المعارج
Al-Ma'arij
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibመላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibመልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡
- Sadiq & Sani Habibጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡
- Sadiq & Sani Habibዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሚስቱም በወንድሙም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibየራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡
- Sadiq & Sani Habibክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡
- Sadiq & Sani Habibለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡
- Sadiq & Sani Habibየጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
- Sadiq & Sani Habibከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
- Sadiq & Sani Habibይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
- Sadiq & Sani Habibያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡