الأنعام

Al-An'am

ሱራ 6 · መካ · 165 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 55

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibምስጋና ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው ጨለማዎችንና ብርሃንንም ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ ከዚያም እነዚያ የካዱት (ጣዖታትን በጌታቸው) ያስተካክላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም (የሞት) ጊዜን የወሰነ ነው፡፡ እርሱም ዘንድ (ለትንሣኤ) የተወሰነ ጊዜ አልለ፡፡ ከዚያም እናንተ (በመቀስቀሳችሁ) ትጠራጠራላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ በሰማያትና በምድር (ሊግገዙት የሚገባው) አላህ ነው፡፡ ምስጢራችሁን ግልጻችሁንም ያውቃል፡፡ የምትሠሩትንም ሁሉ ያውቃል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታቸውም አንቀጾች አንዲትም አንቀጽ አትመጣቸውም ከርሷ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጅ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእውነቱም (ቁርኣን) በመጣላቸው ጊዜ በእርግጥ አስተባበሉ፡፡ በእርሱም ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ዜናዎች (ቅጣት) በእርግጥ ይመጣባቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከበፊታቸው ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንን አላዩምን ለእናንተ ያላስመቸነውን (ለእነርሱ) በምድር ውስጥ አስመቸናቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ዝናምን የተከታተለ ሲኾን ላክን፡፡ ወንዞችንም በሥራቸው እንዲፈሱ አደረግን፡፡ በኃጢአቶቻቸውም አጠፋናቸው፡፡ ከኋላቸውም ሌሎችን የክፍለ ዘመን ሰዎች አስገኘን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibባንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በእርሱም (በሙሐመድ) ላይ መልአክ አይወረድለትም ኖሮአልን» አሉ፡፡ መልአክን ባወረድንም ኖሮ (ባያምኑ በጥፋታቸው) ነገሩ በተፈረደ ነበር፡፡ ከዚያም አይቆዩም ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(መልክተኛውን) መልአክም ባደረግነው ኖሮ ወንድ (በሰው ምስል) ባደረግነው ነበር፡፡ በእነርሱም ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibካንተ በፊትም በመልክተኞች በእርግጥ ተላግጧል፡፡ በእነዚያም ከእነሱ ባላገጡት ላይ በእርሱ ያላግጡ የነበሩት ነገር (ቅጣት) ወረደባቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በምድር ላይ ኺዱ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «የአላህ ነው» በል፡፡ «በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ በትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ እነርሱም አያምኑም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሌሊትና በቀንም ጸጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂ ነው፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ በጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን ከእርሱ ላይ (ቅጣት) የሚመለስለት ሰው (አላህ) በእርግጥ አዘነለት፡፡ ይህም ግልጽ ማግኘት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን አሸናፊ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «አላህ ነው፡፡ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው፡፡ ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስፈራራበት ወደኔ ተወረደ፡፡ ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላችሁን» በላቸው፡፡ «እኔ አልመሰክርም» በላቸው፡፡ «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡ እነዚያ ከእነርሱ ውስጥ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት እነርሱ አያምኑም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው እነሆ በደለኞች አይድኑም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሁላቸውንም የምንሰበስብበትንና ከዚያም ለእነዚያ (ጣዖታትን) ለአጋሩት እነዚያ (ለአላህ) ተጋሪዎች ናቸው ብላችሁ ታስቧቸው የነበራችሁት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው የምንልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም መልሳቸው «በጌታችን በአላህ ይኹንብን አጋሪዎች አልነበርንም» ማለት እንጅ ሌላ አትኾንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበነፍሳቸው ላይ እንዴት እንደ ዋሹና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ከእነሱ እንዴት እንደ ተሰወረ ተመልከት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእነርሱም ወደ አንተ የሚያዳምጥ ሰው አልለ፡፡ በልቦቻቸውም ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን በጆሮዎቻቸውም ላይ ድንቁርናን አደረግን፡፡ ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ በርሷ አያምኑም፡፡ በመጡህም ጊዜ የሚከራከሩህ ሲኾኑ እነዚያ የካዱት «ይህ (ቁርኣን) የቀድሞዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጅ ሌላ አይደለም» ይላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱም (ሰዎችን) ከእርሱ ይከለክላሉ፡፡ ከእርሱም ይርቃሉ፡፡ ነፍሶቻቸውንም እንጂ ሌላን አያጠፉም፤ ግን አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን ከምእምናንም በኾንን ዋ ምኞታችን! ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይልቁንም ከዚህ በፊት ይደብቁት የነበሩት ሁሉ ለእነርሱ ተገለጸ፡፡ (ወደምድረ ዓለም) በተመለሱም ኖሮ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር በተመለሱ ነበር፡፡ እነሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሷም (ሕይወት) «የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም እኛም ተቀስቀቃሾች አይደለንም» አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበጌታቸውም ላይ (ለምርመራ) በተቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር)፡፡ «ይህ እውነት አይደለምን» ይላቸዋል፡፡ «በጌታችን ይኹንብን እውነት ነው» ይላሉ፡፡ «ትክዱት በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉ በእርግጥ ከሰሩ፡፡ ሰዓቲቱም በድንገት በመጣቻቸው ጊዜ እነሱ ኃጢኣቶቻቸውን በጀርባዎቻቸው ላይ የሚሸከሙ ሲኾኑ «በርሷ (በምድረ ዓለም) ባጓደልነው ነገር ላይ ዋ ቁጪታችን» ይላሉ፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ነገር ከፋ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየቅርቢቱም ሕይወት ጨዋታና ላግጣ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ የመጨረሻይቱም አገር (ገነት) ለእነዚያ ለሚጠነቀቁት በጣም በላጭ ናት፡፡ አታውቁምን
  1. Sadiq & Sani Habibእነሆ ያ የሚሉህ ነገር እንደሚያሳዝንህ በእርግጥ እናውቃለን፡፡ እነርሱም (በልቦቻቸው) አያስተባብሉህም፡፡ ግን በዳዮቹ በአላህ አንቀጾች ይክዳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከበፊትህም መልክተኞች በእርግጥ ተስተባበሉ፡፡ በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ፡፡ የአላህንም ንግግሮች ለዋጭ የለም፡፡ ከመልክተኞቹም ወሬ (የምትረጋጋበት) በእርግጥ መጣልህ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ኢስላምን) መተዋቸውም ባንተ ላይ ከባድ ቢኾንብህ በምድር ውስጥ ቀዳዳን ወይም በሰማይ ውስጥ መሰላልን ልትፈልግና በተአምር ልትመጣቸው ብትችል (አድርግ)፡፡ አላህም በሻ ኖሮ በቅኑ መንገድ ላይ በሰበሳባቸው ነበር፡፡ ከተሳሳቱትም ሰዎች በፍጹም አትኹን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጥሪህን የሚቀበሉት እነዚያ የሚሰሙት ብቻ ናቸው፡፡ ሙታንንም አላህ ይቀሰቅሳቸዋል፡፡ ከዚያም ወደርሱ ብቻ ይመለሳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም» አሉ፡፡ «አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከተንቀሳቃሽም በምድር (የሚኼድ)፤ በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም ከዚያም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም በአንቀጾቻችን ያስዋሹ ደንቆሮች ድዳዎችም በጨለማዎች ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ አላህ ማጥመሙን የሚሻውን ሰው ያጠመዋል፡፡ መምራቱን የሚሻውንም ሰው በቀጥተኛ መንገድ ላይ ያደርገዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየአላህ ቅጣት ቢመጣባችሁ ወይም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ብትመጣባችሁ ከአላህ ሌላን ትጠራላችሁን እውነተኞች እንደ ኾናችሁ ንገሩኝ በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአይደለም እርሱን ብቻ ትጠራላችሁ፡፡ ቢሻም ወደርሱ የምትጠሩበትን ነገር ያስወግዳል፡፡ የምታጋሩትንም ነገር ትተዋላችሁ (በላቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከበፊትህም ወደ ነበሩት ሕዝቦች (መልክተኞችን) በእርግጥ ላክን፡፡ እንዲዋደቁም በድህነትና በበሽታ ያዝናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይዋደቁም ኖሯልን ግን ልቦቻቸው ደረቁ፡፡ ይሠሩት የነበሩትንም ነገር ሰይጣን ለነሱ አሳመረላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበርሱም ይገሰጹበት የነበረውን ነገር በተው ጊዜ በእነሱ ላይ የነገርን ሁሉ ደጃፎች ከፈትን (አስመቸናቸው)፡፡ በተሰጡትም ነገር በተደሰቱ ጊዜ በድንገት ያዝናቸው፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ተስፋ ቆራጮች ኾኑ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየእነዚያም የበደሉት ሕዝቦች መጨረሻ ተቆረጠ፡፡ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይገባው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibንገሩኝ አላህ መስሚያችሁንና ማያዎቻችሁን ቢወስድ በልቦቻችሁም ላይ ቢያትም ከአላህ ሌላ እሱን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው በላቸው፡፡ አንቀጾችን እንዴት እንደምናብራራ ከዚያም እነሱ እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ንገሩኝ የአላህ ቅጣት በድንገት ወይም በግልጽ ቢመጣባችሁ አመጠኞች ሕዝቦች እንጅ ሌላ ይጠፋልን» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመልክተኞችንም አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጅ አንልክም፡፡ ያመኑና መልካምን የሠሩ ሰዎችም በእነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም ባንቀጾቻችን ያስዋሹ ያምጹ በነበሩት ምክንያት ቅጣቱ ያገኛቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን አታስተነትኑምን» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳትና አማላጅ የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በርሱ (በቁርኣን) አስፈራራ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያን ጌታቸውን ፊቱን (ውዴታውን) የሚሹ ኾነው በጧትና በማታ የሚጠሩትን አታባር፡፡ ታባርራቸውና ከበደለኞችም ትኾን ዘንድ እነሱን መቆጣጠር ባንተ ላይ ምንም የለብህም፡፡ አንተንም መቆጣጠር በነሱ ላይ ምንም የለባቸውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም «ከመካከላችን አላህ የለገሰላቸው እነዚህ ናቸውን» ይሉ ዘንድ ከፊላቸውን በከፊሉ ሞከርን፡፡ አላህ አመስጋኞቹን ዐዋቂ አይደለምን
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም በተአምራታችን የሚያምኑት (ወደ አንተ) በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ (አላህ) መሓሪ አዛኝ ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም (እውነቱ እንዲገለጽና) የወንጀለኞችም መንገድ ትብራራ ዘንድ አንቀጾችን እንገልጻለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትጠሩዋቸውን ከመገዛት ተከልክያለሁ» በላቸው፡፡ «ዝንባሌያችሁን አልከተልም፡፡ ያን ጊዜ በእርግጥ ተሳሳትኩ፡፡ እኔም ከተመሪዎቹ አይደለሁም» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ ከጌታዬ በኾነች ግልጽ ማስረጃ ላይ ነኝ፡፡ በእርሱም አስተባበላችሁ፡፡ በርሱ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ አይደለም፡፡ ፍርዱ ለአላህ ብቻ ነው፡፡ እውነትን ይፈርዳል፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በእርሱ የምትቻኮሉበት ቅጣት እኔ ዘንድ በኾነ ኖሮ በእኔና በእናንተ መካከል ነገሩ (ቅጣታችሁ) በተፈጸመ ነበር፡፡ አላህም በደለኞችን ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም፡፡ በየብስና በባሕር ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢኾን እንጅ፡፡ ከቅንጣትም በመሬት ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በኾነው መጽሐፍ ውሰጥ (የተመዘገበ) ቢኾን እንጅ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ በሌሊት የሚያስተኛችሁ በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ (በቀን) ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸነፊ ነው፡፡ በናንተም ላይ ጠባቂዎችን (መላእክት) ይልካል፡፡ አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ (የሞት) መልእክተኞቻችን እነርሱ (ትእዛዛትን) የማያጓድሉ ሲኾኑ ይገድሉታል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከየብስና ከባሕር ጨለማዎች በግልጽና በምስጢር የምትጠሩት ስትኾኑ «ከነዚህ ቢያድነን በእርግጥ ከአመስጋኞች እንኾናለን (ስትሉ) የሚያድናችሁ ማነው» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ከሷና ከጭንቅም ሁሉ ያድናችኋል፡፡ ከዚያም እናንተ ታጋራላችሁ በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እርሱ (አላህ) ከበላያችሁ ወይም ከእግሮቻችሁ በታች ቅጣትን በእናንተ ላይ ሊልክ ወይም የተለያዩ ሕዝቦች ስትኾኑ ሊያደባልቃችሁና ከፊላችሁን የከፊሉን ጭካኔ ሊያቀምስ ቻይ ነው» በላቸው፡፡ ያውቁ ዘንድ አንቀጾችን እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱም (በቁርኣን) እሱ እውነት ሲኾን ሕዝቦችህ አስተባበሉ፡፡ በላቸው፡- «በናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibለትንቢት ሁሉ (የሚደርስበት) መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚገቡትን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ሌላ በኾነ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው፡፡ ሰይጣንም (መከልከልህን) ቢያስረሳህ ከትውስታ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእነዚያም በሚጠነቀቁት ላይ ከሒሳባቸው ምንም የለባቸውም፡፡ ግን ይጠነቀቁ ዘንድ መገሰጽ (አለባቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ላግጣ አድርገው የያዙትን ቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው፡፡ በእርሱም (በቁርኣን) ነፍስ በሠራችው ሥራ እንዳትጠፋ አስታውስ፡፡ ለእርሷ ከአላህ ሌላ ረዳትና አማላጅ የላትም፡፡ በመበዢያም ሁሉ ብትበዥ ከርሷ አይወሰድም፡፡ እነዚህ እነዚያ በሠሩት ሥራ የተጠፉት ናቸው፡፡ ለነሱ ይክዱ በነበሩት ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከአላህ ሌላ የማይጠቅመንን እና የማይጎዳንን እንገዛለን አላህም ከመራን ጊዜ በኋላ የኋሊት እንመለሳለን እንደዚያ በምድር ላይ የዋለለ ሲኾን ሰይጣናት እንዳሳሳቱት ለእርሱ ወደኛ ና እያሉ ወደ ቅን መንገድ የሚጠሩ ወዳጆች እንዳሉት (እንደማይከተላቸውም) ሰው እንኾናለን» በላቸው፡፡ «የአላህ መንገድ እርሱ ቀጥተኛው መንገድ ነው፡፡ ለዓለማት ጌታ ልንገዛም ታዘዝን» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሶላትንም በደንቡ ስገዱ ፍሩትም፤ (በማለት ታዘዝን)፡፡ እርሱም ያ ወደርሱ ብቻ የምትሰበሰቡበት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «ጣዖታትን አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ፤ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ (አስታውስ)
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም ኢብራሂምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መለኮት አሳየነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሌሊቱም በእርሱ ላይ ባጨለመ ጊዜ ኮከብን አየ፡፡ «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡ በጠለቀም ጊዜ፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጨረቃንም ወጪ ኾኖ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡ በገባም ጊዜ፡- «ጌታዬ (ቅኑን መንገድ) ባይመራኝ በእርግጥ ከተሳሳቱት ሕዝቦች እኾናለሁ» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibፀሐይንም ጮራዋን ዘርግታ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ነው» አለ፡፡ በገባችም ጊዜ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ» አለ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው (አምላክ) ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» (አለ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወገኖቹም ተከራከሩት፡፡ «በአላህ (አንድነት) በእርግጥ የመራኝ ሲኾን ትከራከሩኛላችሁን በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም፡፡ ግን ጌታዬ ነገርን ቢሻ (ያገኘኛል)፡፡ ጌታዬም ነገሩን ሁሉ ዕውቀቱ ሰፋ፡፡ አትገነዘቡምን» አላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትኾኑ የምታጋሩትን (ጣዖታት) እንዴት እፈራለሁ! የምታውቁም ብትኾኑ ከሁለቱ ክፍሎች በጸጥታ ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው» (አለ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡ እነሱም የተመሩ ናቸው፤
  1. Sadiq & Sani Habibይህችም ማስረጃችን ናት፡፡ ለኢብራሂም በሕዝቦቹ ላይ (አስረጅ እንድትኾን) ሰጠናት፡፡ የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለርሱም ኢስሐቅን (የልጅ ልጁን) ያዕቁብንም ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መራን፡፡ ኑሕንም በፊት መራን፡፡ ከዘሮቹም ዳውድን፣ ሱለይማንንም፣ አዩብንም፣ ዩሱፍንም፣ ሙሳንም፣ ሃሩንንም (መራን)፡፡ እንደዚሁም በጎ ሰሪዎችን እንመነዳለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዘከሪያንም፣ የሕያንም፣ ዒሳንም፣ ኢልያስንም (መራን)፡፡ ሁሉም ከመልካሞቹ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibኢስማዒልንም፣ አልየስዕንም፣ ዩኑስንም፣ ሉጥንም (መራን)፡፡ ሁሉንም በዓለማት ላይ አበለጥናቸውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአባቶቻቸውም፣ ከዘሮቻቸውም፣ ከወንድሞቻቸውም (መራን)፡፡ መረጥናቸውም፤ ወደ ቀጥታውም መንገድ መራናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚህ እነዚያ መጻሕፍትንና ጥበብን፣ ነቢይነትንም የሰጠናቸው ናቸው፡፡ እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርሷ ቢክዱም በእርሷ የማይክዱን ሕዝቦች ለእርሷ በእርግጥ አዘጋጅተናል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚህ (ነቢያት)፤ እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው፡፡ በመንገዳቸውም ተከተል፡፡ «በእርሱ (በቁርአን) ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ እርሱ ለዓለማት ግሣጼ እንጅ ሌላ አይደለም» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም» ባሉም ጊዜ አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ (እንዲህ) በላቸው፡- «ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፡፡ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ፤»
  1. Sadiq & Sani Habib«አላህ (አወረደው)» በላቸው፡፡ ከዚያም በውሸታቸው ውስጥ የሚጫወቱ ሲኾኑ ተዋቸው፡፡ ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ ያንንም በፊቱ የነበረውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው፡፡ የከተሞችን እናት (መካን) እና በዙሪያዋ ያሉትንም ሰዎች ልታስጠነቅቅበት (አወረድነው)፡፡ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የሚያምኑት እነርሱ በሶላታቸው ላይ የሚጠባበቁ ሲኾኑ በርሱ ያምናሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲኾን «ወደኔ ተወረደልኝ» ካለና፡-«አላህም ያወረደውን ብጤ በእርግጥ አወርዳለሁ» ካለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው በደለኞችንም በሞት መከራዎች ውስጥ በኾኑ ጊዜ መላእክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ኾነው « (ለቅጥጥብ) ነፍሶቻችሁን አውጡ፤ በአላህ ላይ እውነት ያልኾነን ነገር ትናገሩ በነበራችሁትና ከአንቀጾቹም ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ» (የሚሏቸው ሲኾኑ) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመጀመሪያም ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ኾናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኋላ የተዋችሁ ስትኾኑ ለየብቻችሁ ኾናችሁ በእርግጥ መጣችሁን እነዚያንም እነሱ በእናንተ ውስጥ (ለአላህ) ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፡፡ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ (ያማልደናል) የምትሉት ጠፋ (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ቅንጣትንና የፍሬን አጥንት ፈልቃቂ ነው፡፡ ሕያውን ከሙት ያወጣል፤ ሙትንም ከሕያው አውጪ ነው፡፡ እርሱ አላህ ነው፤ ታዲያ (ከእምነት) እንዴት ትመለሳላችሁ (ትርቃላችሁ)
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ጎህን (ከሌሊት ጨለማ) ፈልቃቂ ሌሊትንም ማረፊያ ፀሐይንና ጨረቃንም (ለጊዜ) መቁጠሪያ አድራጊ ነው፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው (አላህ) ችሎታ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ከዋክብትን በየብስና በባሕር ጨለማዎች ውስጥ በእርሷ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ ያደረገ ነው፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ፤ ነው፡፡ (በማሕፀን) መርጊያና (በጀርባ) መቀመጫም (አላችሁ)፡፡ ለሚያወቁ ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው፡፡ በርሱም የነገሩን ሁሉ በቃይ አወጣን፡፡ የተደራረበንም ቅንጣት ከርሱ የምናወጣ የኾነን ለምለም (አዝመራ) ከርሱ አወጣን፡፡ ከዘንባባም ከእንቡጧ የተቀራረቡ የኾኑ ዘለላዎች አሉ፡፡ ከወይኖችም፣ ከወይራም፣ ከሩማንም (ቅጠላቸው) ተመሳሳይና (ፍሬያቸው) የማይመሳሰል ሲኾኑ አትክልቶችን (አወጣን)፡፡ ባፈራ ጊዜ ወደ ፍሬውና ወደ መብሰሉ ተመልከቱ፡፡ በእነዚህ ተዓምራት ለሚያምኑ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለአላህም አጋንንትን የፈጠራቸው ሲኾን (በመታዘዝ) ተጋሪዎች አደረጉ፡፡ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችንም ያለ ዕውቀት ለእርሱ ቀጠፉ፡፡ (አላህ) ጥራት የተገባው ከሚሉት ነገር የላቀ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እርሱ) ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ ለእርሱ ሚስት የሌለችው ሲኾን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ ተገዙት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዓይኖች አያገኙትም፤ (አያዩትም)፡፡ እርሱም ዓይኖችን ያያል፡፡ እርሱም ርኅራኄው ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃኖች በእርግጥ መጡላችሁ፡፡ የተመለከተም ሰው (ጥቅሙ) ለነፍሱ ብቻ ነው፡፡ የታወረም ሰው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም» (በላቸው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም « (እንዲገመግሙና ያለፉትን መጻሕፍት) አጥንተሃልም» እንዲሉ ለሚያውቁ ሕዝቦችም (ቁርኣንን) እንድናብራራው አንቀጾችን እንገልጻለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህም በሻ ኖሮ ባላጋሩ ነበር፡፡ በእነሱም ላይ ጠባቂ አላደረግንህም፡፡ አንተም በእነሱ ላይ ኃላፊ አይደለህም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን (ጣዖታትን) አትስደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሰድባሉና፡፡ እንደዚሁ ለሕዝቦች ሁሉ ሥራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ነው፡፡ ይሠሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተዓምርም ብትመጣላቸው በእርሷ በቁርጥ ሊያምኑ ጥብቅ መሐሎቻቸውን በአላህ ማሉ፡፡ «ተዓምራት ሁሉ አላህ ዘንድ ናት» በላቸው፡፡ እርሷ በመጣች ጊዜም አለማመናቸውን (ወይም ማመናቸውን) ምን አሳወቃችሁ
  1. Sadiq & Sani Habibበመጀመሪያም ጊዜ በእርሱ እንዳላመኑ ሁሉ ልቦቻቸውንና ዓይኖቻቸውን እናገላብጣለን፡፡ በጥመታቸውም ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ እንተዋቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛም ወደእነርሱ መላእክትን ባወረድን ሙታንም ባነጋገሩዋቸው ነገሩንም ሁሉ ጭፍራ ጭፍራ አድርገን በእነሱ ላይ በሰበሰብን ኖሮ አላህ ካልሻ በስተቀር የሚያምኑ ባልኾኑ ነበር፡፡ ግን አብዛኞቻቸው (ይህንን) ይስታሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል ልብስብስን ቃል ይጥላሉ፡፡ ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(የሚጥሉትም ሊያታልሉና) የእነዚያም በመጨረሻይቱ ሕይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደእርሱ እንዲያዘነብሉ እንዲወዱትም እነርሱ ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ መጽሐፉን የተብራራ ኾኖ ወደእናንተ ያወረደ ሲኾን «ከአላህ ሌላ ዳኛን እፈልጋለሁን» (በላቸው)፡፡ እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው እርሱ ከጌታህ ዘንድ በእውነት የተወረደ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን ተፈጸመች፡፡ ለቃላቱ ለዋጭ የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጌታህ እርሱ ከመንገዱ የሚሳሳቱትን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአንቀጾቹም አማኞች እንደ ኾናችሁ (ሲታረድ) የአላህ ስም በእርሱ ላይ ከተወሳበት እንስሳ ብሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወደርሱም (መብላት) ከተገደዳችሁበት በስተቀር በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ለእናንተ (አላህ) በእርግጥ የዘረዘረ ሲኾን ከዚያ በእርሱ ላይ የአላህ ስም ከተጠራበት የማትበሉት ለናንተ ምን (ምክንያት) አላችሁ ብዙዎቹም ያለ ዕውቀት በዝንባሌዎቻቸው ያሳስታሉ፡፡ ጌታህ እርሱ ወሰን አላፊዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየኃጢአትንም ግልጹንም ድብቁንም ተውዉ፡፡ እነዚያ ኃጢአትን የሚሠሩ፤ ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው (በክትን በመብላት) ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ፡፡ ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሙት የነበረና ሕያው ያደረግነው ለእርሱም በሰዎች መካከል በእርሱ የሚኼድበትን ብርሃን ያደረግንለት ሰው በጨለማዎች ውስጥ ከርሷ የማይወጣ ኾኖ እንዳልለ ሰው ብጤ ነውን እንደዚሁ ለከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩት ነገር ተጌጠላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም በየከተማይቱ በውስጧ ያሴሩ ዘንድ የተንኮለኞችዋን ታላላቆች አደረግን፡፡ በነፍሶቻቸውም ላይ እንጅ በሌላ ላይ አያሴሩም፤ ግን አያውቁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተዓምርም በመጣቻቸው ጊዜ፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ፡፡ አላህ መልክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ዐዋቂ ነው፡፡ እነዚያን ያመጹትን ሰዎች ይዶልቱ በነበሩት ነገር አላህ ዘንድ ውርደትና ብርቱ ቅጣት ያገኛቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለኢስላም ይከፍትለታል፡፡ ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል፡፡ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህም (ያለህበት) ቀጥተኛ ሲኾን የጌታህ መንገድ ነው፡፡ ለሚያስታውሱ ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘርዝረናል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሰላም አገር አላቸው፡፡ እርሱም (ጌታህ) ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ረዳታቸው ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሁሉንም የሚሰበስብባቸውንም ቀን (አስታውስ)፡፡፡ የአጋንንት ጭፍሮች ሆይ! ከሰዎች (ጭፍራን በማጥመም) በእርግጥ አበዛችሁ (ይባላሉ)፡፡ ከሰዎችም የኾኑት ወዳጆቻቸው፡-«ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ፡፡ ያንንም ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን» ይላሉ፡፡ እሳት አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ መኖሪያችሁ ናት ይላቸዋል፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም የበደለኞችን ከፊል በከፊሉ ላይ ይሠሩት በነበሩት ጥፋት ምክንያት እንሾማለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየጋኔንና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ!፡- «አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን (ቅጣት) ማግኘትን የሚያስፈራሩዋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን» (ይባላሉ)፡፡ «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን፤ (መጥተውልናል)» ይላሉ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታለለቻቸው፡፡ በነፍሶቻቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶችዋ ዘንጊዎች ኾነው ሳሉ በበደል ምክንያት አጥፊ ባለመኾኑ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለሁሉም ከሠሩት ሥራ (የተበላለጡ) ደረጃዎች አልሏቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጌታህም ተብቃቂ የእዝነት ባለቤት ነው፡፡ ቢሻ ያስወግዳችኋል፤ (ያጠፋችኋል)፡፡ ከሌሎች ሕዝቦችም ዘሮች እንዳስገኛችሁ ከበኋላችሁ የሚሻውን ይተካል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየምትቀጠሩት ሁሉ በእርግጥ መጪ ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ሕዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ላይ ሥሩ፤ እኔ (በችሎታዬ ላይ) ሠሪ ነኝና፡፡ ምስጉኒቱም አገር (ገነት) ለእርሱ የምትኾንለት ሰው ማን እንደኾነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡ እነሆ በደለኞች አይድኑም» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለአላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም ድርሻን አደረጉ፡፡ በሐሳባቸውም «ይህ ለአላህ ነው፡፡ ይህም ለተጋሪዎቻችን ነው፡፡» ለተጋሪዎቻቸውም «(ለጣዖታት) የኾነው ነገር ወደ አላህ አይደርስም፡፡ ለአላህም የኾነው እርሱ ወደ ተጋሪዎቻቸው ይደርሳል» አሉ፡፡ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ!
  1. Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም ከአጋሪዎቹ ለብዙዎቹ፤ ተጋሪዎቻቸው ሊያጠፉዋቸው ሃይማኖ ታቸውንም በእነሱ ላይ ሊያቀላቅሉባቸው (ሊያመሳስሉባቸው) ልጆቻቸውን መግደልን አሳመሩላቸው፡፡ አላህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሐሳባቸውም ይህች እርም የኾነች ለማዳ እንስሳና አዝመራ ናት፡፡ የምንሻው ሰው እንጂ ሌላ አይበላትም፡፡ (ይህች) ጀርቦችዋ እርም የተደረገች ለማዳ እንስሳም ናት (አትጫንም)፡፡ ይህች በርሷ ላይ የአላህን ስም (ስትታረድ) የማይጠሩባትም እንስሳ ናት አሉ፡፡ በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ (ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ)፡፡ ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በነዚህም እንስሶች ሆዶች ውስጥ ያለው ለወንዶቻችን በተለይ የተፈቀደ ነው፡፡ በሚስቶቻችንም ላይ እርም የተደረገ ነው፡፡ ሙትም ቢኾን (ሙት ኾኖ ቢወለድ) እነርሱ (ወንዶቹም ሴቶቹም) በርሱ ተጋሪዎች ናቸው» አሉ፡፡ በመቅጠፋቸው አላህ በእርግጥ ይቀጣቸዋል፡፡ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያለ ዕውቀት በሞኝነት ልጆቻቸውን የገደሉና አላህም የሰጣቸውን (ሲሳይ) በአላህ ላይ በመቅጠፍ እርም ያደረጉ በእርግጥ ከሰሩ፡፡ በእርግጥ ተሳሳቱ፡፡ ተመሪዎችም አልነበሩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ዳስ የሚደረግላቸውንና ዳስ የማይደረግላቸውን አትክልቶች የፈጠረ ነው፡፡ ዘምባባንም (የተምርን ዛፍ) አዝመራንም ፍሬዎቹ የተለያዩ ሲኾኑ ወይራንና ሩማንንም (ቅጠላቸው) ተመሳሳይና (ጣዕማቸው) የማይመሳሰል ሲኾኑ (ፈጠረ)፡፡ ባፈራ ጊዜ ከፍሬው ብሉ፡፡ በአጨዳውም ቀን ተገቢውን (ዘካ) ስጡ፡፡ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከለማዳ እንስሳዎችም የሚጫኑትንና የማይጫኑትን (ፈጠረ)፡፡ አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ብሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibስምንትን ዓይነቶች ከበግ ሁለትን (ወንድና ሴትን) ከፍየልም ሁለትን (ፈጠረ)፡፡«ከሁለቱም ክፍሎች አላህ ወንዶቹን እርም አደረገን ወይስ ሴቶቹን ወይስ በርሱ ላይ የሁለቱ ሴቶች ማሕፀኖች ያጠቃለሉትን እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት (በአስረጅ) ንገሩኝ» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከግመልም ሁለትን ከከብትም ሁለትን (ፈጠረ)፡፡«አላህ (ከሁለቱ) ወንዶቹን እርም አደረገን ወይስ ሴቶቹን ወይስ የሁለቱ ሴቶች ማሕፀኖች በእርሱ ላይ ያጠቃለሉትን በእውነቱ አላህ በዚህ ባዘዛችሁ ጊዜ የተጣዳችሁ ነበራችሁን ሰዎችንም ያለ ዕውቀት ሊያጠም በአላህ ላይ ውሸትንም ከቀጠፈ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማን ነው አላህ በደለኞችን ሕዝቦች (ቅኑን መንገድ) አይመራም፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «ወደእኔ በተወረደው ውስጥ በክት ወይም ፈሳሽ ደም ወይም የአሳማ ስጋ እርሱ ርኩስ ነውና ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ አመጸኛና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው (ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም)፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibበእነዚያም አይሁዳውያን በኾኑት ላይ ባለ ጥፍርን ሁሉ እርም አደረግን፡፡ ከከብት፣ ከፍየልና ከበግም ሞራዎቻቸውን ጀርባዎቻቸው ወይም አንጀቶቻቸው የተሸከሙት ወይም በአጥንት የተቀላቀለው (ስብ) ሲቀር በነርሱ ላይ እርም አደረግን፡፡ ይህንን በአመጻቸው ምክንያት ቀጣናቸው፡፡ እኛ እውነተኞች ነን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቢያስተባብሉህም፡- «ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ ብርቱ ቅጣቱም ከአመጸኞች ሕዝቦች ላይ አይመለስም» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያጋሩት «አላህ በሻ ኖሮ እኛም አባቶቻቸንም ባላገራን ነበር፡፡ አንዳችንም ነገር እርም ባላደረግን ነበር ይላሉ፡፡ እንደዚሁ (እነዚህን እንደዋሹ) እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩት ብርቱ ቅጣታችንን እስከቀመሱ ድረስ አስተባባሉ፡፡ ለእኛ ታዘልቁልን ዘንድ (ማጋራታችሁን ለመውደዱ) እናንተ ዘንድ ዕውቀት አለን ጥርጣሬን እንጅ ሌላ አትከተሉም፡፡ እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«የተሟላው ማስረጃ የአላህ ነው፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር» በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እነዚያን አላህ ይህን እርም ማድረጉን የሚመሰክሩትን ምስክሮቻችሁን አምጡ» በላቸው፡፡ ቢመሰክሩም ከእነርሱ ጋር አትመስክር፡፡ የነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን የነዚያንም እነርሱ በጌታቸው (ሌላን) የሚያስተካክሉ ሲኾኑ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑትን ሰዎች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ (በአላህ) ምንንም ነገር አታጋሩ፡፡ ለወላጆችም በጎን ሥራ (ሥሩ)፡፡ ልጆቻችሁንም ከድህንት (ፍራቻ) አትግደሉ፡፡ እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና፡፡ መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለጸውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ፡፡ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጅ አትግደሉ፡፡ ይህን ታውቁ ዘንድ (አላህ) በእርሱ አዘዛችሁ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib«የየቲምንም ገንዘብ ብርታቱን (አካለ መጠን) እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጅ አትቅረቡ፡፡ ስፍርንና ሚዛንንም በትክክሉ ሙሉ፡፡ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም፡፡ በተናገራችሁም ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም እንኳ (እውነትን በመናገር) አስተካክሉ፡፡ በአላህም ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ እነሆ ትገሰጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habib«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም ለሙሳ በዚያ መልካም በሠራው ላይ (ጸጋችንን) ለማሟላት ነገርንም ሁሉ ለመዘርዘር መጽሐፉን (ለእስራኤል ልጆች) መሪና እዝነት ይኾን ዘንድ ሰጠነው፡፡ እነርሱ በጌታቸው መገናኘት ሊያምኑ ይከጀላልና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህም ያወረድነው የኾነ የተባረከ መጽሐፍ ነው፡፡ ተከተሉትም፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ (ከክህደት) ተጠንቀቁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«(ያወረድነውም) መጽሐፍ የተወረደው ከፊታችን በሁለቱ ጭፍሮች ላይ ብቻ ነው፡፡ እኛም ከንባባቸው ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወይም «እኛ መጽሐፍ በእኛ ላይ በተወረደ ኖሮ ከእነሱ ይበልጥ የተመራን እንኾን ነበር» እንዳትሉ ነው፡፡ ስለዚህ ከጌታችሁ ግልጽ ማስረጃ፣ መምሪያም፣ እዝነትም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ በአላህም አንቀጾች ካስተባበለና ከእርሷም ከዞረ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነዚያን አንቀጾቻችንን የሚተውትን ይተውት በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እንቀጣቸዋለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመላእክት ልትመጣላቸው ወይም ጌታህ (ቅጣቱ) ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ይጠባበቃሉን ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ በሚመጣ ቀን ከዚህ በፊት አማኝ ያልኾነችን ነፍስ እምነትዋ ወይም በእምነትዋ (ጊዜ) በጎ ያልሠራችን (ነፍስ ጸጸትዋ) አይጠቅማትም፡፡ ተጠባበቁ እኛ ተጠባባቂዎች ነንና በላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከእነሱ አይደለህም፡፡ ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ ይነገራቸዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበላቸው «እርሱ (አላህ) የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ (ክፉን) አትሠራም፡፡ ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላይቱን ሸክም (ኃጢአት) አትሸከምም፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው፡፡ ወዲያውም በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነገራችኋል፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ በምድር ምትኮች ያደረጋችሁ በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ ከፊላችሁን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ነው፡፡ ጌታህ ቅጣቱ ፈጣን ነው፡፡ እርሱም እጅግ መሓሪ ሩኅሩኅ ነው፡፡