النبإ

An-Naba

ሱራ 78 · መካ · 40 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 80

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibከምን ነገር ይጠያየቃሉ?
  1. Sadiq & Sani Habibከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?
  1. Sadiq & Sani Habibጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?
  1. Sadiq & Sani Habibብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአትክልቶችና ወይኖችም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡