١
- Sadiq & Sani Habibሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡
٢
- Sadiq & Sani Habibየመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡
٣
- Sadiq & Sani Habibሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በምርና የተወሰነ ጊዜንም በመለካት እንጅ (ለቀልድ) አልፈጠርናቸውም፡፡ እነዚያ የካዱትም ከተስፈራሩት ነገር (ትተው) ዘዋሪዎች ናቸው፡፡
٤
- Sadiq & Sani Habib«ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ፡፡ ወይም በሰማያት ለእነርሱ (ከአላህ ጋር) መጋራት አላቸውን? (ያማልዱናል በማለታችሁ) እውነተኞች እንደ ኾናችሁ ከዚህ (ቁርኣን) በፊት የኾነን መጽሐፍ ወይም ከዕውቀት የኾነ ቅርስን አምጡልኝ» በላቸው፡፡
٥
- Sadiq & Sani Habibእስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡
٦
- Sadiq & Sani Habibሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ (ጣዖቶቹ) ለእነርሱ ጠላቶች ይኾናሉ፡፡ (እነሱን) መገዛታቸውንም ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡
٧
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱትን «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡
٨
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? «ብቀጥፈው ለእኔ ከአላህ (ቅጣት ለማዳን) ምንንም አትችሉም፡፡ እርሱ ያንን በእርሱ የምትቀባዥሩበትን ዐዋቂ ነው፡፡ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በእርሱ በቃ፡፡ እርሱም መሓሪው አዛኙ ነው» በላቸው፡፡
٩
- Sadiq & Sani Habib«ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም፡፡ በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሥሠራም አላውቅም፡፡ ወደእኔ የሚወረደውን እንጅ ሌላን አልከተልም፡፡ እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡
١٠
- Sadiq & Sani Habib(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው «እስቲ ንገሩኝ፤ (ቁርኣኑ) ከአላህ ዘንድ ቢኾን፡፡ በእርሱም ብትክዱ፣ ከእስራኤል ልጆችም መስካሪ በብጤው (በእርሱ) ላይ ቢመሰክር፣ ቢያምንም፣ (ከእምነት) ብትኮሩም፣ (በዳይ አትኾኑምን?)» አላህ በእርግጥ በደለኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡
١١
- Sadiq & Sani Habibእነዚያንም የካዱት ሰዎች ስለእነዚያ ስለ አመኑት ሰዎች (እምነቱ) «መልካም ነገር በኾነ ኖሮ ወደርሱ ባልቀደሙን ነበር» አሉ፡፡ በእርሱም ባልተመሩ ጊዜ «ይህ (ቁርኣን) ጥንታዊ ቅጥፈት ነው» ይላሉ፡፡
١٢
- Sadiq & Sani Habibከበፊቱም የሙሳ መጽሐፍ መሪና ጸጋ ሲኾን አልለ፡፡ ይህም እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ ሲኾን (የፊቶቹን መጻሕፍት) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው፡፡ ለበጎ አድራጊዎችም ብስራት ነው፡፡
١٣
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ ከዚያም ቀጥ ያሉ በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነርሱም አያዝኑም፡፡
١٤
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲኾኑ፡፡ በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ታላቅን ምንዳ (ይምመነዳሉ)፡፡
١٥
- Sadiq & Sani Habibሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ በችግር ላይ ኾና አረገዘችው፡፡ በችግርም ወለደችው፡፡ እርግዝናውና ከጡት መለያውም ሰላሳ ወር ነው፡፡ ጥንካሬውንም ወቅት በደረሰ ጊዜ (ከዚያ አልፎ) አርባ ዓመትንም በደረሰ ጊዜ «ጌታዬ ሆይ! ያችን በእኔ ላይና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም መልካም ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ ዘሮቼንም ለእኔ አብጅልኝ፡፡ እኔ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም ከሙስሊሞ ነኝ» አለ፡፡
١٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚህ (ይህንን ባዮች) በገነት ጓዶች ውስጥ ሲኾኑ እነዚያ ከሠሩት ሥራ መልካሙን ከነሱ የምንቀበላቸውና ከኀጢአቶቻቸውም የምናልፋቸው ናቸው፡፡ ያንን ተስፋ ይስሰጡት የነበሩትን እውነተኛ ቀጠሮ (እንሞላላቸዋለን)፡፡
١٧
- Sadiq & Sani Habibያንንም ለወላጆቹ «ፎህ ለእናንተ ከእኔ በፊት የክፍል ዘመናት ሰዎች (ሳይወጡ) በእርግጥ ያለፉ ሲኾኑ (ከመቃብር) እንድወጥጣ ታስፈራሩኛላችሁን?» ያለውን ሁለቱም (ወላጆቹ) አላህን የሚለምኑ ሲኾኑ (ባታምን) «ወዮልህ፡፡ እመን፡፡ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ ነው፡፡» (ሲሉት) «ይህ የፊተኞቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጅ ሌላ አይደለም» የሚለውንም ሰው (አስታውስ)፡፡
١٨
- Sadiq & Sani Habibእነዚህ እነዚያ ከጋኔንም ከሰውም ከእነርሱ በፊት ካለፉት ሕዝቦች ጋር ቃሉ በእነርሱ ላይ የተረጋገጠባቸው ናቸው፡፡ እነርሱ ከሳሪዎች ነበሩና፡፡
١٩
- Sadiq & Sani Habibለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አልሏቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ (ይህንን መነዳቸው) እነርሱም አይበደሉም፡፡
٢٠
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም የካዱት በእሳት ላይ በሚጋፈጡ ቀን «ጣፋጮቻችሁን በአነስተኛይቱ ሕይወታችሁ አሳለፋችሁ፡፡ በእርሷም ተጣቀማችሁ፡፡ ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጹ በነበራችሁት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትምመነዳላችሁ» (ይባላሉ)፡፡
۞٢١
- Sadiq & Sani Habibየዓድንም ወንድም (ሁድን) ሕዝቦቹን በአሕቃፍ ባስጠነቀቀ ጊዜ አውሳለቸው፡፡ በስተፊቱና በስተኋላውም ብዙ አስፈራሪዎች በእርግጥ አልፈዋል፡፡ «ከአላህ በስተቀር አትግገዙ እኔ በእናነተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁና» በማለት (ባሰጠነቀቀ ጊዜ)፡፡
٢٢
- Sadiq & Sani Habib«ከአማልክቶቻችን ልታዞረን መጣህብን? ከውነተኞቹም እንደኾንክ የምትዝትብንን (ቅጣት) አምጣው» አሉ፡፡
٢٣
- Sadiq & Sani Habib«ዕውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ያን በእርሱ የተላክሁበትንም አደርስላችኋለሁ፡፡ ግን እኔ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ኾናችሁ አያችኋለሁ» አላቸው፡፡
٢٤
- Sadiq & Sani Habibሸለቆዎቻቸውን ተቅጣጪ አግዳሚ ደመና ኾኖ ባዩትም ጊዜ «ይህ አዝናቢያችን የኾነ ደመና ነው» አሉ፡፡ (ሁድም) «አይደለም፤ እርሱ ያ በእርሱ የተቻኮላችሁበት መዐት ነው፡፡ በውስጧ አሳማሚ ስቃይ ያለባት ነፋስ ናት፡፡
٢٥
- Sadiq & Sani Habibበጌታዋ ትዕዛዝ አንዳቹን ሁሉ ታጠፋለች» (አላቸው)፡፡ ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ኾኑ፡፡ እንደዚሁ አመጸኞችን ሕዝቦች ሁሉ እንቀጣለን፡፡
٢٦
- Sadiq & Sani Habibበዚያም እናንተን በእርሱ ባላስመቸንበት (ድሎት) በእርግጥ አስመቸናቸው፡፡ ለእነርሱም መስሚያንና ማያዎችን፣ ልቦችንም አደረግንላቸው፡፡ ግን መስሚያቸውና ማያዎቻቸው፣ ልቦቻቸውም ከእነሱ ምንም አልጠቀሟቸውም፡፡ በአላህ አንቀጾች ይክዱ ነበሩና፡፡ በእነርሱም ላይ ያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ወረደባቸው፡፡
٢٧
- Sadiq & Sani Habibከከተሞችም እነዚያን በአካባቢያችሁ የነበሩትን በእርግጥ አጠፋን (ከክሕደታቸው) ይመለሱም ዘንድ አስረጂዎችን መላለስን፡፡
٢٨
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም መቃረቢያ ይኾኑ ዘንድ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው የያዙዋቸው አይረዷቸውም ኖሯልን? በእርግጥ ከነሱ ራቁ፡፡ ይህም ውሸታቸውና (በልማድ) ይቀጥፉት የነበሩት ነው፡፡
٢٩
- Sadiq & Sani Habibከጋኔን የኾኑን ጭፍሮች ቁርኣንን የሚያዳምጡ ሲኾኑ ወዳንተ ባዞርን ጊዜም (አስታውስ)፡፡ በተጣዱትም ጊዜ ዝም ብላችሁ አዳምጡ ተባባሉ፡፡ በተጨረሰም ጊዜ አስጠንቃቂዎች ኾነው ወደ ሕዝቦቻቸው ተመለሱ፡፡
٣٠
- Sadiq & Sani Habibአሉም «ሕዝቦቻችን ሆይ! እኛ ከሙሳ በኋላ የተወረደን መጽሐፍ በፊቱ ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራ የኾነን ሰማን፡፡
٣١
- Sadiq & Sani Habibወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ጠሪ ተቀበሉ፡፡ በእርሱም እመኑ፡፡ (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና፡፡
٣٢
- Sadiq & Sani Habibየአላህንም ጠሪ የማይቀበል ሰው በምድር ውስጥ የሚያመልጥ አይደለም፡፡ ከእርሱም ሌላ ለእርሱ ረዳቶች የሉትም፡፡ እነዚያ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ናቸው» (አሉ)፡፡
٣٣
- Sadiq & Sani Habibያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? (በማስነሳት) ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡
٣٤
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?» (ይባላሉ)፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ (አላህም) «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል፡፡
٣٥
- Sadiq & Sani Habibከመልክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ፡፡ ለእነርሱም (ለሕዝቦችህ ቅጣት) አትቻኮል፡፡ ያንን የሚስፈራሩበትን ቅጣት በሚያዩ ቀን እነርሱ ከቀን አንዲትን ሰዓት አንጅ እንዳልቆዩ ይኾናሉ፡፡ (ይህ ቁርኣን) በቂ ግሳጼ ነው አመጸኞችም ሕዝቦች እንጅ (ሌሎች) ይጥጠፋሉን?