الهمزة

Al-Humazah

ሱራ 104 · መካ · 9 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 32

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habibየተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡