الجن
Al-Jinn
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habib(ሙሐመድ ሆይ!) በል «እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች (ቁርኣንን) አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም› አሉ ማለት ወደእኔ ተወረደ፡፡
- Sadiq & Sani Habib‹ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡›
- Sadiq & Sani Habib‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡›
- Sadiq & Sani Habib‹እነሆም ቂላችን በአላህ ላይ ወሰን ያለፈን (ውሸት) ይናገር ነበር፡፡›
- Sadiq & Sani Habib‹እኛም ሰዎችና ጋኔኖች በአላህ ላይ ውሸትን (ቃል) አይናገሩም ማለትን ጠረጠርን፡፡›
- Sadiq & Sani Habib‹እነሆም ከሰዎች የኾኑ ወንዶች በጋኔን ወንዶች ይጠበቁ ነበሩ፡፡ ኩራትንም ጨመሩዋቸው፡፡›
- Sadiq & Sani Habib‹እነርሱም አላህ አንድንም አይቀሰቅስም ማለትን እንደጠረጠራችሁ ጠረጠሩ፡፡›
- Sadiq & Sani Habib‹እኛም ሰማይን (ለመድረስ) ፈለግን፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡
- Sadiq & Sani Habib‹እኛም ከእርሷ (ወሬን) ለማደመጥ በመቀመጫዎች እንቀመጥ ነበርን፡፡ አሁን ግን የሚያዳምጥ ሰው ለእርሱ ተጠባባቂ ችቦን ያገኛል፡፡
- Sadiq & Sani Habib‹እኛም በምድር ውስጥ ባልሉ ሰዎች ክፉ ተሽቷል? ወይስ በእነርሱ ጌታቸው ደግን ነገር ሽቷል? ማለትን አናውቅም፡፡
- Sadiq & Sani Habib‹እኛም ከእኛ ውስጥ ደጎች አልሉ፡፡ ከኛም ከዚህ ሌላ የኾኑ አልሉ፡፡ የተለያዩ መንገዶች (ባለ ቤቶች) ነበርን፡፡
- Sadiq & Sani Habib‹እኛም አላህን በምድር ውስጥ ፈጽሞ የማናቅተው፤ ሸሽተንም ፈጽሞ የማናመልጠው መኾናችንን አረጋገጥን፡፡
- Sadiq & Sani Habib‹እኛም መሪውን በሰማን ጊዜ በርሱ አመንን፡፡ በጌታውም የሚያምን ሰው መግጎደልንም መጭጨመርንም አይፈራም፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አልሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»
- Sadiq & Sani Habibበዳዮቹማ ለገሀነም ማገዶ ኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆም በመንገዲቱ ላይ ቀጥ ባሉ ኖሮ ብዙ ዝናምን ባጠጣናቸው ነበር (ማለትም ተወረደልኝ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱ ልንሞክራቸው (ባጠጣናቸው ነበር)፡፡ ከጌታውም ማስታወሻ የሚያፈገፍግ ሰው አስቸጋሪን ቅጣት ያገባዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ (በውስጣቸው) ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ (ማለትም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆም የአላህ ባሪያ (ሙሐመድ አላህን) የሚጠራው ኾኖ በተነሳ ጊዜ (ጋኔኖች) በእርሱ ላይ ድርብርቦች ሊኾኑ ቀረቡ (ማለትም)፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኔ የምግገዛው ጌታየን ብቻ ነው፡፡ በእርሱም አንድንም አላጋራም» በል፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ቀጥታንም አልችልም» በላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኔ ከአላህ (ቅጣት) አንድም አያድነኝም፡፡ ከእርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኝም» በላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከአላህ የኾነ ማድረስን መልክቶቹንም በስተቀር (አልችልም)፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚያምጽ ሰው ለእርሱ የገሀነም እሳት አልለው፡፡ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ፡፡»
- Sadiq & Sani Habibየሚስፈራሩበትንም ባዩ ጊዜ ረዳቱ ደካማ፣ ቁጥሩም አነስተኛ የኾነው ማን እንደኾነ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የምትስፈራሩበት ነገር ቅርብ ወይም ጌታየ ለእርሱ የተወሰነ ጊዜን የሚያደርግለት (ሩቅ) መኾኑን አላውቅም» በላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«(እርሱ) ሩቁን ምስጢር ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»
- Sadiq & Sani Habibከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ (ለሌላ አይገልጽም)፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)፡፡