القيامة
Al-Qiyamah
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habib(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?
- Sadiq & Sani Habibአይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡
- Sadiq & Sani Habibባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habib«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአላመነምም አልሰገደምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?
- Sadiq & Sani Habibየሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
- Sadiq & Sani Habibከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?