القلم
Al-Qalam
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibነ.(ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም፡፡
- Sadiq & Sani Habibላንተም (ከጌታህ) የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አልለህ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፡፡
- Sadiq & Sani Habibዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮችም አትታዝዙ፡፡
- Sadiq & Sani Habibብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን፡፡
- Sadiq & Sani Habibለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን፤
- Sadiq & Sani Habibልበ ደረቅን፣ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየገንዘብና የልጆች ባለቤት በመኾኑ (ያስተባብላል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibበአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡
- Sadiq & Sani Habibያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱ» በማለት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡
- Sadiq & Sani Habibዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነን» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibትክክለኛቸው «ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤» (አሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡
- Sadiq & Sani Habibለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን?
- Sadiq & Sani Habibለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?
- Sadiq & Sani Habibበውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል)
- Sadiq & Sani Habibወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን?
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) «ተጋሪዎች» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ «ተጋሪዎቻቸውን» ያምጡ፡፡
- Sadiq & Sani Habibባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነርሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ኾነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፡፡ (እነርሱን እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱንም አዘገያለሁ፡፡ ዘዴዬ ብርቱ ነውና፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?
- Sadiq & Sani Habibወይስ እነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር ዕውቀት አልለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?
- Sadiq & Sani Habibለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ ዓሣው ባለቤትም (እንደ ዮናስ) አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታውም (በነቢይነት) መረጠው፡፡ ከደጋጎቹም አደረገው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ፡፡ «እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነው» ይላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡