الغاشية
Al-Ghashiyah
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibየሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?
- Sadiq & Sani Habibፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተደረደሩ መከዳዎችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
- Sadiq & Sani Habibወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!
- Sadiq & Sani Habibወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
- Sadiq & Sani Habibወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)
- Sadiq & Sani Habibአስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤
- Sadiq & Sani Habibአላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
- Sadiq & Sani Habibመመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡