الأعلى

Al-A'la

ሱራ 87 · መካ · 19 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 8

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመናጢውም ይርቃታል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibመጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡