الإنشقاق
Al-Inshiqaq
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
- Sadiq & Sani Habibምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibበውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡
- Sadiq & Sani Habibአንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡
- Sadiq & Sani Habibመጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤
- Sadiq & Sani Habibበእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡
- Sadiq & Sani Habibመጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤
- Sadiq & Sani Habib(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡
- Sadiq & Sani Habibአይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡
- Sadiq & Sani Habibአትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤
- Sadiq & Sani Habibበጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)
- Sadiq & Sani Habibበእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibአላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡