القارعة

Al-Qari'ah

ሱራ 101 · መካ · 11 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 30

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤
  1. Sadiq & Sani Habibምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት!
  1. Sadiq & Sani Habibቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habibሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤
  1. Sadiq & Sani Habibጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡)
  1. Sadiq & Sani Habibሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤
  1. Sadiq & Sani Habibእርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤
  1. Sadiq & Sani Habibመኖሪያው ሃዊያህ ናት
  1. Sadiq & Sani Habibእርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habib(እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡