١
- Sadiq & Sani Habibሐ.መ (ሓ.ሚም)፤
٢
- Sadiq & Sani Habibየመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ዐዋቂ ከሆነው አላህ ነው፡፡
٣
- Sadiq & Sani Habibኀጢአትን መሓሪ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣ ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከኾነው (አላህ የወረደ ነው)፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው፡፡
٤
- Sadiq & Sani Habibበአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡
٥
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች ከኋላቸውም አሕዛቦቹ አስተባባሉ፡፡ ሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፡፡ በውሸትም በእርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ፡፡ ያዝኳቸውም፡፡ ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር?
٦
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም የጌታህ ቃል በእነዚያ በካዱት ላይ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች፡፡
٧
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡
٨
- Sadiq & Sani Habib«ጌታችን ሆይ! እነርሱንም፣ ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርዮቻቸውም፣ የበጀውን ሁሉ እነዚያን ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አግባቸው፡፡ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ነህና፡፡
٩
- Sadiq & Sani Habib«ከቅጣቶችም ጠብቃቸው፡፡ በዚያ ቀንም የምትጠብቃውን ሰው በእርግጥ አዘንክለት፡፡» ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
١٠
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩና በምትክዱ ጊዜ አላህ (እናንተን) መጥላቱ ነፍሶቻችሁን (ዛሬ) ከመጥላታችሁ የበለጠ ነው» በማለት ይጥጠራሉ፡፡
١١
- Sadiq & Sani Habib«ጌታችን ሆይ! ሁለትን ሞት አሞትከን፡፡ ሁለትንም ሕይወት ሕያው አደረግከን፡፡ በኃጢኣቶቻችንም መሰከርን፡፡ ታዲያ (ከእሳት) ወደ መውጣት መንገድ አለን?» ይላሉ፡፡
١٢
- Sadiq & Sani Habib«ይህ እነሆ አላህ ብቻውን በተጠራ ጊዜ ስለ ካዳችሁ በእርሱም ተጋሪ ቢደረግ የምታምኑ ስለ ኾናችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርዱ ከፍተኛ ታላቅ ለኾነው አላህ ብቻ ነው፡፡»
١٣
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ (ለአምላክነቱ) ምልክቶቹን የሚያሳያችሁ ለእናንተም ከሰማይ ሲሳይን የሚያወርድላችሁ ነው፡፡ ወደእርሱም የሚመለስ ሰው ቢኾን እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡
١٤
- Sadiq & Sani Habibአላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ኾናችሁ ተገዙት፡፡
١٥
- Sadiq & Sani Habib(እርሱ) ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፡፡ የመገናኛውን ቀን ያስፈራራ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ መንፈስን (ራእይን) ያወርዳል፡፡
١٦
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ (ከመቃብር) በሚወጡበት ቀን በአላህ ላይ ከእነርሱ ምንም ነገር አይደበቅም፡፡ «ንግሥናው ዛሬ ለማን ነው?» (ይባላል፤)፡፡ «ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው» (ይባላል)፡፡
١٧
- Sadiq & Sani Habib«ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳለች፡፡ ዛሬ በደል የለም፡፡ አላህ በእርግጥ ምርመራው ፈጣን ነው» (ይባላል)፡፡
١٨
- Sadiq & Sani Habibቅርቢቱንም (የትንሣኤን) ቀን ልቦች ጭንቀትን የተመሉ ኾነው ላንቃዎች ዘንድ የሚደርሱበትን ጊዜ አስጠንቅቃቸው፡፡ ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡
١٩
- Sadiq & Sani Habib(አላህ) የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡
٢٠
- Sadiq & Sani Habibአላህም በእውነት ይፈርዳል፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚግገዟቸው በምንም አይፈርዱም፡፡ አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡
۞٢١
- Sadiq & Sani Habibየእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይኼዱምን? በኀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች፤ ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ነበሩ፡፡ አላህም በኀጢአቶቻቸው ያዛቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ አልነበራቸውም፡፡
٢٢
- Sadiq & Sani Habibይህ (መያዝ) እነርሱ መልክተኞቻቸው በተዓምራቶች ይመጡባቸው ስለነበሩና ስለ ካዱ ነው፡፡ አላህም ያዛቸው፡፡ እርሱ ኀያል ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
٢٣
- Sadiq & Sani Habibሙሳንም በተዓምራቶቻችንና በግልጽ ማስረጃ በእርግጥ ላክነው፡፡
٢٤
- Sadiq & Sani Habibወደ ፈርዖንና ወደ ሃማን፤ ወደ ቃሩንም (ላክነው)፡፡ «ድግምተኛ ውሸታም ነው» አሉም፡፡
٢٥
- Sadiq & Sani Habibከእኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ «የእነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን ሰዎች ወንዶች ልጆች ግደሉ፤ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ» አሉ፡፡ የከሓዲዎችም ተንኮል በጥፋት ውስጥ እንጅ አይደለም፡፡
٢٦
- Sadiq & Sani Habibፈርዖንም «ተዉኝ፤ ሙሳን ልግደል፡፡ ጌታውንም ይጥራ፡፡ ያድነው እንደኾነ፡፡ እኔ ሃይማኖታችሁን ሊለውጥ፤ ወይም በምድር ውስጥ ጥፋትን ሊያሰራጭ እፈራለሁና» አለ፡፡
٢٧
- Sadiq & Sani Habibሙሳም «እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ በጌታዬና በጌታችሁ ተጠበቅሁ» አለ፡፡
٢٨
- Sadiq & Sani Habibከፈርዖንም ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ምእመን ሰው አለ፡- «ሰውየውን ከጌታችሁ በተዓምራቶች በእርግጥ የመጣለችሁ ሲኾን ‹ጌታዬ አላህ ነው› ስለሚል ትገድላላችሁን? ውሸታምም ቢኾን ውሸቱ በርሱው ላይ ነው፡፡ እውነተኛ ቢኾን ግን የዚያ የሚያሰፈራራችሁ ከፊሉ ያገኛችኋል፡፡ አላህ ያንን እርሱ ድንበር አላፊ ውሸታም የኾነውን አይመራምና፡፡
٢٩
- Sadiq & Sani Habib«ወገኖቼ ሆይ! በምድር ላይ አሸናፊዎች ስትኾኑ ዛሬ መንግስቱ የእናንተ ነው፡፡ ታዲያ ከአላህ ቅጣት ቢመጣብን የሚያድነን ማን ነው?» (አለ)፡፡ ፈርዖን «የማየውን ነገር እንጅ፤ አላመለክታችሁም፡፡ ቅኑንም መንገድ እንጅ አልመራችሁም» አላቸው፡፡
٣٠
- Sadiq & Sani Habibያም ያመነው ሰው አለ «እኔ በናንተ ላይ የአሕዛቦቹን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ፡፡
٣١
- Sadiq & Sani Habib«የኑሕን ሕዝቦች፣ የዓድንና የሰሙድንም፣ የእነዚያንም ከኋላቸው የነበሩትን ልማድ ብጤ (እፈራላችኋለሁ)፡፡ አላህም ለባሮቹ መበደልን የሚሻ አይደለም፡፡
٣٢
- Sadiq & Sani Habib«ወገኖቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ፡፡»
٣٣
- Sadiq & Sani Habibወደ ኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለናንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላችሁም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
٣٤
- Sadiq & Sani Habibዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላቸሁ፡፡ ከዚያም እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም፡፡ በጠፋም ጊዜ «አላህ ከእርሱ ኋላ መልክተኛን በጭራሽ አይልክም» አላችሁ፡፡ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ ተጠራጣሪ የኾነን ሰው ያሳስታል፡፡
٣٥
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ተዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ፡፡ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል፡፡
٣٦
- Sadiq & Sani Habibፈርዖንም አለ «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዢም ሕንጻን ለእኔ ካብልኝ፡፡
٣٧
- Sadiq & Sani Habib«የሰማያትን መንገዶች (እደርስ ዘንድ)፣ ወደ ሙሳም አምላክ እመለከት ዘንድ፡፡ እኔም ውሸታም ነው ብዬ በእርግጥ እጠረጥረዋለሁ» (አለ)፡፡ እንደዚሁም ለፈርዖን መጥፎ ሥራው ተሸለመለት፡፡ ከቅን መንገድም ታገደ፡፡ የፈርዖንም ተንኮል በከሳራ ውስጥ እንጅ አይደለም፡፡
٣٨
- Sadiq & Sani Habibያም ያመነው አለ «ወገኖቼ ሆይ! ተከተሉኝ፡፡ ቀጥታውን መንገድ እመራችኋለሁና፡፡
٣٩
- Sadiq & Sani Habib«ወገኖቼ ሆይ! ይህቺ ቅርቢቱ ሕይወት (ጥቂት) መጣቀሚያ ብቻ ናት፡፡ መጨረሻይቱም ዓለም እርሷ መርጊያ አገር ናት፡፡»
٤٠
- Sadiq & Sani Habib«መጥፎን የሠራ ሰው ብጤዋን እንጅ አይምመነዳም፡፡ እርሱ ምእመን ኾኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ፡፡
۞٤١
- Sadiq & Sani Habib«ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለኔ ምን አለኝ!
٤٢
- Sadiq & Sani Habib«በአላህ ልክድና በእርሱም ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ፡፡ እኔም ወደ አሸናፊው፤ መሓሪው (አላህ) እጠራችኋለሁ፡፡
٤٣
- Sadiq & Sani Habib«በእርግጥ ወደእርሱ የምትጠሩብኝ (ጣዖት) ለእርሱ በቅርቢቱም ኾነ በመጨረሻይቱ ዓለም (ተሰሚ) ጥሪ የለውም፡፡ መመለሻችንም በእርግጥ ወደ አላህ ነው፡፡ ወሰን አላፊዎቹም እነሱ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡
٤٤
- Sadiq & Sani Habib«ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሳላችሁ፡፡ ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ፡፡ አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና፡፡»
٤٥
- Sadiq & Sani Habibከመከሩዋቸውም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፡፡ በፈርዖን ቤተሰቦችም ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው፡፡
٤٦
- Sadiq & Sani Habibእሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትኾንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት (ገሀነምን) አግቡዋቸው» (ይባላል)፡፡
٤٧
- Sadiq & Sani Habibበእሳትም ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ደካማዎቹም ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ (አሁን) ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ፡፡
٤٨
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም የኮሩት «እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን፡፡ አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈረደ» ይላሉ፡፡
٤٩
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም በእሳት ውሰጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ አንድን ቀን ያቃልልን» ይላሉ፡፡
٥٠
- Sadiq & Sani Habib(ዘበኞቹም) «መልእክተኞቻችሁ በተዓምራቶች ይመጡላችሁ አልነበሩምን?» ይላሉ፡፡ (ከሓዲዎቹም) «እንዴታ መጥተውናል እንጅ፤ (ግን አስተባበልናቸው)» ይላሉ፡፡ «እንግዲያውስ ጸልዩ፡፡ የከሓዲዎችም ጸሎት በከንቱ እንጅ አይደለም» ይሏቸዋል፡፡
٥١
- Sadiq & Sani Habibእኛ መልክተኞቻችንን፣ እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ሕይወት ምስክሮችም በሚቆሙበት ቀን በእርግጥ እንረዳለን፡፡
٥٢
- Sadiq & Sani Habibበደለኞችን ምክንያታቸው በማይጠቅማቸው ቀን (እንረዳለን)፡፡ ለእነርሱም ርግማን አልላቸው፡፡ ለእነርሱም መጥፎ አገር አልላቸው፡፡
٥٣
- Sadiq & Sani Habibሙሳንም መምሪያን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ የእስራኤልንም ልጆች መጽሐፉን አወረስናቸው፡፡
٥٤
- Sadiq & Sani Habibለባለ አእምሮዎች መሪና ገሳጭ ሲኾን፡፡
٥٥
- Sadiq & Sani Habib(ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፡፡ ለስህተትህም ምሕረትን ለምን፡፡ ከቀትር በኋላም በማለዳም ጌታሀን ከማመስገን ጋር አጥራው፡፡
٥٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ አንቀጾች የሚከራከሩ በልቦቻቸው ውስጥ እነርሱ ደራሾቹ ያልኾኑት ኩራት ብቻ እንጅ ምንም የለም፡፡ በአላህም ተጠበቅ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነውና፡፡
٥٧
- Sadiq & Sani Habibሰማያትንና ምድርን መፍጠር ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
٥٨
- Sadiq & Sani Habibዕውርና የሚያይ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሠሩና መጥፎ ሠሪው አይስተካከሉም፡፡ በጣም ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡
٥٩
- Sadiq & Sani Habibሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ በእርሷ ጥርጥር የለም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡
٦٠
- Sadiq & Sani Habibጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡
٦١
- Sadiq & Sani Habibአላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ) ቀንንም (ልትሠሩበት) የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው፡፡ አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡
٦٢
- Sadiq & Sani Habibይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡
٦٣
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁ እነዚያ በአላህ አንቀጾች ይክዱ የነበሩት (ከእምነት) ይመለሳሉ፡፡
٦٤
- Sadiq & Sani Habibአላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፡፡ የቀረጻችኁም ቅርጻችሁንም ያሳመረ ከጣፋጮችም ሲሳዮች የሰጣችሁ ነው፡፡ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ፡፡
٦٥
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሃይማኖትንም ለእርሱ ያጠራችሁ ስትኾኑ «ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይኹን» የምትሉ ኾናችሁ ተገዙት፡፡
۞٦٦
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዙዋቸውን እንዳልገዛ ተከልክያለሁ፡፡ ለዓለማት ጌታም እንድገዛ ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡
٦٧
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሕጻናት አድርጎ ያወጣችኋል፡፡ ከዚያም ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፤ ከዚያም ሽማግሌዎች ትኾኑ ዘንድ (ያቆያችኋል)፡፡ ከእናንተም ውስጥ ከዚህ በፊት የሚሞት አልለ፡፡ (ይህንንም ያደረገው ልትኖሩና) የተወሰነ ጊዜንም ልትደርሱ ታውቁም ዘንድ ነው፡፡
٦٨
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለውን «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል፡፡
٦٩
- Sadiq & Sani Habibወደእነዚያ በአላህ አንቀጾች ወደሚከራከሩት (ከእምነት) እንዴት እንደሚመለሱ አታይምን?
٧٠
- Sadiq & Sani Habibወደእነዚያ በመጽሐፉ በዚያም መልክተኞቻችንን በእርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉት (አታይምን?) ወደፊትም ያውቃሉ፡፡
٧١
- Sadiq & Sani Habibእንዛዝላዎቹና ሰንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በእርሷ) ይጎተታሉ፡፡
٧٢
- Sadiq & Sani Habibበገሀነም ውስጥ (ይጎተታሉ)፤ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ፡፡
٧٣
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ለእነርሱ ይባላሉ (በአላህ) «ታጋሯቸው የነበራችሁት የታሉ?»
٧٤
- Sadiq & Sani Habib«ከአላህ ሌላ (የምታጋሩዋቸው)፤ ከኛ ተሰወሩን?» «ከቶ ከዚህ በፊት ምንንም የምንገዛ አልነበርንም» ይላሉ፤ እንደዚሁ አላህ ከሓዲዎችን ያሳስታል፡፡
٧٥
- Sadiq & Sani Habibይህ (ቅጣት) ያላግባብ በምድር ውሰጥ ትደሰቱ በነበራችሁትና ትንበጣረሩ በነበራችሁት ነው (ይባላሉ)፡፡
٧٦
- Sadiq & Sani Habibየገሀነምን በሮች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ (ይባላሉ)፡፡ የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ!
٧٧
- Sadiq & Sani Habibታገስም የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም ብንገድልህ ወደኛ ይመለሳሉ፡፡
٧٨
- Sadiq & Sani Habibካንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አልለ፡፡ ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነው አልለ፡፡ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልኾነ ተዓምርን ሊያመጣ አይገባውም፡፡ የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ በእውነት ይፈረዳል፡፡ እዚያ ዘንድም አጥፊዎቹ ይከስራሉ፡፡
٧٩
- Sadiq & Sani Habibአላህ ያ ለእናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን ከእርሷ (ከፊሏን) ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡
٨٠
- Sadiq & Sani Habibለእናንተም በእርሷ ውስጥ ጥቅሞች አልሏችሁ፡፡ በእርሷም ላይ (እቃን በመጫን) በልቦቻችሁ ያሰባችሁትን ጉዳይ ትደርሱ ዘንድ (ፈጠረላችሁ)፡፡ በእርሷም ላይ በመርከቦችም ላይ ትሳፈራላችሁ፡፡
٨١
- Sadiq & Sani Habibተዓምራቱንም ያሳያችኋል፡፡ ታዲያ ከአላህ ተዓምራት የትኛውን ትክዳላችሁ?
٨٢
- Sadiq & Sani Habibየእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይኼዱምን? ከእነርሱ ይበልጥ ብዙዎች በኀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶችም በጣም ብርቱዎች ነበሩ፡፡ ያም ይሠሩት የነበሩት ከእነርሱ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡
٨٣
- Sadiq & Sani Habibመልክተኞቻቸውም ተዓምራቶችን ባመጡላቸው ጊዜ እነርሱ ዘንድ ባለው ዕውቀት ተደሰቱ፡፡ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣትም በእነርሱ ላይ ሰፈረባቸው፡፡
٨٤
- Sadiq & Sani Habibብርቱ ቅጣታችንንም ባዩ ጊዜ «በአላህ አንድ ሲኾን አምነናል፤ በእርሱም እናጋራ በነበርነው (ጣዖታት) ክደናል» አሉ፡፡
٨٥
- Sadiq & Sani Habibብርቱ ቅጣታችንን ባዩ ጊዜ ማመናቸውም የሚጠቅማቸው አልነበረም፡፡ የአላህን ደንብ ያችን በባሮቹ ውስጥ ያለፈችውን (ተጠንቀቁ) በዚያ ጊዜም ከሓዲዎች ከሰሩ፡፡