العاديات

Al-'Adiyat

ሱራ 100 · መካ · 11 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 14

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibእያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤
  1. Sadiq & Sani Habibበማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤
  1. Sadiq & Sani Habibበ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibበልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡