المنافقون
Al-Munafiqun
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibመናፍቃን በመጡህ ጊዜ «አንተ የአላህ መልክተኛ መኾንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ፡፡ አላህም አንተ በእርግጥ መልክተኛው መኾንህን ያውቃል፡፡ አላህም መናፍቃን (ከልብ እንመሰክራለን በማለታቸው) ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡
- Sadiq & Sani Habibመሓሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ፡፡ ከአላህም መንገድ ከለከሉ፡፡ እነርሱ ይሠሩት የነበሩት ነገር ከፋ፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ እነርሱ (በምላስ) ያመኑ ከዚያም (በልብ) የካዱ በመኾናቸው ነው፡፡ በልቦቻቸውም ላይ ታተመባቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡
- Sadiq & Sani Habibባየሃቸውም ጊዜ አካሎቻቸው (ግዙፍነታቸው) ያስደንቁሃል፡፡ ቢናገሩም ለንግግራቸው ታዳምጣለህ፤ (ከዕውቀት ባዶ በመኾን)፡፡ እነርሱ ልክ በግድግዳ የተጠጉ ግንዶችን ይመስላሉ፡፡ ጩኸትን ሁሉ በእነርሱ ላይ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ እነርሱ ጠላቶች ናቸውና ተጠንቀቃቸው፡፡ አላህ ይጋደላቸው፤ (ከእምነት) እንዴት ይመለሳሉ!
- Sadiq & Sani Habibለእነሱም ፡- «ኑ የአላህ መልክተኛ ለእናንተ ምሕረትን ይለምንላችኋል፤» በተባሉ ጊዜ ራሶቻቸውን ያዞራሉ፡፡ እነርሱም ትዕቢተኞች ኾነው ሲሸሹ ታያቸዋለህ፡፡
- Sadiq & Sani Habibምሕረትን ብትለምንላቸው ወይም ምሕረትን ባትለምንላቸው በእነርሱ ላይ እኩል ነው፡፡ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አየመራምና፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ እነዚያ ፡- «አላህ መልክተኛ ዘንድ ላሉት ሰዎች እስከሚበታተኑ ድረስ አትቀልቡ» የሚሉ ናቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ድልቦችም የአላህ ናቸው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያወጣል» ይላሉ፡፡ አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለምእምናን ነው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ፡፡ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡
- Sadiq & Sani Habibማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡