المدثر

Al-Muddaththir

ሱራ 74 · መካ · 56 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 4

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibአንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ!
  1. Sadiq & Sani Habibተነሳ አስጠንቅቅም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጌታህንም አክብር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibልብስህንም አጥራ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጣዖትንም ራቅ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ፤ (በረከትን) አትለግስለለ
  1. Sadiq & Sani Habibለጌታህም (ትዕዛዝ) ታገሥ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበቀንዱም በተነፋ ጊዜ (ነገሩ ይበረታል)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህም (ጊዜ) ያ ቀን አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበከሓዲዎች ላይ ገር ያልኾነ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእርሱም የተዘረጋን ገንዘብ (በያይነቱ) ያደረግሁለት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(በያደባባዩ) ተገኝዎች የኾኑ ወንዶች ልጆችንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለእርሱም (ኑሮውን) መዘርጋትን የዘረጋሁለት (ከኾነ ሰው ገር ተዎኝ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም ልጨምርለት ይከጅላል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይከልከል፤ እርሱ ለአንቀጾቻችን በእርግጥ ተቃዋሚ ነበር፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርግጥ ችግርን አስገድደዋለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ (በቁርኣን ነገር) ሐሰበ፤ ገመተም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተረገመም፤ እንዴት ገመተ!
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም (ከሞት በኋላ) ተረገመ፡፡ እንዴት ገመተ!
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም እንደ ገና (በቁርኣኑ ነገር) ተመለከተ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም ፊቱን አጨፈገገ፤ አኮማተረም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም (ከማመን) ዞረ፤ ኮራም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአለም «ይህ (ከሌላ) የሚቀዳ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ይህ የሰው ቃል እንጅ ሌላ አይደለም፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibበሰቀር ውስጥ በእርግጥ አገባዋለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰቀር ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habib(ያገኘችውን ሁሉ) አታስቀርም አትተውምም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቆዳን በጣም አክሳይ ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ (ዘበኞች) አሉባት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየእሳትንም ዘበኞች መላእክት እንጅ ሌላ አላደረግንም፡፡ ቁጥራቸውንም ለእነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፡፡ እነዚያ መጽሐፍን የተሰጡት እንዲያረጋግጡ፣ እነዚያም ያመኑት እምነትን እንዲጨምሩ፣ እነዚያም መጽሐፍን የተሰጡትና ምእምናኖቹ እንዳይጠራጠሩ፣ እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው (መናፍቃን)፣ ከሓዲዎችም አላህ በዚህ (ቁጥር) ምን ምሳሌ ሽቷል? እንዲሉ (እንጅ አላደረግንም)፡፡ እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡ የሚሻውንም ያቀናል፡፡ የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እርሷም (የሰቀር እሳት) ለሰዎች መገሰጫ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ከክህደት) ይከልከሉ፡፡ በጨረቃ እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበሌሊቱም በኼደ ጊዜ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበንጋቱም ባበራ ጊዜ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሷ (ሰቀር) ከታላላቆቹ (አደጋዎች) አንዷ ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለሰዎች አስፈራሪ ስትኾን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከእናንተ (ወደ በጎ ነገር) መቅደምን ወይም ወደ ኋላ መቅረትን ለሻ ሰው (አስፈራሪ ስትኾኑ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?»
  1. Sadiq & Sani Habib(እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib«እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡»
  1. Sadiq & Sani Habibየአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከግሣጼዬም (ከቁርኣን) የሚያፈገፍጉት ለእነርሱ ምን አልላቸው?
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ አህዮች ይመስላሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዐንበሳ የሸሹ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይልቁንም ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ የተዘረጉ ጽሑፎችን እንዲስሰጥ ይፈልጋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይከልከሉ፡፡ ይልቁንም የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) አይፈሩም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይከልከሉ፡፡ እርሱ (ቁርኣን) መገሠጫ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibስለዚህ የሻ ሰው ይገሰጽበታል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህም ካልሻ በስተቀር አይገሠጹም፡፡ እርሱ (አላህ) የመፈራት ባለቤት የምሕረትም ባለቤት ነው፡፡