المرسلات
Al-Mursalat
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibተከታታይ ኾነው በተላኩት፣
- Sadiq & Sani Habibበኀይል መንፈስን ነፋሾች በኾኑትም፣
- Sadiq & Sani Habibመበተንን በታኞች በኾኑትም፤ (ነፋሶች)፣
- Sadiq & Sani Habibመለየትን ለይዎች በኾኑትም፣
- Sadiq & Sani Habibመገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም፣
- Sadiq & Sani Habibምክንያትን ለማስወገድ ወይም ለማስፈራራት (ጣይዎች በኾኑት መላእክት) እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibያ የምትስፈራሩበት (ትንሣኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዋክብትም (ብርሃንዋ) በታበሰች ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰማይም በተከፈተች ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibጋራዎችም በተንኮተኮቱ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመልክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለየትኛው ቀን ተቀጠሩ (የሚባል ሲኾን)፤
- Sadiq & Sani Habibለመለያው ቀን (በተባለ ጊዜ፤ በፍጡሮች መካከል ይፈረዳል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየፊተኞቹን (ሕዝቦች) አላጠፋንምን?
- Sadiq & Sani Habibከዚያም የኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን?
- Sadiq & Sani Habibበተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በማሕፀን) አደረግነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእስከ ታወቀ ልክ ድረስ፡፡ መጠንነውም፤ ምን ያማርንም
- Sadiq & Sani Habibመጣኞች ነን!
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን?
- Sadiq & Sani Habibሕያዋን ኾናችሁ ሙታንም ኾናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበውስጧም ከፍተኛዎችን ተራራዎች አደረግን፡፡ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት (ቅጣት) አዝግሙ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ባለ ሦስት ቅርንጫፎች ወደ ኾነው ጥላ አዝግሙ፤» (ይባላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibአጠላይ ያልኾነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ኾነው (አዝግሙ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ቃንቄውም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ የማይናገሩበት ቀን ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ፤ ለእነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ መለያው ቀን ነው፡፡ እናንተንም የፊተኞቹንም ሰብሰብናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ፡፡
- Sadiq & Sani Habibላስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?