المطففين
Al-Mutaffifin
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን?
- Sadiq & Sani Habibበታላቁ ቀን፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
- Sadiq & Sani Habibየታተመ መጽሐፍ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
- Sadiq & Sani Habibየታተመ መጽሐፍ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡
- Sadiq & Sani Habibተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habibባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡
- Sadiq & Sani Habibበነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡
- Sadiq & Sani Habibዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡