القمر
Al-Qamar
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡
- Sadiq & Sani Habibተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዜናዎችም በእርሱ ውስጥ መገሰጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መጣላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሙሉ የኾነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አያብቃቁም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ኾነው፤ ፍጹም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸኳዮች ኾነው (ይወጣሉ)፡፡ ከሓዲዎቹ (ያን ጊዜ ምን ይላሉ?) «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፡፡ ባሪያችንንም (ኑሕን) አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ ነውም» አሉ፡፡ ተገላመጠም፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ጠራ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡፡
- Sadiq & Sani Habibየምድርንም ምንጮች አፈነዳን፡፡ ውሃውም (የሰማዩና የምድሩ) በእርግጥ በተወሰነ ኹነታ ላይ ተገናኘ፡፡
- Sadiq & Sani Habibባለ ሳንቃዎችና ባለሚስማሮች በኾነችም ታንኳ ላይ ጫንነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበጥበቃችን ስር ኾና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረው ሰው ምንዳ (ይህንን ሠራን)፡፡
- Sadiq & Sani Habibተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፡፡ ከተገሳጭም አልለን?
- Sadiq & Sani Habibቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?
- Sadiq & Sani Habibቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?
- Sadiq & Sani Habibዓድ አስተባበለች፡፡ ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ!
- Sadiq & Sani Habibእኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በኀይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰዎቹን ልክ ከሥሮቻቸው የተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው (ከተደበቁበት) ትነቅላቸዋለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?
- Sadiq & Sani Habibቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- Sadiq & Sani Habibሰሙድ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከእኛ የኾነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያን ጊዜ በስህተትና በዕብደት ውስጥ ነን» አሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ከኛ መካከል በእርሱ ላይ (ብቻ) ማስገንዘቢያ (ራእይ) ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» (አሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibውሸታሙ ኩሩው ማን እንደኾነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትኾን ዘንድ ላኪዎች ነን፡፡ ተጠባበቃቸውም፡፡ ታገስም፡፡
- Sadiq & Sani Habibውሃውንም በመካከላቸው የተከፈለ መኾኑን ንገራቸው፡፡ ከውሃ የኾነ ፋንታ ሁሉ (ተረኞቹ) የሚጣዱት ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibጓደኛቸውንም ጠሩ፡፡ ወዲያውም (ሰይፍን) ተቀበለ፡፡ ወጋትም፡፡
- Sadiq & Sani Habibቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?
- Sadiq & Sani Habibእኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው፡፡ ወዲያውም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ ርግጋፊ ኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibቁርኣንንም ለመገንዘብ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- Sadiq & Sani Habibየሉጥ ሕዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ (እነርሱንስ) በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእኛ በኾነ ጸጋ (አዳንናቸው)፡፡ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibብርቱይቱን አያያዛችንንም በእርግጥ አስጠነቀቃቸው፡፡ በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት፡፡ ወዲያውም ዓይኖቻቸውን አበስን፡፡ «ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (አልናቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበማለዳም ዘውታሪ የኾነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib«ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (ተባሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- Sadiq & Sani Habibየፈርዖንንም ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡዋቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበተዓምራቶቻችን በሁሏም አስተባበሉ፡፡ የብርቱ ቻይንም አያያዝ ያዝናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሓዲዎቻችሁ ከእነዚህ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለናንተ በመጽሐፎች ውስጥ (የተነገረ) ነፃነት አላችሁን?
- Sadiq & Sani Habibወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉን?
- Sadiq & Sani Habibክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይምመታሉ፡፡ ጀርባዎችንም ያዞራሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ቀጠሮዋቸው ናት፡፡ ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibአመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው በሚጎተቱበት ቀን «የሰቀርን መንካት ቅመሱ» (ይባላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት አንዲት (ቃል) እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- Sadiq & Sani Habibየሠሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibትንሹም ትልቁም ሁሉ የተጻፈ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እነርሱም ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ቻይ የሆነው ንጉሥ ዘንድ ናቸው፡፡