الليل
Al-Layl
ጽሕፈት
ትርጉሞች
ንባቡን፣ አወቃቀሩንና ሥሩን ለማየት የዐረብኛ ቃል ይንኩ።
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
- Sadiq & Sani Habibበሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibበቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡
- Sadiq & Sani Habibወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡
- Sadiq & Sani Habibበመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤
- Sadiq & Sani Habibለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibየሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤
- Sadiq & Sani Habibበመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤
- Sadiq & Sani Habibለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
- Sadiq & Sani Habibበወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡
- Sadiq & Sani Habibቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡
- Sadiq & Sani Habibመጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibየምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡
- Sadiq & Sani Habibከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡
- Sadiq & Sani Habibያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡
- Sadiq & Sani Habibአላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡
- Sadiq & Sani Habibያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡
- Sadiq & Sani Habibለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡
- Sadiq & Sani Habibግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡
- Sadiq & Sani Habibወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡