الشمس
Ash-Shams
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibበቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibበሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤
- Sadiq & Sani Habibበሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤
- Sadiq & Sani Habibበምድሪቱም በዘረጋትም፤
- Sadiq & Sani Habibበነፍስም ባስተካከላትም፤
- Sadiq & Sani Habibአመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habib(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡
- Sadiq & Sani Habib(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡
- Sadiq & Sani Habibሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡
- Sadiq & Sani Habibጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡
- Sadiq & Sani Habibፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡