الذاريات

Adh-Dhariyat

ሱራ 51 · መካ · 60 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 67

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibመበተንን በታኞች በኾኑት (ነፋሶች)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከባድ (ዝናምን) ተሸካሚዎች በኾኑትም (ደመናዎች)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibገር (መንሻለልን) ተንሻላዮች በኾኑትም (መርከቦች)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibነገርን ሁሉ አከፋፋዮች በኾኑትም (መላእክት) እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየምትቀጠሩት (ትንሣኤ) እውነት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እንደየሥራው) ዋጋን ማግኘትም፤ ኋኝ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእናንተ (የመካ ሰዎች) በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስሕተተ ውስጥ ዘንጊዎች የኾኑት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደ ኾነ ይጠይቃሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«መከራችሁን ቅመሱ፤ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው፤ (በገነት ውስጥ ይኾናሉ)፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና (ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አልለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች ምልክቶች አልሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?›
  1. Sadiq & Sani Habibሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ውስጥ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱ ላይ በገቡና «ሰለም» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደ ቤተሰቡም ተዘነበለ፤» ወዲያውም የሰባ ወይፈንን አመጣ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደእነርሱም (አርዶና ጠብሶ) አቀረበው፡፡ «አትበሉም ወይ?» አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነርሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ፡፡ «አትፍራ» አሉት፡፡ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሚስቱም እየጮኸች መጣች፡፡ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚህ ጌታሽ ብሏል፡፡ «እነሆ እርሱ ጥበባ ዐዋቂ ነውና» አሏት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እናንተ መልክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) አሉ፡- «እኛ ወደ አመጸኞች ሕዝቦች ተልከናል፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibበእነርሱ ላይ ከጭቃ የኾኑን ድንጋዮች ልንለቅባቸው (ተላክን)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ (በየስማቸው) ምልክት የተደረገባት ስትኾን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከምእምናንም፤ በእርሷ (በከተማቸው) ውስጥ የነበሩትን አወጣን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧም ከሙስሊሞች ከአንድ ቤት (ቤተሰቦች) በስተቀር አላገኘንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሙሳም (ወሬ) ውስጥ ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም (ከእምነት) ዞረ፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» አለም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው፡፡ እርሱ ተወቃሽ ሲኾን በባሕር ውስጥም ጣልናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበዓድም በእነርሱ ላይ መካንን ነፋስ በላክን ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደ በሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትኾን እንጂ አትተወውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታቸው ትዕዛዝም ኮሩ፡፡ እነርሱም እያዩ ጩኸት ያዘቻቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመቆምንም ምንም አልቻሉም፡፡ የሚርረዱም አልነበሩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየኑሕንም ሕዝቦች ከዚህ በፊት (አጠፋን)፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይንም በኀይል ገነባናት፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምድርንም ዘረጋናት፡፡ ምን ያማርንም ዘርጊዎች (ነን!)
  1. Sadiq & Sani Habibትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና» (በላቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? አይደለም፤ እነርሱ ጥጋበኞች ሕዝቦች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነርሱም (ክርክር) ዘወር በል፤ (ተዋቸው)፡፡ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ (የቅጣት) ፋንታ አልላቸው፡፡ ስለዚህ አያስቸኩሉኝ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለነዚያም ለካዱት ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዮላቸው፡