الزلزلة

Az-Zalzalah

ሱራ 99 · መዲና · 8 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 93

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡