الطور

At-Tur

ሱራ 52 · መካ · 49 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 76

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibበጡር (ጋራ) እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበተጻፈው መጽሐፍም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበተዘረጋ ብራና ላይ፤ (በተጻፈው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበደመቀው ቤትም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከፍ በተደረገው ጣራም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበተመላው ባሕርም እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእርሱ ምንም ገፍታሪ የለውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይኾናል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተራራዎችም መኼድን በሚኼዱበት (ቀን)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮችም ያን ጊዜ ወዮላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነዚያ እነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለኾኑት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደ ገሀነም እሳት በኀይል መግገፍተርን በሚግገፈተሩበት ቀን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህቺ ያቺ በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ (ፊት ትሉ እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን?
  1. Sadiq & Sani Habibግቧት ታገሱም ወይም አትታገሡ በእናንተ ላይ እኩል ነው፡፡ የምትምመነዱት ትሠሩት የነበራችሁትን (ፍዳ) ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ኾነው (በገነት ውስጥ ናቸው)፡፡ የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ትሠሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ኾናችሁ ብሉ፤ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ኾነው (በገነት ይኖራሉ)፡፡ ዓይናማዎች በኾኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በእምነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን በእነርሱ እናስጠጋለን፡፡ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፡፡ ሰው ሁሉ በሠራው ሥራ ተያዢ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፡፡ በውስጧ ውድቅ ንግግርና መውወንጀልም የለም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ (ለማሳለፍ) ይዘዋወራሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሚጠያየቁ ኾነውም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርን» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«አላህም በእኛ ላይ ለገሰ፡፡ የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን፡፡ እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና» (ይላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ሰዎችን) አስታውስም፡፡ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም ዕብድም አይደለህም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የኾነ ባለ ቅኔ ነው ይላሉን?
  1. Sadiq & Sani Habib«ተጠባበቁ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአእምሮዎቻቸው በዚህ ያዟቸዋልን? አይደለም በእውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወይም «ቀጠፈው ይላሉን?» አይደለም፤ በእውነቱ አያምኑም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእውነተኞችም ቢኾኑ መሰሉ የኾነን ንግግር ያምጡ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ለእነርሱ በእርሱ ላይ (ከሰማይ) የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? አድማጫቸውም (ሰማሁ ቢል) ግልጽን አስረጅ ያምጣ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለእናንተም ወንዶች ልጆች አሏችሁን?
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳው የተከበዱ ናቸውን?
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ሩቁ ምስጢር እነርሱ ዘንድ ነውን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያም የካዱት እነርሱ በተንኮል ተሸናፊዎች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወይስ ለእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከሰማይም ቁራጭን (በእነርሱ ላይ) ወዳቂ ኾኖ ቢያዩ ኖሮ «ይህ የተደራረበ ደመና ነው» ይሉ ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያንንም በእርሱ የሚግገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተንኮላቸው ከእነርሱ ምንንም የማይጠቅማቸውንና እነርሱም የማይርረዱበትን ቀን (እስከ ሚገናኙ ተዋቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነዚያ ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አልላቸው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፡፡ ጌታህንም በምትነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከሌሊቱም አወድሰው፡፡ በከዋክብት መዳበቂያ ጊዜም (ንጋት ላይ አወድሰው)፡፡