الحاقة

Al-Haqqah

ሱራ 69 · መካ · 52 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 78

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibእውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአረጋጋጪቱም (እርሷ) ምንድን ናት!
  1. Sadiq & Sani Habibአረጋጋጪቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habibሰሙድና ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፋ፤ (ተወደሙ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ ሕዝቦቹንም፤ በውስጧ የተጣሉ ኾነው ልክ ክፍት የኾኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእነርሱም ቀሪን ታያለህን?
  1. Sadiq & Sani Habibፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየጌታቸውንም መልእክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፡፡ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የኾነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበቀንዱም አንዲት መንነፋት በተነፋች ጊዜ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሣኤ) ትኾናለች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይም ትቀደዳለች፡፡ ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመላእክትም በየጫፎችዋ ላይ ይኾናሉ፡፡ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ያዙት፤ እሰሩትም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በኾነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ ታላቅ በኾነው አላህ አያምንም ነበርና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibድኾችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ (ይባላል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበምታዩትም ነገር እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበማታዩትም ነገር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ (ቁርኣን) የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤
  1. Sadiq & Sani Habibበኀይል በያዝነው ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም (ቁርኣን) ለጥንቁቆቹ መገሠጫ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛም ከእናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም (ቁርኣን) በከሓዲዎቹ ላይ ጸጸት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡