዱ ነው፡፡ እርሱ ለእናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከዋጋ ማንኛውም የጠየቅኋችሁ ቢኖር እርሱ ለእናንተው ነው፤ ዋጋዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ እውነትን ያወርዳል፡፡ ሩቅ የኾኑትን ምስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው፡፡ ብመራም ጌታዬ ወደኔ በሚያወርደው ነው፡፡ እርሱ ሰሚ ቅርብ ነውና» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበደነገጡና ማምለጫ በሌላቸው ጊዜ ከቅርብ ስፍራም በተያዙ ጊዜ (ኹኔታቸውን) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በእርሱም (አሁን) አመንን» ይላሉ፡፡ ለእነርሱም ከሩቅ ስፍራ (እምነትን) በቀላል ማግኘት ከየታቸው?
  1. Sadiq & Sani Habibበፊትም በእርሱ በእርግጥ ክደዋል፡፡ ከሩቅ ስፍራም በግምት ንግግርን ይጥላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚህ ቀደም በመሰሎቻቸው እንደ ተሠራውም ብጤ በእነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ፡፡ እነርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ነበሩና፡፡