١
- Sadiq & Sani Habibሐ.መ (ሐ፡ ሚም)፡፡
٢
- Sadiq & Sani Habibዐ.ሰ.ቀ (ዓይን ሲን ቃፍ)፤
٣
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁ (በዚህች ሱራ ውስጥ እንዳለው) አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ወዳንተ ያወርዳል፡፡ ወደእነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች (አውርዷል)፡፡
٤
- Sadiq & Sani Habibበሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው፡፡
٥
- Sadiq & Sani Habib(ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፡፡ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፡፡ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ ንቁ! አላህ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነው፡፡
٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም ከእርሱ ሌላ (የጣዖታት) ረዳቶችን የያዙ፤ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ ኀላፊ አይደለህም፡፡
٧
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን (የመካን ሰዎች) በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን፡፡ (ከእነርሱም) ከፊሉ በገነት ውሰጥ ከፊሉም በእሳት ውስጥ ነው፡፡
٨
- Sadiq & Sani Habibአላህም በሻ ኖሮ (ባንድ ሃይማኖት ላይ) አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር፡፡ ግን የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባል፡፡ በዳዮችም ለእነርሱ ወዳጅና ረዳት ምንም የላቸውም፡፡
٩
- Sadiq & Sani Habibከእርሱ ሌላ ረዳቶችን ያዙን? (ረዳቶች አይደሉም)፡፡ አላህም ረዳት እርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ሙታንን ሕያው ያደርጋል፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
١٠
- Sadiq & Sani Habibከምንም ነገር ያ በእርሱ የተለያዩበት ፍርዱ ወደ አላህ ነው፡፡ «እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፣ ወደርሱም እመለሳለሁ» (በላቸው)፡፡
١١
- Sadiq & Sani Habibሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡
١٢
- Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር (ድልቦች) መከፈቻዎች የእርሱ ናቸው፡፡ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ እርሱ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
۞١٣
- Sadiq & Sani Habibለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡
١٤
- Sadiq & Sani Habib(የሃይማኖት ሰዎች) ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፡፡ እስከ ተወሰነም ጊዜ (በማቆየት) ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፉን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው፡፡
١٥
- Sadiq & Sani Habibለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ፡፡ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል፡፡ «በላቸውም ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፡፡ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ፡፡ አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው፡፡ ለእኛ ሥራዎቻችን አልሉን፡፡ ለእናንተም ሥራዎቻችሁ አልሏችሁ፡፡ በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም፡፡ አላህ በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ መመለሻም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡»
١٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም በአላህ (ሃይማኖት) ለእርሱ ተቀባይ ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ማስረጃቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ ናት፡፡ በእነርሱም ላይ ቁጣ አልለባቸው፡፡ ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡
١٧
- Sadiq & Sani Habibአላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም (እንደዚሁ)፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል?
١٨
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ፡፡ እነዚያም ያመኑት ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው፡፡ እርሷም እውነት መኾንዋን ያውቃሉ፡፡ ንቁ! እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩት በእርግጥ (ከእውነት) በራቀ ስሕተት ውስጥ ናቸው፡፡
١٩
- Sadiq & Sani Habibአላህ በባሮቹ ሩህሩህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው (በሰፊው) ሲሳይን ይሰጣል፡፡ እርሱም ብርቱው አሸናፊው ነው፡፡
٢٠
- Sadiq & Sani Habib(በሥራው) የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ለእርሱ በአዝመራው ላይ እንጨምርለታለን፡፡ የቅርቢቱንም ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ከእርሷ (የተወሰነለትን ብቻ) እንሰጠዋለን፡፡ ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ፋንታ የለውም፡፡
٢١
- Sadiq & Sani Habibከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ በደለኞችም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አልላቸው፡፡
٢٢
- Sadiq & Sani Habibበደለኞችን ከሠሩት ሥራ (ዋጋ በትንሣኤ ቀን) ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ ነው፡፡ እነዚያም ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት በገነቶች ጨፌዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡
٢٣
- Sadiq & Sani Habibይህ (ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ባሮቹን የሚያበስርበት ነው፡፡ «በእርሱ (መልክቴን በማድረሴ) ላይ በዝምድና ውዴታን እንጅ ዋጋን አልጠይቃችሁም» በላቸው፡፡ መልካሚቱንም ሥራ የሚሠራ ሰው ለእርሱ በእርሷ መልካምን ነገር እንጨምርለታለን፡፡ አላህ መሓሪ አመስጋኝ ነውና፡፡
٢٤
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢሻ በልብህ ላይ ያትማል፡፡ አላህም ውሸቱን ያብብሳል፡፡ እውነቱንም በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
٢٥
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል፣ ከኃጢአቶችም ይቅር የሚል፣ የምትሠሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው፡፡
٢٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያንም ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ልመናቸውን ይቀበላል፡፡ ከችሮታውም ይጨምርላቸዋል፡፡ ከሓዲዎቹም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡
۞٢٧
- Sadiq & Sani Habibአላህም ለባሮቹ (ሁሉ) ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ (ሁሉም) ወሰን ባለፉ ነበር፡፡ ግን የሚሻውን በልክ ያወርዳል፡፡ እርሱ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነውና፡፡
٢٨
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናምን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው፡፡ እርሱም ረዳቱ ምስጉኑ ነው፡፡
٢٩
- Sadiq & Sani Habibሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን (መፍጠሩ) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ እርሱም በሚሻ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው፡፡
٣٠
- Sadiq & Sani Habibከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡
٣١
- Sadiq & Sani Habibእናንተም በምድር ውስጥ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ለእናንተም ከአላህ ሌላ ከዘመድም ከረዳትም ምንም የላችሁም፡፡
٣٢
- Sadiq & Sani Habibበባሕር ላይ እንደ ጋራዎች ኾነው ተንሻላዮቹም (መርከቦች) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው፡፡
٣٣
- Sadiq & Sani Habibቢሻ ነፋሱን የረጋ ያደርገዋል፡፡ በባሕሩም ጀርባ ላይ ረጊዎች ይኾናሉ፡፡ በዚህ ውሰጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለኾነ ሁሉ በእርግጥ ምልክቶች አልሉ፡፡
٣٤
- Sadiq & Sani Habibወይም በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት (በማስጠም) ያጠፋቸዋል፡፡ ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡
٣٥
- Sadiq & Sani Habib(ከእነርሱ ለመበቀል)፤ እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚከራከሩትን ለማወቅ (ያጠፋቸዋል)፡፡ ለእነርሱ ምንም መሸሻ የላቸውም፡፡
٣٦
- Sadiq & Sani Habibከምንም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለእነዚያ ለአመኑትና በጌታቸው ላይ ለሚጠጉት በላጭና ሁል ጊዜ ነዋሪ ነው፡፡
٣٧
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነሱ የሚምሩት ለኾኑት፡፡
٣٨
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው መመካከር ለኾነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት፡፡
٣٩
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ እነርሱ (በመሰሉ) የሚመልሱ ለኾኑት (በላጭና ኗሪ ነው)፡፡
٤٠
- Sadiq & Sani Habibየመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡
٤١
- Sadiq & Sani Habibከተበደሉም በኋላ (በመሰሉ) የተበቀሉ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም (የወቀሳ) መንገድ የለባቸውም፡፡
٤٢
- Sadiq & Sani Habib(የወቀሳ) መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት፣ በምድርም ውስጥ ያለ ሕግ ወሰን በሚያልፉት፣ ላይ ብቻ ነው፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡
٤٣
- Sadiq & Sani Habibየታገስና ምሕረት ያደረገም ሰው ይህ ከምርሮቹ (ከተፈላጊዎቹ) ነገሮች ነው፡፡
٤٤
- Sadiq & Sani Habibአላህ የሚያጠመውም ሰው ከእርሱ በኋለ ለእርሱ ምንም ረዳት የለውም፡፡ በደለኞችንም ቅጣቱን ባዩ ጊዜ ወደ መመለስ መንገድ አልለን? የሚሉ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡
٤٥
- Sadiq & Sani Habibከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ኾነው በዓይን ስርቆት ወደእርሷ (ወደ እሳት) እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀረቡ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡ እነዚያም ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎቹ እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሣኤ ቀን ያከሰሩት ናቸው» ይላሉ፡፡
٤٦
- Sadiq & Sani Habibንቁ! በደለኞች በእርግጥ በዘውታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ዘመዶች ምንም አልነበሩዋቸውም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ (ወደ እውነት) ምንም መንገድ የለውም፡፡
٤٧
- Sadiq & Sani Habibለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህ ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ፡፡ በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም፡፡ ለእናንተም ምንም መካድ የላችሁም፡፡
٤٨
- Sadiq & Sani Habibቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም)፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ ባንተ ላይ ማድረስ እንጅ ሌላ የለብህም፡፡ እኛም ሰውን ከእኛ የኾነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በርሷ ይደሰታል፡፡ እጆቻቸው ባስቀደሙትም ኀጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው (ተስፋ ይቆርጣሉ)፡፡ ሰው (ውለታን) በጣም ከሐዲ ነውና፡፡
٤٩
- Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡
٥٠
- Sadiq & Sani Habibወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡
۞٥١
- Sadiq & Sani Habibለሰውም አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን (መልአክን) የሚልክና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ (በገሃድ) ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡
٥٢
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡
٥٣
- Sadiq & Sani Habibወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ኾነው አላህ መንገድ (ትመራለህ)፡፡ ንቁ! ነገሮቹ ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡