١
- Sadiq & Sani Habibአ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህቺ (ሱራ) ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ (ከቁርኣን) አንቀጾች ናት፡፡
٢
- Sadiq & Sani Habib«ሰዎችን አስፈራራ፡፡ እነዚያንም ያመኑትን ለእነሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን አብስር» በማለት ከነርሱው ወደ ኾነ አንድ ሰው ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» አሉ፡፡
٣
- Sadiq & Sani Habibጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) ተደላደለ፡፡ ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና ተገዙት፤ አትገሰጹምን
٤
- Sadiq & Sani Habibሁላችሁም ኾናችሁ መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፡፡ (ይህም) የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው፤ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሠሩትን በትክክል ይመነዳ ዘንድ ይመልሰዋል፡፡ እነዚያ የካዱትም ይክዱት በነበሩት ነገር ለነርሱ ከፈላ ውሃ የኾነ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
٥
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ (በከንቱ) አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡
٦
- Sadiq & Sani Habibሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡
٧
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩ ቅርቢቱንም ሕይወት የወደዱ በእሷም የረኩ እነዚያም እነሱ ከአንቀጾቻችን ዘንጊዎች የኾኑ፡፡
٨
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው፡፡
٩
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል፡፡ ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡
١٠
- Sadiq & Sani Habibበእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡
۞١١
- Sadiq & Sani Habibአላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው (አጥፋን ሲሉት) ክፉን ነገር ቢያስቸኩል ኖሮ ጊዜያቸው ወደነሱ በተፈጸመ ነበር፡፡ እነዚያንም መገናኘታችንን የማይፈሩትን በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ እንተዋቸዋለን፡፡
١٢
- Sadiq & Sani Habibሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምነናል፡፡ ጉዳቱንም ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ወደ አገኘው ጉዳት እንዳልጠራን ሆኖ ያልፋል፡፡ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ይሠሩት የነበሩት ሥራ ተሸለመላቸው፡፡
١٣
- Sadiq & Sani Habibከእናንተ በፊት የነበሩትንም የክፍለ ዘመናት ሰዎች መልክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጧቸው ሲኾኑ በበደሉና የማያምኑም በኾኑ ጊዜ በእርግጥ አጠፋናቸው፡፡ እንደዚሁ ተንኮለኞችን ሕዝቦች እንቀጣለን፡፡
١٤
- Sadiq & Sani Habibከዚያም እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ፡፡
١٥
- Sadiq & Sani Habibአንቀጾቻችንም ግልጽ ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው ይላሉ፡፡ እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም፡፡ ወደእኔ የሚወርደውን እንጂ አልከተልም፡፡ እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ በላቸው፡፡
١٦
- Sadiq & Sani Habibአላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባለነበብኩትም (አላህ) እርሱን ባላሳወቃችሁም ነበር፡፡ በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት (ምንም ሳልል) ብዙን ዕድሜ በእርግጥ ኖሬአለሁ፤ አታውቁምን
١٧
- Sadiq & Sani Habibበአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነሆ አመጸኞች አይድኑም፡፡
١٨
- Sadiq & Sani Habibከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡
١٩
- Sadiq & Sani Habibሰዎችም አንድ ሕዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም፡፡ ተለያዩም፡፡ ከጌታህ ያለፈች ቃልም ባልነበረች ኖሮ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ (በቶሎ) በተፈረደ ነበር፡፡
٢٠
- Sadiq & Sani Habibበእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
٢١
- Sadiq & Sani Habibሰዎችንም ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን (ዝናብና ምቾትን) ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነሱ በተዓምራቶቻችን (በማላገጥ) ተንኮል ይኖራቸዋል፡፡ አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው፡፡
٢٢
- Sadiq & Sani Habibእርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው፡፡ በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች፡፡ ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል፡፡ እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል፡፡
٢٣
- Sadiq & Sani Habibበአዳናቸውም ጊዜ እነሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው፡፡ (እርሱም) የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኛ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን፡፡
٢٤
- Sadiq & Sani Habibየቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡
٢٥
- Sadiq & Sani Habibአላህም ወደ ሰላም አገር ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡
۞٢٦
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸውም፡፡ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
٢٧
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለቻቸው፡፡ ውርደትም ትሸፍናቸዋለች፡፡ ለእነሱ ከአላህ (ቅጣት) ጠባቂ የላቸውም፡፡ ፊቶቻቸው ከጨለመ ሌሊት ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይኾናሉ፡፡ እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው፡፡
٢٨
- Sadiq & Sani Habibሁሉንም የምንሰበስባቸውን ከዚያም ለእነዚያ ለአጋሩት እናንተም ተጋሪዎችሁም ስፍራችሁን ያዙ የምንልበትን ተጋሪዎቻቸውም እኛን ትገዙ አልነበራችሁም የሚሉዋቸው ሲኾኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
٢٩
- Sadiq & Sani Habib«(ጣዖታቶቹ ለእኛ) ከመገዛታችሁ በእርግጥ ዘንጊዎች ለመኾናችንም በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ» (ይሏቸዋል)፡፡
٣٠
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች፡፡ (አጋሪዎች) ወደ አላህም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል፡፡
٣١
- Sadiq & Sani Habib«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
٣٢
- Sadiq & Sani Habibእርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ
٣٣
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ላይ እነርሱ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠች፡፡
٣٤
- Sadiq & Sani Habib«ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ መፍጠርን የሚጀምር ከዚም የሚመልሰው አለን» በላቸው፡፡ «አላህ መፍጠርን ይጀምራል፤ ከዚያም ይመልሰዋል፡፡ ታዲያ (ከእምነት) እንዴት ትዞራላችሁ» በላቸው፡፡
٣٥
- Sadiq & Sani Habib«ከምታጋሩዋቸው፤ ወደ እውነት የሚመራ አለን» በላቸው፡፡ «አላህ ወደ እውነቱ ይመራል፡፡ ወደ እውነት የሚመራው ሊከተሉት የተገባው ነውን ወይስ ካልተመራ በስተቀር የማይመራው ለእናንተም ምን (አስረጅ) አላችሁ እንዴት (በውሸት) ትፈርዳላችሁ» በላቸው፡፡
٣٦
- Sadiq & Sani Habibአብዛኞቻቸውም ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬ ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
٣٧
- Sadiq & Sani Habibይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡
٣٨
- Sadiq & Sani Habibበእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡
٣٩
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም (ከቁርኣን) እውቀቱን ባላደረሱት ፍቹም ገና ባልመጣቸው ነገር አስተባበሉ፡፡ እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የበዳዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡
٤٠
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱም ውስጥ (ወደፊት) በርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ ከእነርሱም በእርሱ የማያምኑ አልሉ፡፡ ጌታህም አጥፊዎቹን በጣም ዐዋቂ ነው፡፡
٤١
- Sadiq & Sani Habib«ቢያስተባብሉህም ለእኔ ሥራዬ አለኝ፡፡ ለእናንተም ሠራችሁ አላችሁ፡፡ እናንተ ከምሠራው ነገር ንጹሕ ናችሁ፡፡ እኔም ከምትሠሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
٤٢
- Sadiq & Sani Habibከእነሱም ወደ አንተ የሚያዳምጡ (እና የማያምኑ) አልሉ፡፡ አንተ ደንቆሮዎችን የማያውቁ ቢኾኑም ታሰማለህን
٤٣
- Sadiq & Sani Habibከእነሱም ወደ አንተ የሚመለከቱ አልሉ፡፡ አንተ (ልበ) ዕውራንን የማያዩ ቢኾኑም ትመራለህን
٤٤
- Sadiq & Sani Habibአላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡
٤٥
- Sadiq & Sani Habib(ከሓዲዎችን) ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ እንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን (አስታውስ)፡፡ እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት በእርግጥ ከሰሩ የተመሩም አልነበሩም፡፡
٤٦
- Sadiq & Sani Habibየዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም (ሳናሳይህ) ብንገድልህ መመለሻቸው ወደ እኛ ነው፡፡ ከዚያም አላህ በሚሠሩት ስራ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡
٤٧
- Sadiq & Sani Habibለሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛ አላቸው፡፡ መልክተኛውም በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉ) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
٤٨
- Sadiq & Sani Habib«እውነተኞችም ከሆናችሁ ይህ (የቅጣቱ) ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ፡፡
٤٩
- Sadiq & Sani Habib«ለራሴ ጉዳትንም ጥቅምንም አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም፡፡ ለሕዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አልላቸው፡፡ ጊዜያቸው በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም» በላቸው፡፡
٥٠
- Sadiq & Sani Habib«ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ፤ አጋሪዎቹ ከርሱ የሚቻኮሉበት ነገር ምንድን ነው ንገሩኝ» በላቸው፡፡
٥١
- Sadiq & Sani Habib«ከዚያም (ቅጣቱ) በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን» (ይባላሉ)፡፡
٥٢
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ለእነዚያ ለበደሉት፡- «ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ትሠሩት የነበረችሁትን ዋጋ እንጂ አትመነዱም» ይባላሉ፡፡
۞٥٣
- Sadiq & Sani Habibእርሱም «እውነት ነውን» (ሲሉ) ይጠይቁሃል፡፡ «አዎን፤ በጌታዬ እምላለሁ፤ እርሱ እውነት ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፤» በላቸው፡፡
٥٤
- Sadiq & Sani Habibለበደለችም ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ቢኖራት ኖሮ በእርግጥ በተበዠችበት ነበር፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በመካከላቸውም በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
٥٥
- Sadiq & Sani Habibንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ንቁ! የአላህ ተስፋ ቃል እርግጥ ነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
٥٦
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
٥٧
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡
٥٨
- Sadiq & Sani Habib«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡
٥٩
- Sadiq & Sani Habib«አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደውን ከእርሱም እርምና የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን» በላቸው፡፡ «አላህ (ይህንን) ለእናንተ ፈቀደላችሁን ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ» በላቸው፡፡
٦٠
- Sadiq & Sani Habibየእነዚያም በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ (ሰዎች) በትንሣኤ ቀን (በአላህ) ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው (አይቀጡም ይመስላቸዋልን) አላህ በሰዎች ላይ (ቅጣትን ባለማቻኮል) የልግስና ባለቤት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑም፡፡
٦١
- Sadiq & Sani Habib(ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛውም ነገር ላይ አትሆንም፣ ከርሱም ከቁርኣን አታነብም፣ ማንኛውንም ሥራ (አንተም ሰዎቹም) አትሠሩም በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ፡፡ በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል ከጌታህ (ዕውቀት) አይርቅም፡፡ ከዚያም ያነሰ የተለቀም የለም፤ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ፡፡
٦٢
- Sadiq & Sani Habibንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡
٦٣
- Sadiq & Sani Habib(እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው፡፡
٦٤
- Sadiq & Sani Habibለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
٦٥
- Sadiq & Sani Habibንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ ኀይል ሁሉ በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
٦٦
- Sadiq & Sani Habibንቁ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡
٦٧
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ)፤ ቀንንም (ልትሠሩበት) ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ፡፡
٦٨
- Sadiq & Sani Habib«አላህ ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ (ከሚሉት) ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ ተብቃቂ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ እናንተ ዘንድ በዚህ (በምትሉት) ምንም አስረጅ የላችሁም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን
٦٩
- Sadiq & Sani Habib«እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ አይድኑም፤» በላቸው፡፡
٧٠
- Sadiq & Sani Habib(እነሱ) በቅርቢቱ ዓለም መጠቀም አላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደእኛ ነው፡፡ ከዚያም ይክዱ በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን፡፡
۞٧١
- Sadiq & Sani Habibየኑሕንም ወሬ በእነሱ ላይ አንብብላቸው፡፡ ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየቴ በአላህም ተዓምራት ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆን፤ በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ፡፡ ነገራችሁንም ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ጋር ሆናችሁ ቁረጡ፡፡ ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን (ግለጹት)፡፡ ከዚያም (የሻችሁትን) ወደእኔ አድርሱ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)፡፡»
٧٢
- Sadiq & Sani Habib«ብትሸሹም (አትጎዱኝም)፡፡ ከምንዳ ምንንም አልለምናችሁምና፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ፡፡»
٧٣
- Sadiq & Sani Habibአስተባበሉትም፡፡ እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው፡፡ (ለጠፉት) ምትኮችም አደረግናቸው፡፡ እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን፡፡ የተስፈራሩትም ሕዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
٧٤
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ከእርሱ በኋላ መልክተኞችን ወደየሕዝቦቻቸው ላክን፡፡ በግልጽ ማስረጃዎችም መጧቸው፡፡ (ከመላካቸው) በፊት በእርሱ ባስተባበሉበትም ነገር፤ የሚያምኑ አልሆኑም፡፡ እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን፡፡
٧٥
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ከእነሱ ኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተዓምራታችን ላክን፡፡ ኮሩም ትዕቢተኞች ሕዝቦችም ነበሩ፡፡
٧٦
- Sadiq & Sani Habibከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡
٧٧
- Sadiq & Sani Habibሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን ይህ ድግምት ነውን»
٧٨
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) አሉ፡- «አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞረን ለእናንተም በምድር ውስጥ ኩራት (ሹመት) ልትኖራችሁ መጣህብን እኛም ለእናንተ አማኞች አይደለንም፡፡»
٧٩
- Sadiq & Sani Habibፈርዖንም፡- «ዐዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ» አለ፡፡
٨٠
- Sadiq & Sani Habibድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ» አላቸው፡፡
٨١
- Sadiq & Sani Habib(ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ያ በርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው፡፡ አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል፡፡ አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና፡፡»
٨٢
- Sadiq & Sani Habibአላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡
٨٣
- Sadiq & Sani Habibለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን ከመፍራት ጋር ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም፡፡ ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ የኮራ ነበር፡፡ እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር፡፡
٨٤
- Sadiq & Sani Habibሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)፡፡»
٨٥
- Sadiq & Sani Habibአሉም፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ሕዝቦች መፈተኛ አታድርገን፡፡»
٨٦
- Sadiq & Sani Habibበእዝነትህም ከከሓዲዎች ሕዝቦች አድነን፡፡
٨٧
- Sadiq & Sani Habibወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ (ለሙሳ) ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን፡፡
٨٨
- Sadiq & Sani Habibሙሳም አለ፡- «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ሕይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ፡፡ ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ (ሰጠሃቸው)፡፡ ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ፡፡ በልቦቻቸውም ላይ አትም፡፡ አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ አያምኑምና፡፡»
٨٩
- Sadiq & Sani Habib(አላህም) «ጸሎታችሁ በእርግጥ ተሰምታለች፡፡ ቀጥም በሉ፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ» አላቸው፡፡
۞٩٠
- Sadiq & Sani Habibየእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ፡፡
٩١
- Sadiq & Sani Habibከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን (አመንኩ ትላለህ)
٩٢
- Sadiq & Sani Habibዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው፡፡
٩٣
- Sadiq & Sani Habibየእስራኤልንም ልጆች ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው፡፡ ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው፡፡ ዕውቀትም (ቁርኣን) እስከመጣቸው ድረስ አልተለያዩም፡፡ ጌታህ በርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡
٩٤
- Sadiq & Sani Habibወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን፡፡
٩٥
- Sadiq & Sani Habibከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡
٩٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ በእነርሱ ላይ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው አያምኑም፡፡
٩٧
- Sadiq & Sani Habibተዓምር ሁሉ ብትመጣላቸውም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ (አያምኑም)፡፡
٩٨
- Sadiq & Sani Habib(ከዩኑስ በፊት ካለፉት ከተሞች) ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን የዩኑስ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡
٩٩
- Sadiq & Sani Habibጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን
١٠٠
- Sadiq & Sani Habibለማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ልታምን (ችሎታ) የላትም፡፡ (አላህ ለከፊሎቹ እምነትን ይሻል)፡፡ በእነዚያም በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡
١٠١
- Sadiq & Sani Habib«በሰማያትና በምድር ያለውን (ተዓምር) ተመልከቱ» በላቸው፡፡ ተዓምራቶችና አስፈራሪዎችም ለማያምኑ ሕዝቦች አይጠቅሙም፡፡
١٠٢
- Sadiq & Sani Habibየእነዚያን ከእነሱ በፊት ያለፉትን ሕዝቦች ቀኖች ብጤ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን «ተጠባበቁ፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡
١٠٣
- Sadiq & Sani Habibከዚያም መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን እናድናለን፡፡ እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን፡፡ (ይህ) በእኛ ላይ ተረጋገጠ፡፡
١٠٤
- Sadiq & Sani Habib«እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፡፡ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡
١٠٥
- Sadiq & Sani Habibፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡
١٠٦
- Sadiq & Sani Habib«ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)፡፡
١٠٧
- Sadiq & Sani Habibአላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለውም፡፡ በጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም፡፡ ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል፡፡ እርሱም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
١٠٨
- Sadiq & Sani Habib«እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ (በእርሱ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ነው፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡
١٠٩
- Sadiq & Sani Habibወዳንተም የሚወረደውን ነገር ተከተል፡፡ አላህም (በነሱ ላይ) እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው፡፡