١
- Sadiq & Sani Habibአ.ለ.መ.ሰ (አሊፍ፤ ላም ፤ሚም፤ ሷድ)፡፡
٢
- Sadiq & Sani Habib(ይህ) ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር፡፡ (የተወረደውም) በእርሱ ልታስፈራራበትና ለምእምናን መገሠጫ እንዲኾን ነው፡፡
٣
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁ ወደእናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡
٤
- Sadiq & Sani Habibከከተማም ልናጠፋት የሻነው ወዲያውም ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ናቸው፡፡
٥
- Sadiq & Sani Habibቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ «ጸሎታቸው እኛ በደለኞች ነበርን» ከማለት በቀር ሌላ አልነበረም፡፡
٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያንም ወደነሱ የተላከባቸውን (ሕዝቦች) በእርግጥ መልክተኞቹንም እንጠይቃለን፡፡
٧
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱም ላይ (የነበሩበትን ሁሉ) ከዕውቀት ጋር በእርግጥ እንተርክላቸዋለን፡፡ የራቅንም አልነበርንም፡፡
٨
- Sadiq & Sani Habibትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው፡፡ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ ናቸው፡፡
٩
- Sadiq & Sani Habibሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ ተአምራቶቻችንን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡
١٠
- Sadiq & Sani Habibበምድርም ላይ በእርግጥ አስመቸናችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ለናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ፤ ምስጋናችሁ በጣም ጥቂት ነው፡፡
١١
- Sadiq & Sani Habibበእርግጥም ፈጠርናችሁ፡፡ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክቶች «ለአዳም ስገዱ» አልን፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡
١٢
- Sadiq & Sani Habib(አላህ) «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው፡፡ «እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ፡፡
١٣
- Sadiq & Sani Habibከእርሷ ውረድ፤ በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና፡፡ ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው፡፡
١٤
- Sadiq & Sani Habib«እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ» አለ፡፡
١٥
- Sadiq & Sani Habib፡-አንተ ከሚቆዩት ነህ አለው፡፡
١٦
- Sadiq & Sani Habib«ስለአጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ» አለ፡፡
١٧
- Sadiq & Sani Habib«ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፡፡ አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም» (አለ)፡፡
١٨
- Sadiq & Sani Habib«የተጠላህ ብራሪ ስትኾን ከእርሷ ውጣ፡፡ ከእነርሱ የተከተለህ ከእናንተ ከመላችሁም ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው፡፡
١٩
- Sadiq & Sani Habib«አዳም ሆይ! አንተም ሚስትህም በገነት ተቀመጡ፡፡ ከሻችሁትም ስፍራ ብሉ፡፡ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፡፡ (ራሳቸውን) ከሚበድሉት ትኾናላችሁና» (አላቸው)፡፡
٢٠
- Sadiq & Sani Habibሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡ «ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም» አላቸው፡፡
٢١
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው፡፡
٢٢
- Sadiq & Sani Habibበማታለልም አዋረዳቸው፡፡ ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ኀፍረተ ገላቸው ለሁለቱም ተገለጠችላቸው፡፡ ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ ጀመር፡፡ ጌታቸውም «ከዚህ ዛፍ አልከለከልኋችሁምን ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁምን» ሲል ጠራቸው፡፡
٢٣
- Sadiq & Sani Habib«ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡
٢٤
- Sadiq & Sani Habib(አላህ) « ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፡፡ ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ» አላቸው፡፡
٢٥
- Sadiq & Sani Habib«በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ፡፡ ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ» አላቸው፡፡
٢٦
- Sadiq & Sani Habibየአዳም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፡፡ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፡፡ ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)፡፡
٢٧
- Sadiq & Sani Habibየአዳም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባትና እናታችሁን ኀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ የገፈፋቸው ሲኾን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተን አይሞክራችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ያዩዋችኋልና፡፡ እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል፡፡
٢٨
- Sadiq & Sani Habibመጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን አላህም በእርሷ አዞናል ይላሉ፡፡ «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን» በላቸው፡፡
٢٩
- Sadiq & Sani Habibጌታዬ በማስተካከል አዘዘ፡፡ በየመስጊዱም ዘንድ ፊቶቻችሁን (እርሱን ለመገዛት) አስተካክሉ፡፡ ሃይማኖትንም ለእርሱ ፍጹም አድርጋችሁ ተገዙት፡፡ እንደጀመራችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡
٣٠
- Sadiq & Sani Habibከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና፡፡ እነርሱም (ቅኑን መንገድ) የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡
۞٣١
- Sadiq & Sani Habibየአዳም ልጆች ሆይ! (ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡ ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና፡፡
٣٢
- Sadiq & Sani Habib«የአላህን ጌጥ ያችን ለባሮቹ የፈጠራትን ከሲሳይም ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው» በላቸው፡፡ «እርሷ በትንሣኤ ቀን ለእነዚያ ላመኑት ብቻ ስትኾን በቅርቢቱ ሕይወት ተገቢያቸው ናት» በላቸው፡፡ እንደዚሁ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡
٣٣
- Sadiq & Sani Habib«ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡
٣٤
- Sadiq & Sani Habibለሕዝብም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው፡፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፡፡ (ከጊዜያቱ) አይቀደሙምም፡፡
٣٥
- Sadiq & Sani Habibየአዳም ልጆች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ በናንተ ላይ አንቀጾቼን የሚያነቡ መልከተኞች ቢመጧችሁ ከእናንተ ክሕደትን የተጠነቀቁና መልካምንም የሠሩ በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነሱም አያዝኑም፡፡
٣٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
٣٧
- Sadiq & Sani Habibበአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስዋሸ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነዚያ (ከተጻፈላቸው) ከመጽሐፉ ውስጥ ሲኾን ዕድላቸው ያገኛቸዋል፡፡ (የሞት) መልክተኞቻችንም የሚገድሏቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሃዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡
٣٨
- Sadiq & Sani Habib«ከጋኔንም ከሰውም ከእናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ሕዝቦች ጋር ኾናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ» ይላቸዋል፡፡ አንዲቱ ሕዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር (ያሳሳተቻትን) ብጤዋን ትረግማለች፡፡ መላውም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙም ጊዜ የኋለኛይቱ ለመጀመሪያይቱ (ተከታዮች ለአስከታዮች) «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን፡፡ ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው» ትላለች፡፡ (አላህም)፡- ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም ይላቸዋል፡፡
٣٩
- Sadiq & Sani Habib«መጀመሪያይቱም ለኋለኛይቱ ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም» ትላለች፡፡ «ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ» (ይላቸዋል)፡፡
٤٠
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ገነትን አይገቡም፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡
٤١
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱ ከገሀነም እሳት (በሥራቸው) ምንጣፍ ከበላያቸውም (የእሳት) መሸፈኛዎች አሏቸው፡፡ እንደዚሁም በደለኞችን እንቀጣለን፡፡
٤٢
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድምና፤ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
٤٣
- Sadiq & Sani Habibበደረቶቻቸው ውስጥ ያለውንም ጥላቻ እናስወግዳለን፡፡ ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ፡፡ «ለዚያም ወደዚህ (ላደረሰን ሥራ) ለመራን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡ አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር፡፡ የጌታችን መልክተኞች በእውነት ላይ ሲኾኑ በእርግጥ መጥተውልናል» ይላሉ፡፡ ይህች ገነት ትሠሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ፡፡
٤٤
- Sadiq & Sani Habibየገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል፡፡
٤٥
- Sadiq & Sani Habib(በደለኞች) እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚከለክሉ፣ (የአላህም መንገድ) እንድትጣመምም የሚፈልጉዋት፣ እነርሱም በመጨረሻዋ ዓለም ከሓዲዎች የኾኑ ናቸው፡፡
٤٦
- Sadiq & Sani Habibበመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ፡፡ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አልሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም (የአዕራፍ ሰዎች) የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም፡፡
۞٤٧
- Sadiq & Sani Habibዓይኖቻቸውም ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! ከበደለኞች ጋር አታድርገን» ይላሉ፡፡
٤٨
- Sadiq & Sani Habibየአዕራፍም ሰዎች በምልክታቸው የሚያውቁዋቸውን (ታላላቅ) ሰዎች ይጣራሉ፡፡ «ስብስባችሁና በብዛታችሁ የምትኮሩ መኾናችሁም ከእናንተ ምንም አልጠቀማችሁ» ይሏቸዋል፡፡
٤٩
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ አላህ በችሮታው አያገኛቸውም ብላችሁ የማላችሁት (ደካሞች) እነዚህ ናቸውን «ገነትን ግቡ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም አታዝኑም» (ተባሉ ይሏቸዋል)፡፡
٥٠
- Sadiq & Sani Habibየእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች «በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ (ጣሉልን)» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል፡፡
٥١
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙ የቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸው ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን እንደረሱ በተአምራታችንም ይክዱ እንደነበሩ ዛሬ እንረሳቸዋልን፡፡
٥٢
- Sadiq & Sani Habibከዕውቀት ጋርም የዘረዘርነው የኾነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መምሪያና እዝነት ሲኾን በእርግጥ አመጣንላቸው፡፡
٥٣
- Sadiq & Sani Habib(የዛቻውን) ፍጻሜውን እንጂ ሌላ አይጠባበቁም፡፡ ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልክተኞች በእርግጥ በውነት መጥተዋል፡፡ ለእኛ ያማልዱም ዘንድ አማላጆች አልሉን ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላን ሥራ እንሠራ ዘንድ (ወደ ምድረ ዓለም) እንመለሳለን» ይላሉ፡፡ ነፍሶቻቸውን በእርግጥ አከሰሩ፡፡ ይቀጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ጠፋቸው፡፡
٥٤
- Sadiq & Sani Habibጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም (ስልጣኑ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡
٥٥
- Sadiq & Sani Habibጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት፡፡ እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና፡፡
٥٦
- Sadiq & Sani Habibበምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ፈርታችሁና ከጅላችሁም ተገዙት፡፡ የአላህ ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና፡፡
٥٧
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ያ ነፋሶችን ከችሮታው (ከዝናም) በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው፡፡ ከባዳዎችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ኾነ አገር እንነዳዋለን፡፡ በእርሱም ውሃን እናወርዳለን፡፡ ከፍሬዎችም ሁሉ በእርሱ እናወጣለን፡፡ እንደዚሁ ትገነዘቡ ዘንድ ሙታንን (ከመቃብር) እናወጣለን፡፡
٥٨
- Sadiq & Sani Habibመልካሙም አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ (ያማረ ኾኖ) ይወጣል፡፡ ያም መጥፎ የኾነው (በቃዩ) ደካማ ኾኖ እንጂ አይወጣም፡፡ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ሕዝቦች ታምራትን እናብራራለን፡፡
٥٩
- Sadiq & Sani Habibኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡»
٦٠
- Sadiq & Sani Habibከሕዝቦቹ (የካዱት) መሪዎቹ፡- «እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾነህ በእርግጥ እናይሃለን» አሉት፡፡
٦١
- Sadiq & Sani Habibአላቸው «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ፡፡»
٦٢
- Sadiq & Sani Habib«የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ፡፡»
٦٣
- Sadiq & Sani Habib«አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን» (አላቸው)፡፡
٦٤
- Sadiq & Sani Habibወዲያውም አስተባበሉት፡፡ እርሱንና እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያሉትን (አማኞች) በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው፡፡ እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን፡፡ እነርሱ (ልበ) ዕውራን ሕዝቦች ነበሩና፡፡
۞٦٥
- Sadiq & Sani Habibወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ (የአላህን ቅጣት) አትፈሩምን» አላቸው፡፡
٦٦
- Sadiq & Sani Habibከሕዝቦቹ እነዚያ የካዱት መሪዎች «እኛ በሞኝነት ላይ ኾነህ በእርግጥ እናይሃለን፡፡ እኛም ከውሸተኞቹ ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን» አሉት፡፡
٦٧
- Sadiq & Sani Habib(እርሱም) አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ ነኝ፡፡»
٦٨
- Sadiq & Sani Habib«የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ እኔም ለእናንተ ታማኝ መካሪ ነኝ፡፡»
٦٩
- Sadiq & Sani Habib«ከጌታችሁ የኾነ ግሣጼ ከእናንተው ውስጥ ባንድ ሰው ላይ ያስጠነቀቃችሁ ዘንድ ቢመጣባችሁ ትደነቃላችሁን ከኑሕም ሕዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጠረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ የሻችሁትንም ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡»
٧٠
- Sadiq & Sani Habib«አላህን ብቻውን እንድንገዛ አባቶቻችንም ይገዙት የነበረውን (አማልክት) እንድንተው መጣህብን ከውነተኞች ከኾንክ የምታስፈራብንን (ቅጣት) አምጣብን» አሉ፡፡
٧١
- Sadiq & Sani Habib«ከጌታችሁ የኾነ ቅጣትና ቁጣ በእናንተ ላይ በእውነት ተረጋገጠ፡፡ እናንተና አባቶቻችሁም (አማልክት ብላችሁ) በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእርሷ ምንም ማስረጃ ያላወረደባት ስትኾን ትከራከሩኛላችሁን ተጠባባቁም እኔ ከእናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና» አለ፡፡
٧٢
- Sadiq & Sani Habibእርሱንና እነዚያንም አብረውት የነበሩትን ከእኛ በኾነው ችሮታ (ከቅጣት) አዳንናቸው፡፡ የእነዚያንም በተአምራታችን ያስተባበሉትንና አማኞች ያልነበሩትን መሠረት ቆረጥን፡፡
٧٣
- Sadiq & Sani Habibወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፡፡ አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ (እውነተኛ ለመኾኔ) ከጌታችሁ የኾነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች፡፡ ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትኾን የአላህ ግመል ናትና ተዋት፡፡ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፤ (ትጠጣም)፡፡ በክፉ አትንኳትም፡፡ አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና፡፡»
٧٤
- Sadiq & Sani Habib«ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ፡፡ ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ፡፡ ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ፡፡»
٧٥
- Sadiq & Sani Habibከወገኖቹ እነዚያ የኮሩት መሪዎች ለእነዚያ ለተሸነፉት ከነሱ ላመኑት፡- «ሷሊህ ከጌታው መላኩን ታውቃላችሁን» አሏቸው፡፡ « (አዎን)፡- እኛ እርሱ በተላከበት ነገር አማኞች ነን» አሉ፡፡
٧٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ የኮሩት፡- «እኛ በዚያ እናንተ በርሱ ባመናችሁበት ከሓዲዎች ነን» አሉ፡፡
٧٧
- Sadiq & Sani Habibወዲያውም ግመሊቱን ወጓት፡፡ ከጌታቸውም ትዕዛዝ ወጡ፡፡ አሉም፡- «ሷሊህ ሆይ! ከመልክተኞቹ እንደኾንክ የምታስፈራራብንን (ቅጣት) አምጣብን፡፡»
٧٨
- Sadiq & Sani Habibወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡
٧٩
- Sadiq & Sani Habib(ሷሊህ) ከእነርሱም ዞረ፡፡ (እንዲህም) አለ «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልክት በእርግጥ አደረስኩላችሁ፡፡ ለእናንተም መከርኳችሁ፡፡ ግን መካሪዎችን አትወዱም፡፡»
٨٠
- Sadiq & Sani Habibሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «አስቀያሚን ሥራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡»
٨١
- Sadiq & Sani Habib«እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁ፡፡ በእውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ፡፡»
٨٢
- Sadiq & Sani Habibየሕዝቦቹም መልስ « (ሎጥንና ተከታዮቹን) ከከተማችሁ አውጧቸው፡፡ እነሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡
٨٣
- Sadiq & Sani Habibእርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ (ለጥፋት) ከቀሩት ኾነች፡፡
٨٤
- Sadiq & Sani Habibበእነሱም ላይ (የእሳት) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
٨٥
- Sadiq & Sani Habibወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ በእርግጥ መጥታላችኋለች፡፡ ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ፡፡ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡»
٨٦
- Sadiq & Sani Habib« (ሰዎችን) የምታስፈራሩና ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱ መጥመሟንም የምትፈልጉዋት ኾናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ፡፡ ጥቂቶችም በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ፡፡»
٨٧
- Sadiq & Sani Habib«ከእናንተም በዚያ እኔ በእርሱ በተላክሁበት ያመኑ ጭፍሮችና ያላመኑ ጭፍሮችም ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሱ፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡»
۞٨٨
- Sadiq & Sani Habibከሕዝቦቹ እነዚያ የኮሩት መሪዎች፡- «ሹዓይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ከአንተጋር ያመኑትን ከከተማችን በእርግጥ እናስወጣችኋለን፡፡ ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ አሉ፡፡ የጠላንም ብንኾን» አላቸው፡፡
٨٩
- Sadiq & Sani Habib«አላህ ከእርሷ ከአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን፡፡ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለእኛ ወደእርሷ ልንመለስ አይገባንም፡፡ ጌታችን ዕውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ፡፡ በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ፡፡ አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ» (አለ)
٩٠
- Sadiq & Sani Habibከወገኖቹም እነዚያ የካዱት መሪዎች «ሹዓይብን ብትከተሉ እናንተ ያን ጊዜ ከሳሪዎች ናችሁ» አሉ፡፡
٩١
- Sadiq & Sani Habibወዲያውም የምድር መንቀጥቀጥ (ጩኸትም) ያዘቻቸው፡፡ በከተማቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡
٩٢
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ሹዓይብን ያሰተባበሉት በእርሷ እንዳልነበሩባት ኾኑ፡፡ እነዚ ሹዓይብን ያስተባበሉት እነርሱ ከሳሪዎች ኾኑ፡፡
٩٣
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱም (ትቷቸው) ዞረ፡- «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ፡፡ ለእናንተም መከርኩ፡፡ ታዲያ በከሓዲዎች ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ» አለም፡፡
٩٤
- Sadiq & Sani Habibበከተማ አንድንም ነቢይ አልላክንም ሰዎችዋን ይዋደቁ ዘንድ በድህነትና በጉዳት የያዝናቸው ብንኾን እንጂ፡፡
٩٥
- Sadiq & Sani Habibከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡
٩٦
- Sadiq & Sani Habibየከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው፡፡
٩٧
- Sadiq & Sani Habibየከተማዋ ሰዎችም እነሱ የተኙ ኾነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን
٩٨
- Sadiq & Sani Habibየከተማዋ ሰዎችም እነሱ የሚጫወቱ ኾነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋድ ሊመጣባቸው አይፈሩምን
٩٩
- Sadiq & Sani Habibየአላህንም ማዘናጋት አይፈሩምን የአላህንም ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡
١٠٠
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያ ምድርን ከባለቤቶችዋ (ጥፋት) በኋላ ለሚወርሱት ብንሻ ኖሮ በኃጢኣቶቻቸው የምንቀጣቸው መኾናችን አልተገለጸላቸውምን በልቦቻቸውም ላይ እናትማለን፡፡ ስለዚህ እነርሱ አይሰሙም፡፡
١٠١
- Sadiq & Sani Habibእነዚህ ከተሞች (ከኑሕ እስከ ሹዓይብ ሰዎች የተነገሩት) ከወሬዎቻቸው ባንተ ላይ እንተርካለን፡፡ መልክተኞቻቸውም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጥተዋቸዋል፡፡ ከመምጣታቸው በፊት ባስተባበሉትም ነገር የሚያምኑ አልኾኑም፡፡ እንደዚሁ አላህ በከሓዲያን ልቦች ላይ ያትማል፡፡
١٠٢
- Sadiq & Sani Habibለብዙዎቻቸውም በቃል ኪዳናቸው መሙላትን አላገኘንም፡፡ አብዛኞቻቸውንም በእርግጥ አመጸኞች ኾነው አገኘናቸው፡፡
١٠٣
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ከበኋላቸው ሙሳን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቶቹ በተዓምራታችን ላክነው፡፡ በእርሷም ካዱ፡፡ ያጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
١٠٤
- Sadiq & Sani Habibሙሳም አለ፡- «ፈርዖን ሆይ! እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ መልክተኛ ነኝ፡፡»
١٠٥
- Sadiq & Sani Habib«»በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፡፡ ከጌታችሁ በተዓምር በእርግጥ መጣኋችሁ፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከእኔ ጋር ልቀቅ፡፡
١٠٦
- Sadiq & Sani Habib(ፈርዖንም «በተዓምር የመጣህ እንደኾንክ ከውነተኞቹ ከኾንክ እርሷን አምጣት» አለው፡፡
١٠٧
- Sadiq & Sani Habibበትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች፡፡
١٠٨
- Sadiq & Sani Habibእጁንም አወጣ፡፡ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ኾነች፡፡
١٠٩
- Sadiq & Sani Habibከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹ፡- «ይህ በእርግጥ ዐዋቂ ድግምተኛ ነው» አሉ፡፡
١١٠
- Sadiq & Sani Habib«ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል» (አሉ)፡፡ «ታዲያ ምን ታዛላችሁ» (አለ)
١١١
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) አሉ «እርሱንና ወንድሙን አቆይ፡፡ ወደ ከተሞቹም ሁሉ ሰብሳቢዎችን (ዘበኞች) ላክ፡፡»
١١٢
- Sadiq & Sani Habib«ዐዋቂ ድግምተኛ የኾነን ሁሉ ያመጡልሃልና፡፡»
١١٣
- Sadiq & Sani Habibድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡ፡፡ «እኛ አሸናፊዎች ብንኾን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን» አሉ፡፡
١١٤
- Sadiq & Sani Habib«አዎን እናንተም በእርግጥ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡
١١٥
- Sadiq & Sani Habib«ሙሳ ሆይ (በትርህን) ወይም (በፊት) ትጥላለህ ወይም እኛ ጣዮች እንኾናለን» አሉት፡፡
١١٦
- Sadiq & Sani Habib«ጣሉ» አላቸው፡፡ (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ ትልቅ ድግምትንም አመጡ፡፡
۞١١٧
- Sadiq & Sani Habibወደ ሙሳም፡- «በትርህን ጣል» ስንል ላክን፡፡ (ጣላትም) ወዲያውኑም የሚቀጣጥፉትን (ማታለያ) ትውጣለች፡፡
١١٨
- Sadiq & Sani Habibእውነቱም ተገለጸ፡፡ ይሠሩት የነበሩትም (ድግምት) ተበላሸ፡፡
١١٩
- Sadiq & Sani Habibእዚያ ዘንድ ተሸነፉም፡፡ ወራዶችም ኾነው ተመለሱ፡፡
١٢٠
- Sadiq & Sani Habibድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡
١٢١
- Sadiq & Sani Habibአሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡»
١٢٢
- Sadiq & Sani Habib«በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡»
١٢٣
- Sadiq & Sani Habibፈርዖን አለ፡- «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰዎቿን ከእርሷ ለማውጣት በእርግጥ የተስማማችሁበት ተንኮል ነው፡፡ ወደፊትም (የሚደርስባችሁን) ታውቃላችሁ፡፡»
١٢٤
- Sadiq & Sani Habib«እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ፡፡ ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ እሰቅላችኋለሁ፡፡»
١٢٥
- Sadiq & Sani Habibአሉ፡- «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡»
١٢٦
- Sadiq & Sani Habib«የጌታችንም ተዓምራቶች በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም፡፡ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፡፡ ሙስሊሞች ኾነን ግደለን፡፡»
١٢٧
- Sadiq & Sani Habibከፈርዖንም ሰዎች ታላላቆቹ (ለፈርዖን) «ሙሳንና ሰዎቹን በምድር ላይ እንዲያበላሹና (ሙሳም) አንተንና አማልክቶችህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን» አሉ፡፡ «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን፡፡ ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን፡፡ እኛም ከበላያቸው ነን፡፡ አሸናፊዎች (ነን)» አለ፡፡
١٢٨
- Sadiq & Sani Habibሙሳ ለሰዎቹ፡- «ለአላህ ተገዙ ታገሱም፡፡ ምድር ለአላህ ናትና፡፡ ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል፡፡ ምሰጉንዋም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት» አላቸው፡፡
١٢٩
- Sadiq & Sani Habib«ከመምጣትህም በፊት ከመጣኽልንም በኋላ ተሰቃየን» አሉት፡፡ «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋ እንዴት እንደምትሠሩም ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይሻል» አላቸው፡፡
١٣٠
- Sadiq & Sani Habibየፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅ ዓመታትና ከፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ ያዝናቸው፡፡
١٣١
- Sadiq & Sani Habibደጊቱም ነገር (ምቾት) በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ (ተገቢ) ናት» ይላሉ፡፡ ክፉትም ብታገኛቸው በሙሳና አብረውት ባሉት ገደቢስነት ያመካኛሉ፡፡ ንቁ! ገደቢስነታቸው አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡
١٣٢
- Sadiq & Sani Habib(ለሙሳም) «በማንኛይቱም ተዓምር በእርሷ ልትደግምብን ብትመጣብን እኛ ለአንተ የምናምንልህ አይደለንም» አሉ፡፡
١٣٣
- Sadiq & Sani Habibወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡
١٣٤
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱም ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸው ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ ነገር ለእኛ ለምንልን፡፡ ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ለአንተ በእርግጥ እናምንልሃለን፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከአንተ ጋር በእርግጥ እንለቃለን፤» አሉ፡፡
١٣٥
- Sadiq & Sani Habibእነርሱም ደራሾቹ እኾኑበት ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን ያፈርሳሉ፡፡
١٣٦
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ በተዓምራታችን ስለአስተባበሉም ከእርሷ ዘንጊዎች ስለኾኑም፤ ከእነሱ ተበቀልን፡፡ በባሕርም ውስጥ አሰጠምናቸው፡፡
١٣٧
- Sadiq & Sani Habibእነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው፡፡ የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች፡፡ ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን፡፡
١٣٨
- Sadiq & Sani Habibየእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሻገርናቸው፡፡ ለእነርሱ በኾኑ ጣዖታት (መገዛት) ላይ በሚዘወትሩ ሕዝቦች ላይ አለፉም፡፡ «ሙሳ ሆይ፡- ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን» አሉት፡፡ «እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡
١٣٩
- Sadiq & Sani Habib«እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው፡፡ ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው» (አላቸው)፤
١٤٠
- Sadiq & Sani Habib«ከአላህ ሌላ እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲኾን (የምትገዙት) አምላክን እፈልግላችኋለሁን» አለ፡፡
١٤١
- Sadiq & Sani Habibከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሱዋችሁ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተዉ ሲኾኑ ባዳናችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ በዚህም ውስጥ ከጌታችሁ ዘንድ የኾነ ከባድ ፈተና አለበት፡፡
۞١٤٢
- Sadiq & Sani Habibሙሳንም ሰላሳን ሌሊት (ሊጾምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው፡፡ በዐስርም (ሌሊት) ሞላናት፡፡ የጌታውም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲኾን ተፈጸመ፡፡ ሙሳም ለወንድሙ ሃሩን «በሕዝቦቼ ላይ ተተካኝ፡፡ አሳምርም የአጥፊዎችንም መንገድ አትከተል» አለው፡፡
١٤٣
- Sadiq & Sani Habibሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ (አላህም)፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም (በወቅቱ) የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡
١٤٤
- Sadiq & Sani Habib(አላህም) አለው፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ፡፡ የሰጡህንም ያዝ፡፡ ከአመስጋኞቹም ኹን፡፡»
١٤٥
- Sadiq & Sani Habibለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት፡፡ (አልንም) በብርታትም ያዛት፡፡ ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው፡፡ የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ፡፡
١٤٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያን ያለአግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀጾቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ፡፡ ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ በርሷ አያምኑም፡፡ ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም፡፡ ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል፡፡ ይህ እነርሱ በአንቀጾቻችን ስለአስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለኾኑ ነው፡፡
١٤٧
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም በአንቀጾቻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ ይሠሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን
١٤٨
- Sadiq & Sani Habibየሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ (መኼድ) በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለርሱ ማግሳት ያለውን (አምላክ አድርገው) ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን (አምላክ አድርገው) ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡
١٤٩
- Sadiq & Sani Habibበተጸጸቱና እነሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መኾናቸውን ባዩ ጊዜ፡- «ጌታችን ባያዝንልንና ባይምረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡
١٥٠
- Sadiq & Sani Habibሙሳም እየተቆጣና እያዘነ ወደ ሕዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «ከእኔ በኋላ በእኔ ላይ የተካችሁት ነገር ከፋ! የጌታችሁን ትእዛዝ ተቻኮላችሁን» አላቸው፡፡ ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው፡፡ የወንድሙንም ራስ (ጸጉር) ወደርሱ የሚጎትተው ሲኾን ያዘ፡፡ (ወንድሙም)፡- «የናቴ ልጅ ሆይ! ሕዝቦቹ ናቁኝ፡፡ ሊገድሉኝም ተቃራቡ፡፡ ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ፡፡ ከአመጸኞች ሕዝቦችም ጋር አታድርገኝ» አለው፡፡
١٥١
- Sadiq & Sani Habib(ሙሳም)፡- «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወንድሜም ማር፡፡ በእዝነትህም ውስጥ አግባን፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ፡፡
١٥٢
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ወይፈኑን (አምላክ አድርገው) የያዙ ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ፤ በቅርቢቱም ሕይወት ውርደት በእርግጥ ያገኛቸዋል፡፡ እንዲሁም ቀጣፊዎችን እንቀጣለን፡፡
١٥٣
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
١٥٤
- Sadiq & Sani Habibከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ፡፡
١٥٥
- Sadiq & Sani Habibሙሳም ከሕዝቦቹ ውስጥ ለቀጠሮዋችን ሰባን ሰዎች መረጠ፡፡ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በያዘቻቸውም ጊዜ ሙሳ አለ «ጌታዬ ሆይ! በሻህ ኖሮ ከአሁን በፊት በአጠፋሃቸው ነበር፡፡ እኔንም (ባጠፋኸኝ ነበር)፡፡ ከእኛ ቂሎቹ በሠሩት ነገር ታጠፋናለህን እርሷ (ፈተናይቱ) ያንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ፡፡ የምትሻውንም ታቀናለህ፡፡ አንተ ረዳታችን ነህና ለእኛ ምሕረት አድርግልን፡፡ እዘንልንም፡፡ አንተም ከመሓሪዎች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»
۞١٥٦
- Sadiq & Sani Habib«ለእኛም በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም (መልካሟን) ጻፍልን፡፡ እኛ ወደ አንተ ተመለስን፡፡» (ሲል ሙሳ ጸለየ፤ አላህም) አለ፡- «ቅጣቴ በእርሱ የምሻውን ሰው እቀጣበታለሁ፡፡ ችሮታየም ነገሩን ሁሉ ሰፋች፡፡ ለእነዚያም ለሚጠነቀቁ፣ ዘካንም ለሚሰጡ፣ ለእነዚያም እነሱ በአንቀጾቻችን ለሚያምኑ በእርግጥ» እጽፋታለሁ፡፡
١٥٧
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)፡፡ በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፡፡ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፡፡ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፡፡ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል፡፡ ከእነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል፡፡ እነዚያም በእርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንንም ከእርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚያድኑ ናቸው፡፡
١٥٨
- Sadiq & Sani Habib(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ (እርሱም) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡»
١٥٩
- Sadiq & Sani Habibከሙሳም ሕዝቦች በእውነት የሚመሩት በእርሱም (ፍርድን) የሚያስተካክሉ ጭፍሮች አሉ፡፡
١٦٠
- Sadiq & Sani Habibዐሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ (መታውም) ከእርሱ ዐሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ፡፡ ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ በእነሱም ላይ ደመናን አጠለልን፡፡ በእነሱም ላይ መናንና ድርጭትን አወረድን፡፡ «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ» (አልን፤ ጸጋችንን በመካዳቸው) አልበደሉንምም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡
١٦١
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱም በተባሉ ጊዜ (አስታውስ) «በዚህች ከተማ ተቀመጡ፡፡ ከእርሷም በሻችሁት ስፍራ ብሉ፡፡ (የምንፈልገው) የኃጢኣታችንን መርገፍ ነው በሉም፡፡ የከተማይቱንም በር አጎንብሳችሁ ግቡ፡፡ ኃጢኣቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና፡፡ በጎ ለሠሩት በእርግጥ እንጨምራለን፡፡»
١٦٢
- Sadiq & Sani Habibከእነሱም ውስጥ እነዚያ (ራሳቸውን) የበደሉት ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የኾነን ቃል ለወጡ፡፡ በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል መዐትን ከሰማይ ላክንባቸው፡፡
١٦٣
- Sadiq & Sani Habibከዚያችም በባህሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በቅዳሜ (ቀን) ወሰን ባለፉ ጊዜ በሰንበታቸው ቀን ዐሳዎቻቸው የተከማቹ ኾነው በሚመጡላቸው ጊዜ (የኾነውን) ጠይቃቸው፡፡ ሰንበትንም በማያከብሩበት (በሌላው) ቀን አይመጡላቸውም፡፡ እንደዚሁ ያምጹበት በነበሩት ምክንያት እንሞክራቸዋለን፡፡
١٦٤
- Sadiq & Sani Habibከእነሱም (ከፊሎቹ) ሕዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጪአቸው የኾኑትን ሕዝቦች ለምን ትገስፃጻላችሁ» ባሉ ጊዜ (ገሳጮቹ) «ወደ ጌታችሁ በቂ ምክንያት እንዲኾንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው» አሉ፡፡
١٦٥
- Sadiq & Sani Habibበእርሱም የተገሰጹበትን ነገር በተዉ ጊዜ እነዚያን ከክፉ የሚከለከሉትን አዳንን፤ እነዚያንም የበደሉትን ያምጹ በነበሩት ምክንያት በብርቱ ቅጣት ያዝናቸው፡፡
١٦٦
- Sadiq & Sani Habibከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወረዶች ዝንጀሮች ኹኑ አልን፤» (ኾኑም)፡፡
١٦٧
- Sadiq & Sani Habibጌታህም እስከ ትንሣኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ሰው በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መኾኑን ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሳቸው)፡፡ ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ እርሱም በእርግጥ እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
١٦٨
- Sadiq & Sani Habib(የእስራኤልን ልጆች) በምድር ላይ የተለያዩ ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው፡፡ ከእነሱ መልካሞች አሉ፡፡ ከእነሱም ከዚያ ሌላ አልሉ፡፡ ይመለሱ ዘንድም በተድላዎችም በመከራዎችም ሞከርናቸው፡፡
١٦٩
- Sadiq & Sani Habibከኋላቸውም፡- መጽሐፉን የወረሱ መጥፎ ምትኮች ተተኩ፡፡ የዚህን የቅርቡን ጠፊ ጥቅም ይይዛሉ፡፡ ብጤውም ጥቅም ቢመጣላቸው የሚይዙት ሲኾኑ « (በሠራነው)፡- ለኛ ምሕረት ይደረግልናል» ይላሉ፡፡ በአላህ ላይ ከእውነት በቀር እንዳይናገሩ በእነርሱ ላይ የመጽሐፉ ቃል ኪዳን አልተያዘባቸውምን በእርሱ ውስጥ ያለውንም አላነበቡምን የመጨረሻይቱም አገር ለእነዚያ ጌታቸውን ለሚፈሩት በላጭ ናት፡፡ አታውቁምን
١٧٠
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም መጽሐፉን ጠብቀው የሚይዙ ሶላትንም በደንቡ የሰገዱ እኛ የመልካም ሠሪዎችን ዋጋ አናጠፋም፡፡
۞١٧١
- Sadiq & Sani Habibየጡርን ተራራ ነቅለን ከበላያቸው እንደ ጥላ ኾኖ በአነሳነውና እርሱም በነሱ ላይ ወዳቂ መኾኑን ባረጋገጡ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «የሰጠናችሁን በብርታት ያዙ፡፡ ትጠነቀቁም ዘንድ በውስጡ ያለውን ተገንዘቡ» (አልን)፡፡
١٧٢
- Sadiq & Sani Habibጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና «ጌታችሁ አይደለሁምን» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡ «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ፡፡ «በትንሣኤ ቀን ከዚህ (ኪዳን) ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፡፡»
١٧٣
- Sadiq & Sani Habibወይም «(ጣዖታትን) ያጋሩት ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው፡፡ እኛም ከእነሱ በኋላ የኾን ዘሮች ነበርን፡፡ አጥፊዎቹ በሠሩት ታጠፋናለህን» እንዳትሉ (አስመሰከርናችሁ)፡፡
١٧٤
- Sadiq & Sani Habibእንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡
١٧٥
- Sadiq & Sani Habibየዚያንም ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን ከጠማሞቹም የኾነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው፡፡
١٧٦
- Sadiq & Sani Habibበሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡
١٧٧
- Sadiq & Sani Habibየእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትና ነፍሶቻቸውን ይበድሉ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ከፋ!
١٧٨
- Sadiq & Sani Habibአላህ የሚያቀናው ሰው ቅን እርሱ ነው፡፡ የሚያጠመውም ሰው እነዚያ ከሳሪዎቹ እነሱ ናቸው፡፡
١٧٩
- Sadiq & Sani Habibከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ለእነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤
١٨٠
- Sadiq & Sani Habibለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ (ስትጸልዩ) በእርሷም ጥሩት፡፡ እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፡፡ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይምመነዳሉ፡፡
١٨١
- Sadiq & Sani Habibከፈጠርናቸውም ሰዎች በእውነት የሚመሩ በእርሱም (ፍርድን) የሚያስተካክሉ ሕዝቦች አልሉ፡፡
١٨٢
- Sadiq & Sani Habibእነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ (ምቾትን በመጨመር) እናዘነጋቸዋለን፡፡
١٨٣
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ ጥበቤ ብርቱ ነውና፡፡
١٨٤
- Sadiq & Sani Habibበነቢያቸው (በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መኾኑን አያስተውሉምን እርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
١٨٥
- Sadiq & Sani Habibበሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛው ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜያቸውም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መኾኑን አያስተውሉምን ከእርሱም (ከቁርኣን) ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ፡፡
١٨٦
- Sadiq & Sani Habibአላህ የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኝ የለውም፡፡ በጥምመታቸውም ውስጥ እየዋለሉ ይተዋቸዋል፡፡
١٨٧
- Sadiq & Sani Habibከሰዓቲቱ መቼ እንደምትረጋ (እንደምትመጣ) ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ነው፡፡ በጊዜዋ እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጣትም፡፡ በሰማያትና በምድርም ከበደች፡፡ በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣችሁም» በላቸው፡፡ ከእርሷ አጥብቀህ እንደ ተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡
١٨٨
- Sadiq & Sani Habib«አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡ ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፡፡ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡
۞١٨٩
- Sadiq & Sani Habibእርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው፡፡ በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች፡፡ እርሱንም (ፅንሱን) ይዛው ኼደች፡፡ በከበደችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንኾናለን፤» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ፡፡
١٩٠
- Sadiq & Sani Habibመልካም ልጅ በሰጣቸውም ጊዜ በሰጣቸው ልጅ (ስም) ለእርሱ ተጋሪዎችን አደረጉለት፡፡ አላህም ከሚያጋሩት ሁሉ ላቀ፡፡
١٩١
- Sadiq & Sani Habibምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን
١٩٢
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)
١٩٣
- Sadiq & Sani Habib(ጣዖቶቹን) ወደ ቅን መንገድ ብትጠሩዋቸውም አይከተሉዋችሁም፡፡ ብትጠሩዋቸው ወይም እናንተ ዝምተኞችም ብትኾኑ በእናንተ ላይ እኩል ነው፡፡
١٩٤
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገ³ቸው ብጤዎቻችሁ ተገዢዎች ናቸው፡፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ጥሩዋቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ፤ (መመለስ ግን አይችሉም)፡፡
١٩٥
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱ በእርሳቸው የሚኼዱባቸው እግሮች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በርሳቸው የሚጨብጡባቸው እጆች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸውን ወይስ ለእነሱ በእርሳቸው የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸውን «ያጋራችኋቸውን ጥሩ ከዚያም ተተናኮሉኝ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ፤ (አልፈራችሁም)» በላቸው፡፡
١٩٦
- Sadiq & Sani Habib«የእኔ ረዳቴ ያ መጽሐፉን (ቁርኣንን) ያወረደልኝ አላህ ነውና፤ እርሱም መልካም ሠሪዎችን ይረዳል» (በላቸው)፡፡
١٩٧
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም ከእርሱ በቀር የምትገ³ቸው ሊረÇችሁ አይችሉም፡፡ ነፍሶቻቸውንም አይረዱም፡፡
١٩٨
- Sadiq & Sani Habib«ወደ ቅንም መንገድ (እንዲመሩዋችሁ) ብትጠሩዋቸው አይሰሙም፤» (በላቸው)፡፡ እነርሱንም የማያዩ ሲኾኑ ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡
١٩٩
- Sadiq & Sani Habibገርን ጠባይ ያዝ፡፡ በመልካምም እዘዝ፡፡ ባለጌዎቹንም ተዋቸው፡፡
٢٠٠
- Sadiq & Sani Habibከሰይጣንም (በኩል) ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
٢٠١
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፡፡ ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ፡፡
٢٠٢
- Sadiq & Sani Habibወንድሞቻቸውም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል፤ ከዚያም (እነርሱ) አይገቱም፡፡
٢٠٣
- Sadiq & Sani Habibበተዓምርም ባልመጣሃቸው ጊዜ (በራስህ) «ለምን አትፈጥራትም» ይላሉ፡፡ ከጌታዬ ወደኔ የተወረደውን ብቻ እከተላለሁ፡፡ ይህ (ቁርኣን) ከጌታችሁ ሲኾን ለሚያምኑ ሕዝቦች መረጃዎችና መምሪያ እዝነትም ነው በላቸው፡፡
٢٠٤
- Sadiq & Sani Habibቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡
٢٠٥
- Sadiq & Sani Habibጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡
۩٢٠٦
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ ያወድሱታልም፡፡ ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ፡፡