الحديد

Al-Hadid

ሱራ 57 · መዲና · 29 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 94

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibበሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፡፡ እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ዐዋቂ ነወ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአላህና በመልክተኛው እመኑ፡፡ (አላህ) በእርሱ ተተኪዎች ባደረጋችሁም ገንዘብ ለግሱ፡፡ እነዚያም ከእናንተ ውስጥ ያመኑትና የለገሱት ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመልክተኛው በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲኾን (ጌታችሁ) ኪዳናችሁንም የያዘባችሁ ሲኾን በአላህ የማታምኑት ለእናንተ ምን አልላችሁ? የምታምኑ ብትኾኑ (ወደ እምነት ቸኩሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ሊያወጣችሁ ያ ግልጾች የኾኑን አንቀጾች በበሪያው ላይ የሚያወርድ ነው፡፡ አላህም ለእናንተ በእርግጥ ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ሲኾን በአላህ መንገድ የማትለግሱትም ለእናንተ ምን አልላችሁ? ከእናንተ ውስጥ (መካን) ከመክፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው (ከተከፈተች በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ጋር) አይስተካከልም፡፡ ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፡፡ ሁሉንም አላህ መልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድር ለእርሱም (አላህ) የሚያነባብርለት ሰው ማነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አልለው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምእመናንንና ምእምናትን በስተፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲኾን በምታያቸው ቀን (ምንዳ አልላቸው)፡፡ ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቁ ዕድል ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመናፍቃንና መናፍቃት ለእነዚያ ለአመኑት «ተመልከቱን፤ ከብርሃናችሁ እናበራለንና» የሚሉበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ «ወደ ኋላችሁ ተመለሱ፡፡ ብርሃንንም ፈልጉ» ይባላሉ፡፡ ግቢው በውስጡ ችሮታ (ገነት) ያለበት ውጭውም ከበኩሉ ስቃይ (እሳት) ያለበት የኾነ (ደጃፍ ባለው አጥር)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከእናንተ ጋር አልነበርንምን?» በማለት ይጠሩዋቸዋል፡፡ «እውነት ነው፡፡ ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ፡፡ (በነቢዩ አደጋዎችን) ተጠባበቃችሁም፡፡ ተጠራጠራችሁም፡፡ የአላህም ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ፡፡ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገስ) ሸነገላችሁ፤» ይሏቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ዛሬም ከእናንተ ቤዛ አይወስድም፡፡ ከእነዚያ ከካዱትም፡፡ መኖሪያችሁ እሳት ናት፡፡ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» (ይሏቸዋል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው የሚያደርጋት መኾኑን ዕወቁ፡፡ ታወቁ ዘንድ አንቀጾችን ለእናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየመጸወቱ ወንዶችና፣ የመጸወቱ ሴቶች፣ ለአላህም መልካምን ብድር ያበደሩ ለእነርሱ መልካም ምንዳ አልላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም በአላህና በመልክተኞቹ ያመኑት እነዚያ እነርሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው፡፡ ለእነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፡፡ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታችሁ ወደ ኾነች ምሕረት፣ ወርዷ እደ ሰማይና ምድር ወርድ ወደ ሆነችም ገነት ተሽቀዳደሙ፡፡ ለእነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ ላመኑት ተዘጋጅታለች፡፡ ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፡፡ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሁሉ አይወድም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በስስት የሚያዝዙ ናቸው፡፡ (ከእውነት) የሚሸሽም ሰው (ጥፋቱ በራሱ ላይ ነው)፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደእነርሱ አወረድን፤ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያልሉበት ሲኾን አወረድን፡፡ (እንዲጠቀሙበት) አላህም ሃይማኖቱንና መልክተኞቹን በሩቅ ኾኖ የሚረዳውን ሰው ሊያውቅ (ሊገልጽ አወረደው)፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibኑሕን፣ ኢብራሂምንም በእርግጥ ላክን፡፡ በዘሮቻቸውም ውስጥ ነቢይነትንና መጽሐፎችን አደረግን፡፡ ከእነርሱም ቅን አልለ፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት (ሰዎች) ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን፣ አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አደረግን፡፡ በእነርሱ ላይ (ምንኩስናን) አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ (ፈጠሩዋት)፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም፤ አልጠበቋትም፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ በመልእክተኛውም እመኑ፡፡ ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና፡፡ ለእናንተም በእርሱ የምትኼዱበት የኾነ ብርሃንን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ይህም) የመጽሐፉ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መኾናቸውን ችሮታም በአላህ እጅ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል ማለትን እንዲያውቁ ነው፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡