الواقعة
Al-Waqi'ah
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibመከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ
- Sadiq & Sani Habibሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
- Sadiq & Sani Habibበተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡
- Sadiq & Sani Habibብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡
- Sadiq & Sani Habibከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibደናግሎችም አደረግናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡
- Sadiq & Sani Habibቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡
- Sadiq & Sani Habibበታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡
- Sadiq & Sani Habibይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?
- Sadiq & Sani Habib«የፊተኞቹ አባቶቻችንም?»
- Sadiq & Sani Habibበላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ!
- Sadiq & Sani Habib« ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»
- Sadiq & Sani Habibይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?
- Sadiq & Sani Habib(በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን?
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?
- Sadiq & Sani Habibእኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
- Sadiq & Sani Habibብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን?
- Sadiq & Sani Habibየምትዘሩትንም አያችሁን?
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
- Sadiq & Sani Habibብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡
- Sadiq & Sani Habibያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን?
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
- Sadiq & Sani Habibብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?
- Sadiq & Sani Habibያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?
- Sadiq & Sani Habibእኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibየታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?
- Sadiq & Sani Habibሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?
- Sadiq & Sani Habib(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡
- Sadiq & Sani Habibየማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡