الصافات
As-Saffat
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibመሰለፍን በሚሰለፉት፡፡
- Sadiq & Sani Habibመገሠጽንም በሚገሥጹት፤
- Sadiq & Sani Habibቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibአመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡
- Sadiq & Sani Habibተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?
- Sadiq & Sani Habib«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habibአይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤
- Sadiq & Sani Habibበድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡
- Sadiq & Sani Habibፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡»
- Sadiq & Sani Habib(የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን?
- Sadiq & Sani Habib«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
- Sadiq & Sani Habibእኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibበውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
- Sadiq & Sani Habibምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!
- Sadiq & Sani Habibእርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡
- Sadiq & Sani Habibዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤
- Sadiq & Sani Habibበርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»
- Sadiq & Sani Habibእኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
- Sadiq & Sani Habibኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
- Sadiq & Sani Habib«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?»
- Sadiq & Sani Habib«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?»
- Sadiq & Sani Habibበኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?»
- Sadiq & Sani Habib«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»
- Sadiq & Sani Habib«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»
- Sadiq & Sani Habibጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habibታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!
- Sadiq & Sani Habibራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡
- Sadiq & Sani Habibረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን?
- Sadiq & Sani Habibበዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?
- Sadiq & Sani Habibአላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)?
- Sadiq & Sani Habibአስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን?
- Sadiq & Sani Habibዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤
- Sadiq & Sani Habibእስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?»
- Sadiq & Sani Habibወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?
- Sadiq & Sani Habibንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡-
- Sadiq & Sani Habib«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን?
- Sadiq & Sani Habibለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
- Sadiq & Sani Habibአትገነዘቡምን?
- Sadiq & Sani Habibወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን?
- Sadiq & Sani Habib«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibአላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤
- Sadiq & Sani Habibበእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡
- Sadiq & Sani Habibያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-
- Sadiq & Sani Habib«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤
- Sadiq & Sani Habib«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»
- Sadiq & Sani Habibግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበቅጣታችንም ያቻኩላሉን?
- Sadiq & Sani Habibበቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
- Sadiq & Sani Habibእነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤
- Sadiq & Sani Habibምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡