البروج
Al-Buruj
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibየቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበተቀጠረው ቀንም፤
- Sadiq & Sani Habibበተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibየጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?
- Sadiq & Sani Habibየፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡