الإنفطار

Al-Infitar

ሱራ 82 · መካ · 19 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 82

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibመቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤
  1. Sadiq & Sani Habibየተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habib(እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡