الرحمن
Ar-Rahman
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibአል-ረሕማን፤
- Sadiq & Sani Habibቁርኣንን አስተማረ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰውን ፈጠረ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመናገርን አስተማረው፡፡
- Sadiq & Sani Habibፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡
- Sadiq & Sani Habibበውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡
- Sadiq & Sani Habibየገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡
- Sadiq & Sani Habibጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibየሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
- Sadiq & Sani Habibሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibእንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
- Sadiq & Sani Habibእናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibየጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibየቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibየውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibየበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?›
- Sadiq & Sani Habibከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibበሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- Sadiq & Sani Habibየግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡