الفجر
Al-Fajr
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበጎህ እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዐሥር ሌሊቶችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበጥንዱም በነጠላውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን?
- Sadiq & Sani Habibጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን?
- Sadiq & Sani Habibበኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡
- Sadiq & Sani Habibበፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?)
- Sadiq & Sani Habibበእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡
- Sadiq & Sani Habibሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibበሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡
- Sadiq & Sani Habibድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibመላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ?
- Sadiq & Sani Habib«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡
- Sadiq & Sani Habibበዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡
- Sadiq & Sani Habibየእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ!
- Sadiq & Sani Habib«ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡
- Sadiq & Sani Habib«በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡
- Sadiq & Sani Habibገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡