التكوير
At-Takwir
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibየዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibእንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibበሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibበምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤
- Sadiq & Sani Habibጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibገነትም በተቀረበች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤
- Sadiq & Sani Habibተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibበንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibእርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡