١
- Sadiq & Sani Habibእኛ ላንተ ግልጽ የኾነን መክፈት ከፈትንልህ፡፡
٢
- Sadiq & Sani Habibአላህ ከኃጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)፡፡
٣
- Sadiq & Sani Habibአላህ ብርቱን እርዳታ ሊረዳህም (ከፈተልህ)፡፡
٤
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ በምእምናን ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው፡፡ ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
٥
- Sadiq & Sani Habibምእምናንንና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ሊያገባቸው ከነርሱም ኃጢአቶቻቸውን ሊያብስላቸው (በትግል አዘዛቸው)፡፡ ይህም ከአላህ ዘንድ የኾነ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
٦
- Sadiq & Sani Habibበአላህም ክፉ ጥርጣሬን ተጠራጣሪዎቹን መናፍቃንና መናፍቃትን፣ ወንዶች አጋሪዎቻችንና ሴቶች አጋሪዎችንም ያሰቃይ ዘንድ (በትግል አዘዘ)፡፡ በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው፡፡ በእነርሱም ላይ አላህ ተቆጣባቸው፡፡ ረገማቸውም፡፡ ለእነርሱም ገሀነምን አዘጋጀላቸው፡፡ መመለሻነትዋም ከፋች፡፡
٧
- Sadiq & Sani Habibለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
٨
- Sadiq & Sani Habibእኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን በእርግጥ ላክንህ፡፡
٩
- Sadiq & Sani Habibበአላህ ልታምኑ፣ በመልክተኛውም (ልታምኑ)፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም፣ (አላህን) በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም (ላክነው)፡፡
١٠
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ የአላህ እጅ (ኀይሉ) ከእጆቻቸው በላይ ነው፡፡ ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላም ሰው ታላቅ ምንዳን በእርግጥ ይሰጠዋል፡፡
١١
- Sadiq & Sani Habibከአዕራብ ሰዎች እነዚያ (ከዘመቻ) ወደ ኋላ የቀሩት ለአንተ «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸገሩን፤ ስለዚህ ምሕረትን ለምንልን፤» ይሉሃል፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ፡፡ (አላህ) «በእናንተ ላይ ጉዳትን ቢሻ ወይም በእናንተ መጥቀምን ቢሻ ከአላህ (ለማገድ) ለእናንተ አንዳችን የሚችል ማነው? በእውነቱ አላህ፤በምትሠሰሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
١٢
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም መልክተኛውና ምእመናኖቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ፈጽሞ አለመመለሳቸውን ጠረጠራችሁ፡፡ ይህም በልቦቻችሁ ውስጥ ተሸለመላችሁ፡፡ መጥፎንም መጠርጠር ጠረጠራችሁ፡፡ ጠፊዎች ሕዝቦችም ኾናችሁ፡፡
١٣
- Sadiq & Sani Habibበአላህና በመልክተኛው ያላመነም ሰው እኛ ላከሓዲዎች እሳትን አዘጋጅተናል፡፡
١٤
- Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር ንግሥናም የአላህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይምራል፤ የሚሻውንም ይቀጣል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
١٥
- Sadiq & Sani Habibወደ ዘረፋዎች ልትይዟት በኼዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተዉን እንከተላችሁ» ይሏችኋል፡፡ (በዚህም) የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ፡፡ «ፈጽሞ አትከተሉንም፡፡ ይህን (ቃል) ከዚህ በፊት አላህ ብሏል» በላቸው፡፡ ይልቁንም «ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም፡፡ በእውነት እነርሱ ጥቂትን እንጅ የማያውቁ ነበሩ፡፡
١٦
- Sadiq & Sani Habibከአዕራቦች ወደ ኋላ ለቀሩት በላቸው፡- «የብርቱ ጭካኔ ባለቤት ወደ ኾኑ ሕዝቦች (ውጊያ) ወደ ፊት ትጥጠራላችሁ፡፡ ትጋደሏቸዋላችሁ፤ ወይም ይሰልማሉ፡፡ ብትታዘዙም አላህ መልካም ምንዳን ይሰጣችኋል፡፡ ከአሁን በፊት እንደ ሸሻችሁ ብትሸሹም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣችኋል፡፡»
١٧
- Sadiq & Sani Habibበዕውር ላይ (ከዘመቻ በመቅቱ) ኃጢአት የለበትም፡፡ በአንካሳም ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባዋል፡፡ የሚሸሸውንም ሰው አሳማሚውን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
۞١٨
- Sadiq & Sani Habibከምእምናኖቹ በዛፊቱ ሥር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ወደደ፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ ያለውን ዐወቀ፡፡ በእነርሱም ላይ እርጋታን አወረደ፡፡ ቅርብ የኾነንም መክፈት መነዳቸው፡፡
١٩
- Sadiq & Sani Habibብዙዎች ዘረፋዎችንም የሚወስዷቸው የኾኑን (መነዳቸው)፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
٢٠
- Sadiq & Sani Habibአላህ ብዙዎችን ዘረፋዎች የምትወስዷቸው የኾኑን ተስፋ አደረገላችሁ፡፡ ይህችንም ለእናንተ አስቸኮለላችሁ፡፡ ከእናንተም የሰዎችን እጆች ከለከለላችሁ፡፡ (ልታመሰግኑትና) ለምእምናንም ምልክት እንድትኾን ቀጥተኛውን መንገድ ይመራችሁም ዘንድ (ይህንን ሠራላችሁ)፡፡
٢١
- Sadiq & Sani Habibሌላይቱንም በእርሷ ላይ ገና ያልቻላችኋትን አላህ ያወቃትን (ለእናንተ አዘጋጃት)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
٢٢
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም የካዱት (የመካ ሰዎች በሑደይቢያ) በተወጉወችሁ ኖሮ ( ለሺሺት) ጀርባዎችን ባዞሩ ነበር፡፡ ከዚያም ዘመድም ረዳትም አያገኙም፡፡
٢٣
- Sadiq & Sani Habibአላህ ያችን ከዚህ በፊት በእርግጥ ያለፈችውን ልማድ ደነገገ፡፡ ለአላህም ልማድ ለውጥን አታገኝም፡፡
٢٤
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻለችሁ በኋላ እጆቻቸውን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
٢٥
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ እነዚያ የካዱ፣ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ፣ መስዋእቱንም የታሰረ ሲኾን በስፍራው እንዳይደርስ (የከለከሉ) ናቸው፡፡ የማታውቋቸው የኾኑ ምእመናን ወንዶችና ምእምናት ሴቶች (ከከሓዲዎቹ ጋር) ባልነበሩ ያለ ዕውቀት እነርሱን መርገጣችሁና ከእነረሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባልኾነ ኖሮ (እጆቻችሁን ባላገድን ነበር) አላህ የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባ ዝንድ (እጆቻችሁን አገደ)፡፡ በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእነርሱ ውስጥ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር፡፡
٢٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ የካዱት ደራይቱን የመሀይምነቲቱን ደራ በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ (በቀጣናቸው ነበር)፡፡ አላህም በመልክተኛው ላይና በምእምናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ፡፡ መጥጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው፡፡ በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶችዋም ነበሩ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
٢٧
- Sadiq & Sani Habibአላህ ለመልክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲኾን አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት፡፡ (ከእርቁ) ያላወቃችሁትንም ነገር ዐወቀ፡፡ ከዚህም በፊት ቅርብን መክፈት አደረገ፡፡
٢٨
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት በሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡
٢٩
- Sadiq & Sani Habibየአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፡፡ በኢንጂልም ውስጥ ምሳሌያቸው ቀንዘሉን አንደአወጣ አዝመራና፣ (ቀንዘሉ) እንዳበረታው፣ እንደወፈረምና፣ ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ኾኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ (አዝመራ) ነው፡፡ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሓዲዎችን በእነርሱ ሊያስቆጭ ነው፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን የሠሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል፡፡