البلد

Al-Balad

ሱራ 90 · መካ · 20 አንቀጾች · የወረደበት ቅደም ተከተል፦ 35

ጽሕፈት
ትርጉሞች

ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
  1. Sadiq & Sani Habibበዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
  1. Sadiq & Sani Habib«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibአንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
  1. Sadiq & Sani Habibለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
  1. Sadiq & Sani Habibምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
  1. Sadiq & Sani Habibዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
  1. Sadiq & Sani Habib(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibየዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
  1. Sadiq & Sani Habibወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
  1. Sadiq & Sani Habib(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibእነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
  1. Sadiq & Sani Habibበእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡