النازعات
An-Nazi'at
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበኃይል አውጪዎች በኾኑት፤
- Sadiq & Sani Habibበቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤
- Sadiq & Sani Habibመዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤
- Sadiq & Sani Habibመቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤
- Sadiq & Sani Habibነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤
- Sadiq & Sani Habibለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)»
- Sadiq & Sani Habib«ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሙሳ ወሬ መጣልህን?
- Sadiq & Sani Habibጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡
- Sadiq & Sani Habibበለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?»
- Sadiq & Sani Habib«ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡
- Sadiq & Sani Habibታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአስተባበለም፤ አመጸም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ኾኖ ዞረ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም፡፡
- Sadiq & Sani Habibአለም፡- «እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡»
- Sadiq & Sani Habibአላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በእርግጥ መገምገሚያ አለበት፡፡
- Sadiq & Sani Habibባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡
- Sadiq & Sani Habibከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም፡፡
- Sadiq & Sani Habibሌሊቷንም አጨለመ፡፡ ቀንዋንም ገለጸ፡፡
- Sadiq & Sani Habibምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡
- Sadiq & Sani Habibውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡
- Sadiq & Sani Habibጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእናንተና ለእንስሶቻችሁ መጣቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፣
- Sadiq & Sani Habibሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን፣
- Sadiq & Sani Habibገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፣
- Sadiq & Sani Habibየካደ ሰውማ፣
- Sadiq & Sani Habibቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፣
- Sadiq & Sani Habibገሀነም እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibበጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ
- Sadiq & Sani Habibገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከሰዓቲቱ መቼ ነው መኾኛዋ?» ሲሉ ይጠይቁሃል፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ?
- Sadiq & Sani Habib(የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፏዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡