١
- Sadiq & Sani Habibአንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
٢
- Sadiq & Sani Habibአላህ ለእናንተ የመሓሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፡፡ አላህም ረዳታችሁ ነው፡፡ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው፡፡
٣
- Sadiq & Sani Habibነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን (ማውራትዋን) ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፡፡ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት፤
٤
- Sadiq & Sani Habibወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ)፡፡ በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፡፡ ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡
٥
- Sadiq & Sani Habib(መላችሁንም) ቢፈታችሁ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ (ለአላህ) ተገዢዎች፣ ጾመኛዎች ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጀላል፡፡
٦
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡
٧
- Sadiq & Sani Habibእላንተ የካዳችሁ ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፡፡ የምትመነዱት ያንን ትሠሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡
٨
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ንጹሕ የኾነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፡፡ ጌታችሁ ከእናንተ ኀጢኣቶቻችሁን ሊሰርይላችሁ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ሊያስገባችሁ ይከጀላልና፡፡ አላህ ነቢዩን፣ እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት ቀን ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲኾን «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፣ ለእኛ ምሕረትም አድርግልን፣ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» ይላሉ፡፡
٩
- Sadiq & Sani Habibአንተ ነቢዩ ሆይ! ከሓዲዎችንና መናፍቃንን ታገል፡፡ በእነርሱም ላይ በርታ፡፡ መኖሪያቸውም ገሀነም ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!
١٠
- Sadiq & Sani Habibአላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑሕን ሴትና የሉጥን ሴት ምሳሌ አደረገ፡፡ ከባሮቻችን ከኾኑ ሁለት መልካም ባሪያዎች ሥር ነበሩ፡፡ ከዱዋቸውም፡፡ ከአላህም (ቅጣት ኑሕና ሉጥ) ከሚስቶቻቸው ምንም አልገፈተሩላቸውም፡፡ ከገቢዎቹም ጋር «እሳትን ግቡ» ተባሉ፡፡
١١
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያ ለአመኑትም የፈርኦንን ሴት አላህ ምሳሌ አደረገ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለእኔ ቤትን ገንባልኝ፡፡ ከፈርዖንና ከሥራውም አድነኝ፡፡ ከበደለኞቹ ሕዝቦችም አድነኝ» ባለች ጊዜ፡፡
١٢
- Sadiq & Sani Habibየዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን (ምሳሌ አደረገ)፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡