الطارق
At-Tariq
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
- Sadiq & Sani Habibጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
- Sadiq & Sani Habibከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
- Sadiq & Sani Habibእርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibእርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
- Sadiq & Sani Habibእነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡