الدخان

Ad-Dukhan

ሱራ 44 · መካ · 59 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 64

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡-
  1. Sadiq & Sani Habibእርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየዘቁመ ዛፍ
  1. Sadiq & Sani Habibየኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib«ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡