التكاثر
At-Takathur
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡
- Sadiq & Sani Habibተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡
- Sadiq & Sani Habibገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡