محمد

Muhammad

ሱራ 47 · መዲና · 38 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 95

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድም የከለከሉ (አላህ) ሥራዎቻቸውን አጠፋባቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመኾናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የኾነን እውነት ስለተከተሉ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያንም የካዱትን (በጦር ላይ) ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኀይል ምቱ፡፡ ባደካማችኋቸውም ጊዜ (አትግደሏቸው ማርኳቸው)፡፡ ማሰሪያውንም አጥብቁ፡፡ በኋላም ወይም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ፤ ወይም ትበዧቸዋላችሁ፡፡ (ይህም) ጦሪቱ መሳሪያዋን እስከምትጥል ድረስ ነው፡፡ (ነገሩ) ይህ ነው፡፡ አላህም ቢሻ ከእነርሱ (ያለጦር) በተበቀለ ነበር፡፡ ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)፡፡ እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ሥራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርግጥ ይመራቸዋል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሃይማኖቱን) ብትረዱ፤ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት (ከሓዲዎች) መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ያዩ ዘንድ በምድር ለይ አልኼዱምን? አላህ በእነርሱ ላይ (ያላቸውን ሁሉ) አጠፋባቸው፡፡ ለከሐዲዎችም ሁሉ ብጤዎችዋ አልሏቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ስለኾነና ከሓዲዎችም ለእነርሱ ረዳት ስለሌላቸው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፡፡ እነዚያም የካዱት (በቅርቢቱ ዓለም) ይጣቀማሉ፡፡ እንስሳዎችም እንደሚበሉ ይበላሉ፡፡ እሳትም ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከከተማም እርሷ ከዚያች ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በኀይል ጠንካራ የኾነች (ባለቤቶችዋን) ያጠፋናቸው ብዙ ናት፡፡ ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታው በኾነች አስረጅ ላይ የኾነ ምእመን ክፉ ሥራቸው ለእነርሱ እንደ ተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉት ነውን?
  1. Sadiq & Sani Habibየዚያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምስል በውስጧ ሺታው ከማይለውጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት፡፡ ለእነርሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ (በያይነቱ) ከጌታቸው ምሕረትም አልላቸው፡፡ (በዚች ገነት ውስጥ ዘውታሪ የኾነ ሰው) እርሱ በእሳት ውስጥ ዘውታሪ እንደኾነ ሰው፣ ሞቃትንም ውሃ እንደተጋቱ፣ አንጀቶቻቸውንም ወዲያውኑ እንደቆራረጠው ነውን? (አይደለም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነርሱም ወዳንተ የሚያዳምጡ አልሉ፡፡ ከአንተም ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ ዕውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ፡፡ እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም የተመሩት (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፡፡ (ከእሳት) መጥጠበቂያቸውንም ሰጣቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መኾንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተወል፡፡ በመጣቻቸውም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል?
  1. Sadiq & Sani Habibእነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህም መዘዋወሪያችሁን፣ መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም ያመኑት ሰዎች (መታገል ያለባት) «ሱራ አትወርድም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ የጠነከረችም ሱራ በተወረደችና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የኾነ መከራ በርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለእነሱም ወዮላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibታዛዥነትና መልካም ንግግር (ይሻላቸዋል) ትዕዛዙም ቁርጥ በኾነ ጊዜ ለአላህ (ትዕዛዝ) እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው፣ ያደነቆራቸውም፣ ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን?
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ለእነርሱ ቅኑ መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን ለእነርሱ መመለሳቸውን ሸለመላቸው፡፡ ለእነርሱም አዝዘናጋቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊል እንታዘዛችኋለን» ያሉ በመኾናቸው ነው፡፡ አላህም መደበቃቸውን ያውቃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመላእክትም ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲኾኑ በገደሉዋቸው ጊዜ (ኹኔታቸው) እንዴት ይኾናል?
  1. Sadiq & Sani Habibይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ስለ ተከተሉ ውዴታውንም ስለ ጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አላህ ቂሞቻቸውን አለማውጣቱን ጠረጠሩን?
  1. Sadiq & Sani Habibበሻንም ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸውም በእርግጥ ባወቅሃቸው ነበር፡፡ ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ፡፡ አላህም ሥራዎቻችሁን ያውቃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእናንተም ታጋዮቹንና ታጋሾቹን እስከምናውቅ፣ ወሬዎቻችሁንም እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልክተኛውን የተከራከሩ አላህን በምንም አይጎዱትም፡፡ ሥራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ የካዱ፣ ከአላህም መንገድ ያገዱ፣ ከዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእናንተም አሸናፊዎቹ ስትኾኑ አላህ ከእናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ፡፡ ወደ ዕርቅም አትጥሩ፡፡ ሥራዎቻችሁንም ፈጽሞ አያጎድልባችሁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት፡፡ ብታምኑም ብትጠነቀቁም ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል፡፡ ገንዘቦቻችሁንም (ሁሉ) አይጠይቃችሁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ፡፡ ቂሞቻችሁንም ያወጣል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibንቁ! እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጥጠሩ ናችሁ፡፡ ከእናንተም ውስጥ የሚሰስት ሰው አልለ፡፡ የሚሰስትም ሰው የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡ ብትሸሹም ሌሎችን ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ ከዚያም (ባለመታዘዝ) ብጤዎቻችሁ አይኾኑም፡፡