النجم
An-Najm
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከልብ ወለድም አይናገርም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡
- Sadiq & Sani Habibታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን?
- Sadiq & Sani Habibበሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡
- Sadiq & Sani Habibበመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤
- Sadiq & Sani Habibእርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡
- Sadiq & Sani Habibቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን?
- Sadiq & Sani Habibሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?)
- Sadiq & Sani Habibለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን?
- Sadiq & Sani Habibይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡
- Sadiq & Sani Habibለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን?
- Sadiq & Sani Habibመጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (የጠመመውንና የቀናውን ያውቃል)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን?
- Sadiq & Sani Habibጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን?)
- Sadiq & Sani Habibየሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን?
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን?
- Sadiq & Sani Habibበዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?)
- Sadiq & Sani Habib(እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibመጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡
- Sadiq & Sani Habibያለበሳትንም አለበሳት፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?
- Sadiq & Sani Habibይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?
- Sadiq & Sani Habibትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን?
- Sadiq & Sani Habibእናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡