يس

Ya-Sin

ሱራ 36 · መካ · 83 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 41

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibየ.ሰ.(ያ ሲን)
  1. Sadiq & Sani Habibጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንተ በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበቀጥታም መንገድ ላይ ነህ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአሸናፊ አዛኝ ከሆነው አምላክ መወረድን ተወረደ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ሕዝቦች ልታስጠነቅቅበት (ተወረደ)፡፡ እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአብዛኞቻቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ፡፡ ስለዚህ እነርሱ አያምኑም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን፡፡ እርሷም (እንዛዝላይቱ) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት፡፡ እነርሱም ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከስተፊታቸውም ግርዶን ከስተኋላቸውም ግርዶን አደረግን፡፡ ሸፈንናቸውም፡፡ ስለዚህ እነሱ አያዩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibብታሰጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፡፡ አያምኑም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው፡፡ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ (የኾነውን) ግለጽላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደእነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ (የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡ አልረሕማንም ምንም ነገር አላወረደም፡፡ እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም አሉዋቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(መልክተኞቹም) አሉ «ጌታችን ያውቃል፡፡ እኛ ወደእናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በእኛ ላይም ግልጽ የኾነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib(ሕዝቦቹም) «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ኾን፡፡ ባትከለከሉ በእርግጥ እንወግራችኋለን፡፡ ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ገደ ቢስነታችሁ ከእናንተው ጋር ነው፡፡ ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ» አሏቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣ፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! መልክተኞቹን ተከተሉ» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እነርሱ ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲኾኑ ዋጋን የማየጠይቁዋችሁን ሰዎች ተከተሉ» (አላቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ያንንም የፈጠረኝን፤ ወደርሱም የምትመለሱበትን (ጌታ) የማልገዛ ለእኔ ምን አለኝ?» (አለ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም፤ አያድኑኝምም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ በጌታችሁ አመንኩ፤ ስሙኝም፤» (አለ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ገነትን ግባ» ተባለ፡፡ (እርሱም) አለ፡- «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ ለእኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መኾኑን፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibከእርሱም በኋላ በሕዝቦቹ ላይ (ልናጠፋቸው) ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም፡፡ (በማንም ላይ) አወራጆችም አልነበርንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ቅጣታቸው) አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ኾኑ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበባሮቹ ላይ ዋ ቁልጭት! ከመልክተኛ አንድም አይመጣቸውም በእርሱ የሚሳለቁበት ቢኾኑ እንጅ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንንና እነርሱ ወደነርሱ የማይመለሱ መኾናቸውን አላወቁምን?
  1. Sadiq & Sani Habibሁሉም እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሞተችውም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት! ሕያው አደረግናት፡፡ ከእርሷም ፍሬን አወጣን፤ ከርሱም ይበላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሷም ውሰጥ ከዘምበባዎችና ከወይኖች የኾኑ አትክልቶችን አደረግን፡፡ በእርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከፍሬውና እጆቻቸው ከሠሩትም ይበሉ ዘንድ (ይህን አደረግን)፤ አያመሰግኑምን?
  1. Sadiq & Sani Habibያ ምድር ከምታበቅለው ከነፍሶቻቸውም ከማያውቁትም ነገር ዓይነቶችን ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡ ከእርሱ ላይ ቀንን እንገፍፋለን፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibፀሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲኾን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪኾን ድረስ (መኼዱን) ለካነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም፡፡ ሌሊትም ቀንን (ያለ ጊዜው) ቀዳሚ አይኾንም፡፡ ሁሉም በመዞሪያቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛም (የቀድሞ) ትውልዳቸውን በተሞላች መርከብ ውስጥ የጫን መኾናችን ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibብንሻም እናሰጥማቸዋለን፡፡ ለእነርሱም ረዳት የላቸውም፡፡ እነርሱም የሚድዳኑ አይደሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibግን ከእኛ ለኾነው ችሮታና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም (አዳንናቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱም «በስተፊታችሁና በኋለችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁ ይታዘንላችኋልና» በተባሉ ጊዜ (ፊታቸውን ያዞራሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታቸውም ተዓምራት ማንኛይቱም ተዓምር አትመጣላቸውም፤ ከእርሷ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጅ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱም «አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ» በተባሉ ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን ሰው እናበላለን? እናንተ በግልጽ ስህተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እውነተኞችም እንደኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱ የሚከራከሩ ሲኾኑ በድንገት የምትይዛቸው የኾነችን አንዲትን ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ያን ጊዜ) መናዘዝንም አይችሉም፡፡ ወደ ቤተሰቦቻቸወም አይመለሱም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበቀንዱም ይነፋል፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ (በእርሱ) የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እርሷ) አንዲት ጩኸት እንጂ አይደለችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንም አትበደልም፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም» (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በሥራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱም ሚስቶቻቸውም በጥላዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧ ለእነርሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው፡፡ ለእነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አልላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ለእነርሱም) አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አላቸው።
  1. Sadiq & Sani Habib(ይላልም) «እናንተ አመጸኞች ሆይ! ዛሬ (ከምእምናን) ተለዩ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibየአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን?
  1. Sadiq & Sani Habibተገዙኝም፤ ይህ ቀጥተኘ መንገድ ነው፤ (በማለትም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል፡፡ የምታውቁም አልነበራችሁምን?
  1. Sadiq & Sani Habibይህቺ ያቺ ትቀጠሩዋት የነበረችው ገሀነም ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ ግቧት (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibብንሻም ኖሮ በዐይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር፡፡ መንገድንም (እንደ ልመዳቸው) በተሽቀዳደሙ ነበር፡፡ እንዴትም ያያሉ?
  1. Sadiq & Sani Habibብንሻም ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጠናቸው ነበር፡፡ መኼድንም መመለስንም ባልቻሉም ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዕድሜውንም የምናረዝመውን ሰው በፍጥረቱ (ወደ ደካማነት) እንመልሰዋለን፤ አያውቁምን?
  1. Sadiq & Sani Habib(ሙሐመድን) ቅኔንም አላስተማርነውም፡፡ ለእርሱም አይግገባውም፡፡ እርሱ (መጽሐፉ) መገሰጫና ገላጭ ቁርኣን እንጅ (ቅኔ) አይደለም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ግሣጼነቱም ልቡ) ሕያው የኾነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሓዲዎች ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ እጆቻችን (ኃይሎቻችን) ከሠሩት ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱም ገራናት፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ውስጥ የሚጋልቡት አልለ፡፡ ከእርሷም ይበላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱም በእርሷ ውስጥ (ሌሎች) ጥቅሞች መጠጦችም አሉዋቸው፡፡ ታዲያ አያመሰግኑምን;
  1. Sadiq & Sani Habibመረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አማልክትን ያዙ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመርዳታቸውን አይችሉም፡፡ እነርሱም ለእርሳቸው (ወደ እሳት) የተቀረቡ ሰራዊት ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ እኛ የሚደብቁትንም የሚገልጹትንም እናውቃለንና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰውየው እኛ ከፍቶት ጠብታ የፈጠርነው መኾናችን አላወቀምን? ወዲያውም እርሱ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይኾናልን?
  1. Sadiq & Sani Habibለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ «አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ያ በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ሕያው ያደርጋታል፡፡ እርሱም በፍጡሩ ሁሉ (ኹኔታ) ዐዋቂ ነው» በለው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያ ለእናንተ በእርጥብ ዛፍ እሳትን ያደረገላችሁ ነው፡፡ ወዲያውኑም እናንተ ከእርሱ ታቀጣጥላላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? ነው እንጅ፡፡ እርሱም በብዙ ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ ኹን ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የኾነው ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡